FANA FM98.1 Radio News

FANA FM98.1 Radio News Welcome to Fana 98.1 Radio News! https://www.youtube.com/channel/UC4E6LQ_lqIlbA_GwoVw8tAA
(2)

ማንቸስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 አሸነፈበእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንማውዝን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል...
24/08/2026

ማንቸስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 አሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንማውዝን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ቦርንማውዝ በ26ኛው ደቂቃ በታቨርኒየር ግብ መሪ መሆን ቢችሉም፣ ማንቸስተር ሲቲዎች በ85ኛው ደቂቃ በማርክ ጉሂ ግብ አቻ ሆነዋል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በጭማሪ ሰዓት 90+2 ላይ ጆስኮ ግቫርዲዮል ሁለተኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሮ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ብራይተን በአሜክስ ስታዲየም አስቶን ቪላን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

#

22/08/2026

Man United vs Hull City (0-2) HIGHLIGHTS

ማንቸሰተር ዩናይትድ ውድድሩን በሽንፈት ጀመረ ትላንት በተጀመረው የ2026/27 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኤምኬኤም ስታዲየም አዲስ አዳጊውን ሃል ሲቲን የገጠመው ማንቸስተር ዩ...
22/08/2026

ማንቸሰተር ዩናይትድ ውድድሩን በሽንፈት ጀመረ

ትላንት በተጀመረው የ2026/27 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኤምኬኤም ስታዲየም አዲስ አዳጊውን ሃል ሲቲን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 ተሸንፏል።

አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ዮሪ ቴሌማንስና አንድሬ ሳንቶስ ቋሚ ተሰላፊ ሆነው በጀመሩበት እንዲሁም ማርከስ ራሽፎርድ ተቀይሮ በገባበት ጨዋታ፤ ሃል ሲቲ የማሸነፊያዎቹን ሁለት ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ ነው ያስቆጠረው።

17ኛው ደቂቃ ላይ ሰሚ አጃዬ እንዲሁም ኖቤል ሜንዲ 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች ሃል ሲቲ የውድድር ዓመቱን በድል እንዲጀምር አስችለዋል።

በታሪኩ በፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዩናይትድን አሸንፎ ለማያውቀው ሃል ሲቲ ይህ ድል የመጀመሪያ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

16/08/2026

Arsenal vs Manchester city

አርሰናል የ2026 የእንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን አነሳ*****************በካርዲፍ ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም በተካሄደው በኮሚዩኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ሲቲን 3 ...
16/08/2026

አርሰናል የ2026 የእንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን አነሳ
*****************

በካርዲፍ ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም በተካሄደው በኮሚዩኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ አርሰናል ማንቸስተር ሲቲን 3 ለ 0 በመርታት የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሪካርዶ ካላፊዮሪ 1ኛው ደቂቃ ላይ፣ ካይ ሃቨርትዝ 28ኛው ደቂቃ ላይ፤ እንዲሁም ማርቲን ኦዲጋርድ በሁለተኛው አጋማሽ 48ኛው ደቂቃ ላይ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

የቀደመው የውድድር ዓመት የፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ አሸናፊዎች እርስ በርስ በሚያደርጉት በዚህ ጨዋታ፤ አርሰናል ከሦስት ዓመታት በኋላ ነው ዳግም ዋንጫውን ያነሳው።

በታሪኩ ያነሳቸውን የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫዎች ቁጥርም 18 አድርሷል።

አርሰናል 2-0 እየመራ ረፍት ወተዋል
16/08/2026

አርሰናል 2-0 እየመራ ረፍት ወተዋል

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ - የኮሚዩኒቲ ሺልድ አሸናፊን የሚለየው ፍልሚያ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል የ2026 የኢንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሺልድ ዓመታዊ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል። የኢንግ...
16/08/2026

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ - የኮሚዩኒቲ ሺልድ አሸናፊን የሚለየው ፍልሚያ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል

የ2026 የኢንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሺልድ ዓመታዊ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል። የኢንግሊዝ እግር ኳስ የውድድር ዘመን መክፈቻ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ መርሐ-ግብር፣ የቀደመውን የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን አርሰናልን ከኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ማንቸስተር ሲቲ አገናኝቷል።

ይህ ታሪካዊ ጨዋታ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከለንደን ውጭ በዌልስ ካርዲፍ በሚገኘውና 74,500 ተመልካቾችን በሚይዘው ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም ይካሄዳል።

የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን የሚኬል አርቴታው አርሰናል፣ በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ወቅት ከጂሮና እና ኤምኬ ዶንስ ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በድል ቢያጠናቅቅም፣ ከሪያል ቤቲስና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ገጥሞታል።

ሆኖም ባለፈው ረቡዕ ከጣሊያኑ ክለብ ኮሞ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመለያ ምት በማሸነፍ ለዚህ የዋንጫ ፍልሚያ መልካም ስንቅ ሰንቋል።

የአርሰናሉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ለመድፈኞቹ ስጋት ሆኗል።

ለማንቸስተር ሲቲ ይህ ጨዋታ የፔፕ ጋርዲዮላ ስኬታማ ዘመን አብቅቶ ከአዲሱ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ጋር የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው።

ሲቲ በቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት ጨዋታዎች ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ከኬ ሊግ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች የ3 ለ 1 ተከታታይ ድል አስመዝግቧል።

በሁለቱ ቡድኖች የቅርብ ጊዜ ግንኙነት ማንቸስተር ሲቲ የበላይነት አለው። ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ሲቲ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፣ አርሰናል አንድ ጊዜ ባለ ድል ሆኗል። በተቀሩት ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡

የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን አርሰናል 17 ጊዜ፣ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ 7 ጊዜ አንስተዋል። በ2023 አርሰናል ሲቲን በመለያ ምት አሸንፎ ዋንጫውን ማንሳቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

✅✅በወዳጅነት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ✅✅በቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ሊድስ ዩናይትድን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1 ለ 1 በሆነ ...
12/08/2026

✅✅በወዳጅነት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ✅✅

በቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት መርሐ-ግብር ሊድስ ዩናይትድን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቅቋል።
ለማንቸስተር ዩናይትድ ጆሹዋ ዚርክዚ ሲያስቆጥር፣ ለሊድስ የኣቻነቷን ግብ ብሬንደን አሮንሰን ከመረብ አሳርፏል።
አሸናፊውን ለመለየት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቶ ማንቸስተር ዩናይትድ 5 ለ 4 ረቷል።
በሌላ የወዳጅነት ጨዋታ አርሰናል ኮሞ 1907ን ገጥሞ በተመሳሳይ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቅቋል።

ልዊስ ስኬሊ ለአርሰናል፣ ማርቲን ባቱሪና ደግሞ ለኮሞ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

አሸናፊውን ለመለየት ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቶ አርሰናል 4 ለ 3 አሸንፏል።

12/08/2026

ኤቨርተን ከኒውካስትል ያደረጉት ጨዋታ ሃይላይት

09/08/2026

አርሰናል-ከቦርሲያ

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FANA FM98.1 Radio News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share