FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) This is the official Fana Broadcasting Corporate (FBC) page - where you can get all the latest news in Amharic.

You can follow us on: https://twitter.com/fanatelevision https://t.me/fanatelevision https://www.tiktok.com/ Join us on:

Website: http://www.fanabc.com

Youtube: https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

Telegram: https://t.me/fanatelevision

Twitter: https://twitter.com/fanatelevision

TikTok: https://www.tiktok.com/

Email: [email protected]

SMS: 8222, 8111, 8333

Live FM 98.1 studio tel: 0115 536006, 0115536008, 0115 509151,

Live National Studio Tel: 0115 538084



Addis Ababa, Ethiopia

የባሕል ዲፕሎማሲ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ባህልና ጥልቅ ጥበብ ለማሳየት ያለመ የባሕል ዲፕሎማሲ መድረክ ዛሬ ማምሻውን በአ...
19/09/2025

የባሕል ዲፕሎማሲ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ባህልና ጥልቅ ጥበብ ለማሳየት ያለመ የባሕል ዲፕሎማሲ መድረክ ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትሮችና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የባሕል ስራዎችና የጥበብ ክዋኔዎች ቀርበዋል፡፡

የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) በዚሁ ወቅት÷ የ13 ወር ጸጋ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የፍጥረት መነሻና ዛሬም የሚወሱ የበርካታ ታሪኮች ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው፥ አሁንም ታሪክ እየሰራች ቀጥላለች ብለዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን ባህልና ጥልቅ ጥበብ ለማሳየት ያለመና ግንኙነትን እንደሚያዳብር ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መርቃ አዲስ ዓመትን በተቀበለችበት ማግስት መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።

የባሕል ዲፕሎማሲ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም አውጥቶ ከመጠቀም አንፃር እየተሰሩ ላሉ ተግባራትም ማሳያ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

19/09/2025

በጉጉት የሚጠበቀው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍጻሜው ፍልሚያ #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናላምሮት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን
فانا_عربي_بودكاست

19/09/2025

የቅዳሜ ጠዋት የፋና 90 ጉዳዮች …

19/09/2025

ደስታ፣ ዕውቅና፣ ቃል ኪዳን . . . #ወቅታዊ #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #እንግዳ #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን

19/09/2025

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስልጣን ሰጡ
👉የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት

የዛሬ ምሽት የሬድዮ ዜና መፅሔት ጉዳዮች👉 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በተለይ ከኃይል አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፣ እስክ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ቱሪዝም ምን በረከቶች ...
19/09/2025

የዛሬ ምሽት የሬድዮ ዜና መፅሔት ጉዳዮች

👉 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በተለይ ከኃይል አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፣ እስክ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ቱሪዝም ምን በረከቶች ይኖሩታል?

👉 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ የነበራቸው የገንዘብ እና የዲፕሎማሲ ላቅ ያለ አስተዋጽዖን እንቃኛለን።

👉 ከ13 ዓመት በፊት በአራት ወረዳዎች መተግበር የጀመረው የጤና መድህን አግልግሎት በእስካሁኑ ጉዞው ምን ስኬት ተመዘገበበት? የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን እና ተገልጋዮችን አናግረንበታል።


👉ወደ ኮሚሽንነት ያደገው የናይል ትብብር ማዕቀፍ፤ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? የኮሚሽኑ መቋቋምስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምን እንዴት ያስጠብቃል?

👉በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በመንግስት እና በህብረተሰቡ አጋርነት ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሃብት የትምህርት ዘርፉን ለማጠናከር ፈሰስ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር ነግሮናል።

👉 አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ያቀረበውን የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪ ውድቅ አደረገች።

👉 ስፖርት - ዛሬ የተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች

የእለቱ አብይ ርእሰ ጉዳዮች በዝርዝር እና በትንታኔ።

የዜና ክፍል ጋዜጠኞች እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ዘገባዎችን አካተው በፋና የምሽቱ ዜና መጽሔት ሊያስደምጧችሁ ዝግጁ ናቸው።

ጌታቸው አለሙ ይጠብቃችኋል።

በኤፍ ኤም 98.1 እና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ኤፍ ኤሞቻችን እንዲሁም www.fanamc.com በመላው ሃገሪቱና በዓለም ዙሪያ ስርጭታችንን መከታተል ትችላላችሁ።

ከምሽቱ 1:ሰዓት ይጠብቁን።

በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተ...
19/09/2025

በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ተደረገ።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው፥ የተጠርጣሪዎቹ የገንዘብ እንቅስቃሴ ታግዶ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በሂደት ላይ ይገኛል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በህጋዊ መንገድ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን እየተጠቀሙ ቢሆንም አንዳንድ አካላት ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ለማትረፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው በክትትል ተረጋግጧል።

በተጨማሪም አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ የክትትል መረጃው ውጤት የሚያመላክት በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አገልግሎቱ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ተግባርና ሌሎች መሰል የወንጀል ድርጊቶች ላይ ተሳታፊ በሆኑ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

19/09/2025

ደስታ፣ ዕውቅና፣ ቃል ኪዳን . . . ዛሬ ምሽት 1፡00 በፋና ፖድካስት ይጠብቁን

#ወቅታዊ #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #እንግዳ #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን

19/09/2025

የፖለቲካ ታሪካችንን ከእምነት ወደ እውቀት … -ከታሪክ፣ ቅርስ እና ባህል ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያ (ፕ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ

እሁድ 8፡00 በፋና ፖድካስት ይጠብቁን

#ለሀገር #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን

ወላይታ ድቻ እና አል ኢትሃድ አቻ ተለያዩ
19/09/2025

ወላይታ ድቻ እና አል ኢትሃድ አቻ ተለያዩ

ወላይታ ድቻ እና አል ኢትሃድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ከአል ኢትሃድ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያን የሚወክለው ወላይታ ድቻ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሊቢያው አል ኢትሃድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል።

ወላይታ ድቻ የመልሱን ጨዋታ ከሳምንት በኋላ ከሜዳው ውጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለ...
19/09/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ. እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) - የብሔራዊ ባንክ ገዥ

2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

19/09/2025

አንድ እድል - ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

Address

Addis Ababa, Ethiopia Infront Of Black Lion Hospital
Addis Ababa
P.O.BOX30702

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.):

Share