KIYA BUNO Bedele

KIYA BUNO Bedele I am a Digital creator to entartain and educate adult people all over the world

08/05/2025
31/03/2025

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ 1 ሺ 446ኛውን የኢድ አል አድሀ /አረፋ/በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺ 446ኛው የኢድ አል አድሀ /አረፋ/በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን።

በዓሉ የሰላም፣የጤና የመተሳሰብ እና የአንድነት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።

የኢድ አል አድሀ(አረፋ ) በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በድምቀት ከሚያከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው።

በዓሉ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ዕሴቶቻችንን ከፍ አድርገን የምታሳይበት እንደመሆኑ ወገኖቻችንን የምናስብበት እንደሚሆን አምናለሁ ።

በመሆኑም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማገዝና ማዕድ በማጋራት በዓሉን እንዲያሳልፍ አደራ እላለሁ።

በድጋሜ መልካም የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓል!
ኢድ ሙባረክ!!
አቶ ሙሉጌታ ጉልማ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

31/03/2025
17/09/2024
17/09/2024

አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2035 የአፍሪካ ቁልፍ ከተማ ትሆናለች -

አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2035 የአፍሪካ ቁልፍ ከተማ እንደምትሆን የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ያወጣው ሪፖርት አመላከተ፡፡

ተቋሙ “የአፍሪካ ከተሞች 2035” በሚል ርዕስ ባወጣው ሪፖርት አዲስ አበባን ጨምሮ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ከተሞች በከፍተኛ ፍጥነት ሊያድጉ እንደሚችሉ አስታውቋል።

እንደ ካይሮ፣ ሌጎስ እና ጆሃንስበርግ ያሉ የአፍሪካ ግዙፍ ከተሞች የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን እንደሚያስቀጥሉ ሲጠበቅ እንደ አዲስ አበባ ያሉ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ከተሞች ደግሞ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ትንበያው አመላክቷል፡፡

አዲስ አበባን ተከትለው ከፍተኛ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ከተገመቱት ከተሞች መካከል ብራዛቪል፣ ዳሬሰላም እና ሉዋንዳ ይገኙበታል።

ዕድገቱ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን፣ የከተሞች መስፋፋት እና በአቅራቢያ ያሉ የትላልቅ ከተሞች መፈጠር አንደሚያካትት ሪፖርቱ ያመላክታል።

ከአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ በማስመዝገብ አንዷ ሆና እውቅና ያገኘችው አዲስ አበባ እስከ ፈረንጆቹ 2035 ድረስ በዓመት ባለ ሁለት አሃዝ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት (ጂዲፒ) እንደምታስመዘግብም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በአንፃሩ እንደ ናይሮቢ እና አቡጃ ያሉ ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከ6 በመቶ እስከ 8 በመቶ የዕድገት ምጣኔ እንደሚኖራቸውም ሪፖርቱ ይጠቅሳል።

17/09/2024

ብዝሀነታችንን ለአብሮነታችን በማዋል ማህበራዊ ፀጋዎቻችንን እናጠናክር!

ኢትዮጵያ በተፈጥሯዊ፣ በቁሳዊ እና በመንፈሳዊ ሀብቶቿ የታደለች፣ በአግባቡ አልምታ መጠቀም ከቻለች ከራሷ አልፋ ለሌሎች መትረፍረፍ የምትችል ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል ፣ የቀን አቆጣጠር ፣ መልክዓ ምድር ያላት የብዙ ባህል ፣ ቋንቋ ፣ ትውፊት እና እሴት ባለቤት የሆነች፣ ቀደምት ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሀገራት መካከልም አንዷ መሆኗ እሙን ነው።

ብዝሀ ባህሎቻችን ብቻ ብንመለከት እንደ ሀገር በዓለም መድረኮች እውቅና እንድናገኝ ያደረጉን ቅርሶቻችን ናቸው፡፡ ህዝባዊም ሆነ ሀይማኖታዊ በዓላት አንድነታችንን እና አብሮነታችንን በማጠናከር ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውተዋል፤ እየተጫወቱም ይገኛል።

ብዝሀ ባህሎቻችንን በማዳበር እና እሴታቸውን ጠብቀው ለዓለም ጭምር እንዲተርፉ ለማስቻል ፓርቲያችን በማህበራዊ ፕሮግራሙ ያመላከተ ሲሆን በተጨባጭም እየተጋ ይገኛል፡፡ ባህሎቻችን ጥላሸት እንዲለብሱ፣ እንዳይዳብሩ፣ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ማጠናከሪያ ሳይሆን የመገፋፋት፣ የመጠላለፍ እንዲሁም የሁከትና ብጥብጥ ምክንያት እንዲሆኑ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲሰራ ስለነበር ለህዝባችንና ለሀገራችን ማበርከት የሚገባቸውን እንዳያበረክቱ አድርጎ ቆይቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን በህብር ያደመቁን በርካታ ብዝሀ ማንነቶች ቢኖሩንም የሚያመሳስሉንም በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ለከፉፉዮች እና ለነጣጣዮች የማንመች ህዝቦች መሆናችንን በተግባር በማሳየት በተለይም ከለውጡ በኋላ ህብረ- ብሔራዊ አብሮነታችን ደምቆ መታየት ጀምሯል፡፡

ቀደምት እናት አባቶቻችን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነው ጭምር አብሮነታችንን የሚያጠናክሩ ህዝባዊም ሆነ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችንን ጠብቀው አስጠብቀው ለትውልድ አስተላልፈዋል።

እኛም የመደመር ወረቶች ላይ የምንደምር የመደመር ትውልድ እንደመሆናችን መልካም እሴቶቻችንን አዳብሮ እና አጎልብቶ ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር ይጠበቅብናል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

17/09/2024

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ( ዶ/ር)

23/08/2024

Address

Addis Ababa Space Science
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KIYA BUNO Bedele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to KIYA BUNO Bedele:

Share