Evangelist Ruth Dawit Aysheshim

Evangelist Ruth Dawit Aysheshim Ruth Dawit is an Ethiopian Pentecostal evangelist known for her dedicated work in spreading the gospel through her ministry, Salvation for All Nations.

Her outreach targets various regions of Ethiopia, emphasizing spiritual transformation.

13/08/2026

የ 2018 አ.ም አገልግሎታችንን የጨረስን ሲሆን ቀሪ ሚሽኖቻችን እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር በሚቀጥለው አመት የሚደረጉ ይሆናሉ። አብራችሁን ያገለገላችሁ ሁሉ በብዙ ተባረኩ።

የልደቴን ሳምንት በማስመልከት ጥያቄዎቻችሁን እመልሳለሁ!! ለህይወታችሁ ልምድና ለትምህርት ይሆኑናል ብላችሁ የምታስቧቸውን እንዲሁም ደግሞ የወዳጅ መልስ ያስፈልጋቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥ...
12/08/2026

የልደቴን ሳምንት በማስመልከት ጥያቄዎቻችሁን እመልሳለሁ!!

ለህይወታችሁ ልምድና ለትምህርት ይሆኑናል ብላችሁ የምታስቧቸውን እንዲሁም ደግሞ የወዳጅ መልስ ያስፈልጋቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥያቄዎች በ comment box አስቀምጡልኝ ካለፍኩባቸው መንገዶች በመነሳት በሰፊው እመልስላችኋለው። ተባረኩልኝ 😍❤😍

''ኢየሱስ ያድናል።''
12/08/2026

''ኢየሱስ ያድናል።''

🌍ሁሉ ይስማ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።
12/08/2026

🌍ሁሉ ይስማ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

11/08/2026
10/08/2026
ከሞአብ እስከ ቤተልሔም ከቤተልሔም እስከ ክርስቶስ የዘር ሀረግ ''ታማኟ ሩት''በረሃብ ምክንያት ከባሏና እና ከሁለት ወንዶች ልጆቿ ጋር ወደ ሰው ሀገር ተሰደደች።  ሞትን ፈርተው ተሰደዱ  መ...
09/08/2026

ከሞአብ እስከ ቤተልሔም
ከቤተልሔም እስከ ክርስቶስ የዘር ሀረግ
''ታማኟ ሩት''

በረሃብ ምክንያት ከባሏና እና ከሁለት ወንዶች ልጆቿ ጋር ወደ ሰው ሀገር ተሰደደች። ሞትን ፈርተው ተሰደዱ መራራ ሞት ግን በመላው ቤተሰቡ ላይ አንዣበበ።

በመጀመሪያ ባሏ ሞተ፤ ሲቀጥል በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በተሰደዱበት ሚስት አግብተው የነበሩ ልጅ እንኳን ያልወለዱ ሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ሞቱ። ባሏንና ልጆቿን ቀብራ ፣ ብቻዋን የቀረች እናት በመራራ ሀዘን ተስፋ ቆርጣ ወደ ሀገሯ ለመመለስ ወሰነች።

ምራቶቿንም ጠርታ "እኔ ምንም አልጠቅማችሁም ወደ ወገኖቻችሁ ተመለሱ" ብላ ብትለምናቸው፣ አንዷ ስማ ወደ ሕዝቧ ተመለሰች። ሌላኛዋ ግን ፍጹም የተለየ ሐሳብ ነበራት። ልቧን የሚቆርጥ ጽኑ ውሳኔ አደረገች፤ የአማቷን እጅ ይዛ፦
«ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናልና እንድተውሽ፣ እንዲልመለስም አትማጸኝኝ፤ ሞት እንጂ ሌላ የሚለየን ነገር የለም» በማለት የዘላለም የታማኝነት ቃል ኪዳን ገባች።

ከዘመዶቿና ከምቾቷ ተለይታ፣ ወደ ማታውቀው አገር ከአማቷ ጋር ተጓዘች። ይህ እርምጃዋ ማንም ሊለካው የማይችል የታማኝነትና የፍቅር ጉዞ ነበር።

ወደ አማቷም ሀገር ሲደርሱ ድሮ አማቷን የሚያቋት ሰዎች ተንጫጩባት "ተውኝ ተዋርጂያለሁ ፣ ባዶ እጄን ተመልሻለሁ ፣ የሚታወቁትን ያንን ስሜን ለውጡት አሁን ማራ(መራራ) ብላችሁ ጥሩኝ።" አለች።

ያልተለየቻት ምራት ግን አማቷን ለመርዳት ፣ ራሷን አዋርዳ ከሰው እርሻ እህል ለመቃረም ፣ ወደ አዝመራ ሜዳ አመራች፣ በእግዚአብሔርም መሪነት የአማቿ ዘመድ የሆነውን ሰው አገኘችው።

ሰውዬው የቸርነት እና የባለጠግነት ምሳሌ ነበር። ስለ እሷ መስዋዕትነት ሰምቶ ነበርና ልቡ በምሕረት ተነካ። «ልጄ ሆይ፣ ስሚ... እግዚአብሔር ላደረግሽው ሥራ ዋጋዋን ይስጥሽ፤ በእስራኤል አምላክ በውኑ በእርሱ ክንፍ ሥር ለመጠጋት መጥተሻልና» በማለት አክብሯት፤ ከእህሉም ሰፈረላት። ...... ተበዣት።

በእስራኤል ሕግ መሠረት አንድ ሰው ንብረቱን ወይም ነጻነቱን ሲያጣ፣ ቅርብ ዘመድ የሆነው "ቤዛ" በመሆን ዕዳውን ይከፍላል፤ ነጻነቱንም ይመልሰዋል። ቦዔዝ ለሩትና ለኑሃሚን ያደረገው ይህንን ነበር። የኑሃሚንን የድህነትና የባዶነት ሕይወት በሀብቱና በፍቅሩ ዋጀው።

እኛም በኃጢአት ባርነት ተይዘን፣ መንፈሳዊ ባዶነት ይዞን በሞት ጥላ ስር ሳለን ፣ ክርስቶስ የእኛ ቅርብ ዘመድ (ሰው) በመሆን መጣ። በመስቀል ላይ ሕይወቱን በመክፈል ከእርግማን ዋጀን። በቸርነቱ ጥላ ሥር ከለለን ፤ ባዶነታችንንም በሰማያዊ በረከት ለወጠው።

ታሪኩ በሩትና በኑሃሚን ህይወት ብቻ አላበቃም። ቦዔዝ ሩትን በሕግ አገባት፤ እግዚአብሔርም ማሕፀኗን ባረከው። ከእነርሱ የተወለደው ኦቤድ፣ የንጉሥ ዳዊት አባት ሆነ። ከእዚያም ዘር ተተክሎ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ።

(መሉ ታሪኩን "ከሩት መጽሐፍ አንብቡ)

"እግዚአብሔር ባዶ ሆኖ ወደ እርሱ የሚመጣውን ሁሉ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ሞልቶ፣ ከጨለማ ወደ ድንቅ ብርሃኑ ያወጣዋል"።

''በሚጨመርላችሁ አዲስ የህይወት ዘመን በሀዘን መንፈስ ፈንታ የደስታን አክሊል እግዚአብሔር ይስጣችሁ''
06/08/2026

''በሚጨመርላችሁ አዲስ የህይወት ዘመን በሀዘን መንፈስ ፈንታ የደስታን አክሊል እግዚአብሔር ይስጣችሁ''

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251994451584

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Evangelist Ruth Dawit Aysheshim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share