09/06/2025
ውጭ ሀገር ስንሄድ "መቼ ነው ኢትዮጵያስ እንደዚህ ውብ እና ምርጥ ከተማ የምትሆነው?" እያልን የምንቀና ሰዎች ግን ለምንድነው የእኛ ሀገር ሲሰራና ሲለማ አይሆንም የምንለው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ልዩ ቆይታ የ ኢትዮጵያ ከተሞች ከአለም ከተሞች ጋር የተወዳሪ ከተማ የመሆን ሂደት ላይ እንዳሉ ከራሳቸው እና ከሀገር ወዳድ ዜጎች ፍላጎት በመነሳት እንዲህ ገልጸውታል፡፡
ውጭ ሀገር ሲሄድ ስለ ኢትዮጵያ የማይቀና ሰው የለም፤ ሁላችንም "መቼ ነው ኢትዮጵያስ እንደዚህ የምትሆነው?" እያልን እንቀናለን
የዛሬ 20 ዓመት ሻንጋይ ሄደው እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በወቅቱ ካየሁት የህንፃው እና የመንገዱ ብዛት፣ የከተማው ስፋት አንፃር መቼ ነው ሀገሬ እንደዚህ ዓይነት መልክ የምትይዘው? ይህ እንዲያውስ ይቻላል ወይ? የሚለውን ሳስበው ነገሩ ተስፋ አስቆራጭ መስሎኝ ስጋት ነበረኝ ብለዋል።
በቅርቡ ሻንጋይ በድጋሚ ሲሄዱ ግን ሀገሬ እንደሻንጋይ መሆን ትችል ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከፍራቻ ወደ ተስፋ እና እርግጠኝነት ተቀይሮ ነው የተመለስኩት፤ ምክንያቱም ይቻላል የሚለውን ፍንጭ በሀገሬ አይቼው ነበርና ሲሉ ተናግረዋል።
ብዙ ሰዎች ሌላ ሀገር ሄደው በሚያዩት የተለያየ ነገር "ሀገራችንም ቢመጣ?" በማለት እንደሚመኙ ጠቅሰው፤ ነገር ግን ያ ያዩት፣ የተመኙት ነገር በሀገራቸው ሲሰራ ደግሞ "የለም፣ አንፈልግም" ብለው እንደሚቃወሙ አንስተዋል። ይህ የእኛ ልምምድና ባህል እየሆነ ነው፤ ጠንከር ያለ ሥራ ሲሰራ ብዙ ስላልለመድን ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልፀውታዋል።
መቼም በሀገራችን ታሪክ እንደዚህ በከሞቻችን ጠንከር ያለ ልማታዊ እና ሀገራዊ ለወጥ ተደርጎ አይታወቅም ይህንን ለመቀበል አና የልማቱ አካል ለመሆን መቸገራችን ከመጣንበት የኋላ ታሪካችን ጠንከር ያሉ ለውጦችን ካለመለማመዳችን የተነሳ መሆኑ ግልጽነው፡፡
ሆኖም ዛሬ ላይ ኢትዮጵዊያን የአለምን ፈጣን እድገት እና ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለልጆቻችን ምቹ ና ተመራጭ ከተማን ለመገንባት ትላልቅ ምዕራፎችን መሻገራችን እያለፍንበት ያለነው እና አማራጭ የሌለው መፍትሄ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ዝግጁ መሆን እና መደገፍ እንጂ ምኞት ብቻ ሆነን መቅረት የለብንም ፡