Kidame News

Kidame News ፈጣን እና እውነተኛ መረጃዎችን ያግኙ

የፍርድ ቤት ውሳኔ * 16 ዓመት አደይ ጌታቸው ፅኑ እስራት * 15 ዓመት ሉንጎ ሉቃስ ፅኑ እስራት የአለልኝ አዘነ ግድያ እና የተላለፈው ፍርድ!የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነን በ...
22/07/2025

የፍርድ ቤት ውሳኔ

* 16 ዓመት አደይ ጌታቸው ፅኑ እስራት
* 15 ዓመት ሉንጎ ሉቃስ ፅኑ እስራት

የአለልኝ አዘነ ግድያ እና የተላለፈው ፍርድ!

የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነን በመግደል ወንጀል ተከሰው የነበሩት ባለቤቱ ወ/ሮ አደይ ጌታቸው እና የእህቷ ባል ሉንጎ ሉቃስ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጽኑ እስራት ተፈረደባቸው።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት ባስተላለፈው ውሳኔ፣

1. ወ/ሮ አደይ ጌታቸው የ16 ዓመት ጽኑ እስራት ሲፈረድባቸው፣

2. የባለቤቱ የእህቷ ባል (ሉንጎ ሉቃስ) ላይ ደግሞ የ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተበይኖበታል።

ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተከሰተው አለልኝ አዘነ እና ባለቤቱ ከተጋቡ ከ15 ቀናት በኋላ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር።

ፍርድ ቤቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች መሠረት ወንጀሉ መፈጸሙን ካረጋገጠ በኋላ ይህን ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።

የአለልኝ አዘነ ግድያ በብዙዎች ዘንድ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ክስተት ሆኖ ሲነገር ቆይቷል።

ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣቸውን አወጡኦባማ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳይ በ AI የተፈጠረ ቪዲዮ አጋርተዋል ነው የተባለውየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ...
21/07/2025

ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣቸውን አወጡ

ኦባማ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳይ በ AI የተፈጠረ ቪዲዮ አጋርተዋል ነው የተባለው

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ ትኩረትን የሚስብ እና አነጋጋሪ የሆኑ ተከታታይ ልጥፎችን አጋርተዋል ተብሏል።

የትራምፕ የማህበራዊ ሚዲያ ቁጣ ከቱልሲ ጋባርድ ስለ ኦባማ አስተዳደር የ"ትራምፕ-ሩሲያ ትብብር" ታሪክን እንደፈጠረ የሚያሳዩ ሰነዶችን ከማጋራቷ ጀምሮ፣ የዴሞክራት ፖለቲከኞችን ብርቱካናማ ዩኒፎርም (የእስረኛ ልብስ) ለብሰው የሚያሳዩ ምስሎችን መልሶ እስከ ማጋራት ደርሷል ነው የተባለው።

በተለይ ትኩረትን የሳበው እና ውዝግብ የፈጠረው ልጥፍ ደግሞ በሰው ሰራሽ አድታውሎት(Artificial Intelligence - AI) የተፈጠረ ቪዲዮ ሲሆን፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኦቫል ቢሮ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳይ ነበር ተብሏል።

የዚህ አይነቱ በ AI የተፈጠረ ይዘት መሰራጨት በፖለቲካዊ ዘመቻዎች ውስጥ የሐሰት መረጃ ስርጭት አሳሳቢነትን ዳግም አንስቷል ነው የተባለው።

ትራምፕ በእንቅስቃሴያቸው፣ ቀደም ሲል በኦባማ አስተዳደር ላይ የቀረቡ ክሶችን መልሰው በማንሳት እና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪዎቻቸውን በተለያዩ መንገዶች በመተቸት ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።

ይህ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዙሪያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ በ AI የተፈጠሩ የውሸት ምስሎች እና ቪዲዮዎች (deepfakes) የፖለቲካ ክርክሮችን ሊያዛቡ እና ህዝባዊ መተማመንን ሊያሳጡ የሚችሉ አደገኛ መሳሪያዎች ናቸው ተብሏል።

ይህ የትራምፕ ልጥፍ በዲጂታል ዘመን የሐሰት መረጃዎችን የመለየት አስፈላጊነትን እና በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚደረጉ የይዘት ቁጥጥርን አስመልክቶ አዳዲስ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ ተመላክቷል።

መነኸሪያ ኤፍ ኤም

አልዋሊድ ቢን ካሌድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ! እንቅልፋም ልዑል'ከ20 ዓመታት ኮማ በኋላ 'እንቅልፋም ልዑል' በመባል የሚታወቀው ልዑል አልዋሊድ ቢን ካሌድ ቢን ታላል ዛሬ ቅዳሜ ከዚህ ዓለም...
19/07/2025

አልዋሊድ ቢን ካሌድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ! እንቅልፋም ልዑል'

ከ20 ዓመታት ኮማ በኋላ 'እንቅልፋም ልዑል' በመባል የሚታወቀው ልዑል አልዋሊድ ቢን ካሌድ ቢን ታላል ዛሬ ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተዘግቧል።

ልዑል አልዋሊድ እ.ኤ.አ. በ2005 ለትምህርት ወደ ለንደን ባቀኑበት ወቅት ባጋጠማቸው ከባድ የመኪና አደጋ ሳቢያ ኮማ ውስጥ ከገቡ በኋላ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ምንም ሳያውቁ ቆይተዋል።

አባታቸው ልዑል ካሌድ ቢን ታላል የልጃቸውን ህይወት ለመታደግ ላደረጉት ጥረት እና ላሳዩት ጽናት አድናቆትን አትርፈዋል።

የቀብር ስነ ስርዓቱ ነገ እሁድ ዕለት ከዐስር ሶላት በኋላ በሪያድ በሚገኘው ኢማም ቱርኪ ቢን አብዱላህ መስጊድ ይፈጸማል።

የልዑል አልዋሊድ ታሪክ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ የነካ ሆኗል

ዜናየቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሕወሓት እና የፌዴራል መንግስቱን ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡እየተባባሰ የሄደውን የሕወሓት እና ፌዴራል መንግስቱን ውጥረት ተከትሎ የቀድ...
18/07/2025

ዜና

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሕወሓት እና የፌዴራል መንግስቱን ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

እየተባባሰ የሄደውን የሕወሓት እና ፌዴራል መንግስቱን ውጥረት ተከትሎ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች ስብሰባ ለመጥራት ማቀዳቸውን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይሁንና ግን ይህ የንግግር ጥሪ ከማዕከላዊ መንግስቱ ተቃውሞ እንደገጠመው ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው እለት ከትግራይ ከተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ጋር መነጋገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

የአለልኝ አዘነ ሞት ጉዳይ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል! የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሟቹ ተጫዋች * ባለቤት እና * የባለቤቱ እህት ባል በሞቱ ተጠያቂ ናቸው ሲል ወስኗል። ይህ ውሳኔ አለል...
18/07/2025

የአለልኝ አዘነ ሞት ጉዳይ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል! የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሟቹ ተጫዋች

* ባለቤት እና
* የባለቤቱ እህት ባል በሞቱ ተጠያቂ ናቸው
ሲል ወስኗል።

ይህ ውሳኔ አለልኝ ራሱን አጥፍቶ እንዳልሞተ በግልፅ አረጋግጧል።

የፍርድ ቤቱ ዝርዝር ውሳኔ ከሰዓት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ የፍትህ ሂደት የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ከሰዓት በኃላ እንጠብቃለን::

ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች !መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " -" ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመ...
11/07/2025

ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች !

መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " -

" ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመለስም ! "

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ አከባቢ ነዋሪዎች " በአዲስ የመዋቅር ጥናት እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወረዳዉ መንግስት እንዲያነጋግን ብንጠይቅም ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘታችን በአደባባይ ወጥተን ድምፃችንን ለማሰማት ተሰብስበናል "ብለዋል

ከሀዋሳ ከተማ አዲስ የመዋቅር አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የተናገሯቸው መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ሕዝቡ የወረዳው መንግስት ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ነገር ግን የሚያናግር አካል ባለመምጣቱ 18 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ባለሃብቶችን ያካተተ የሕብረተሰቡ ተወካዮች ተሰይመዉ በየደረጃው የመንግስት አካላትን እንዲያነጋግሩ ቢላኩም ተገቢው ምላሽ ስላልተሰጣቸው ሕዝቡ ሜዳ ላይ ተሰብስቦ መዋሉን አስረድተዋል።

የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ " ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ባፋኖ አከባቢ ያሉ አምስት ቀበሌያት በአዲስ መልክ ይዋቀራል በተባለዉ የሀዋሳ አንድ ክፍለ ከተማ ስር ተካተዋል " መባሉ ነዉ ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ " ይህ የወረዳዉን አቅም ያዳክመዋል የሚል ቅሬታ ሕዝቡ ዘንድ ፈጥሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዛሬዉ ዕለትም ' የሚያናግራችሁ የመንግስት አመራር ይመጣል ' ተብለን ቀኑን ሙሉ ብንጠበቅም እንደተባለው ባለመምጣቱ ሕዝቡ በነቅስ ወደ ወረዳ አስተዳዳሪዉ ቢሮ ሄዷል ' አመራሩ ተነጋግሮ ያነጋግራችኋል ' ተብለን ምላሽ ባለመምጣቱ ሕዝቡ ' የሚያነጋግረን የመንግስት አካል እስኪመጣ ወደ ቤታችን አንመለስም ' በማለት ምሽቱንም በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስቦ ይገኛል "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል !በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የጭካኔ የግድያ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኞች ተብለው የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው። ተከሳሾቹ ለፍርድ ውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል ...
11/07/2025

የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል !

በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የጭካኔ የግድያ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኞች ተብለው የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።

ተከሳሾቹ ለፍርድ ውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል በማለት " የቆየ ህመም አለብን " ቢሉም የመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሃኪሞች የምርመራ ማስረጃ " የቆየ ህመም የለባቸውም " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የመቐለ ማእላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ ግድያ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?

የተጠርጣሪ ጠበቆች ትናንት ሀምሌ 3 " ደምበኞቻችን የቆየ ህመም አለባቸው ይህንን ለማረጋገጥ የህክምና ማስረጃ ለአርብ ሀምሌ 4 እናቀርባለን " ብለው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ይህን ተቀብሎ ለዛሬ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

ዛሬ አርብ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም ከመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰዓት በፊት ቤተሰብ የሚገኙባቸው የሚድያና የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች በፍርድ ቤቱ በራፍ ደርሰው ተሰባስበዋል።

ተከሳሾች ለውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል ብለው የጠየቁት የህክምና ማስረጃ የቆየ ህመም እንደሌለባቸው አረጋግጧል።

ዳኞችም ይህን ካረጋገጡ በኋላ በተከሳሾች ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል።

አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ያሬድ ገብረስላሰ በላይ እና ኣንገሶም ሃይለማርያም በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመርካታቸው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች የወንጀል ደርጊቱን ከማጠራት እስከ ምርመራና ውሳኔ ድረስ በችግሮች የተተበተበ እንደነበር በመግለፅ ማረሚያ ቤት የፍርድ ውሳኔውን በጥብቅ እንዲተገብረው ጠይቀዋል።

" የጭካኔ ግድያው የሞት ፍርድ ያሰጥ ነበር " ያሉ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የተበዳይ ቤተሰቦች ወደ ቀጣዩ የፍርድ ቤት ይግባኝ ይጠይቁ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሳቢያ ሊቋረጥ መሆኑ ተሰምቷልየዘንድሮው የበጎ ሰው የሽልማት መርሃ ግብር በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ላይካሄድ እንደሚችል ተሰማ፡፡ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ ...
11/07/2025

የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሳቢያ ሊቋረጥ መሆኑ ተሰምቷል

የዘንድሮው የበጎ ሰው የሽልማት መርሃ ግብር በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ላይካሄድ እንደሚችል ተሰማ፡፡
ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ መጨረሻ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በጎ አስተዋፅኦ ላደርጉ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ድርጅቱን በሚደግፉ ተቋማት የፋይናንስ እጥረት ሳቢያ የመቋረጥ አደጋ እንዳጋጠው ተነግሯል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ላለፉት 10 ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ ሽልማቱን ሲደግፍ የቆየው ሄኒከን ኢትዮጵያ የቢራ ማስታውቂያ በብሮድካስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ መታገዱን ምክንያት በማድረግ የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት ሽልማቱን ስፖንስር ከሚያደርግበት በጀት ጋር የማይመጣጠን ማስታስታወቂያ ሽፋን በመሰጠቱ የተነሳ የስፖንሰር ድጋፉን ማቋረጡ ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማትን እንደ ቴሌና ንግድ ባንክ ባሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስፖንስር ለማስደረግና ለማስቀጠል የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት ላይካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበና በበጎ ፈቃደኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት በጀቱን አሁንም በለጋሾች ድጋፍ ነው የሚያካሂደው፡፡

ቁምነገር ሚዲያ

ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ...
11/07/2025

ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።

በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች " በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

CAPITAL

ዩቲዩብ የትኞቹን ከክፍያ አገደ?📌ዩቲዩብ ከጁላይ 15 ጀምሮ የገቢ ማግኛ (monetization) ፖሊሲውን እያጠበቀ ነው።ዋናው ትኩረቱ "ኦሪጅናል ያልሆኑ" (inauthentic)፣ "በብዛት የ...
11/07/2025

ዩቲዩብ የትኞቹን ከክፍያ አገደ?

📌ዩቲዩብ ከጁላይ 15 ጀምሮ የገቢ ማግኛ (monetization) ፖሊሲውን እያጠበቀ ነው።

ዋናው ትኩረቱ "ኦሪጅናል ያልሆኑ" (inauthentic)፣ "በብዛት የሚመረቱ" (mass-produced) እና "ተደጋጋሚ" (repetitious) ይዘቶችን ላይ ነው።

በአጠቃላይ ዩቲዩብ የሚከተሉትን አይነቶች ይዘቶች ከገቢ ማግኛ ሊከለክል ይችላል (አንዳንዶቹ ከዚህ በፊትም ተከልክለው ነበር፣ አሁን ግን ትግበራው ይበልጥ ይጠብቃል ነው የተባለው።

ዩቲዩብ የትኞቹን የገቢ ማግኛ ለመከልከል ወሰነ❓

👉ዝቅተኛ ጥረት የሚጠይቁ እና ተደጋጋሚ ይዘቶች (Low-effort and repetitive content):

🛑ሌሎች ቪዲዮዎችን ወይም ምስሎችን በመውሰድ ምንም አይነት ትርጉም ያለው ለውጥ ሳያደርጉ መልቀቅ።

🛑የተለያዩ ክሊፖችን (clips) አንድ ላይ አቀናብሮ ምንም ተጨማሪ አስተያየት ወይም ትንታኔ ሳይሰጥ መልቀቅ።

🛑በጣም ቀላል የሆኑ የስላይድ ሾው (slideshow) ቪዲዮዎች፣ ለምሳሌ ፎቶዎችን ብቻ በተራ በማሳየት እና ከበስተጀርባ ሙዚቃ በማስገባት።
አንድን ቪዲዮ ፍጥነቱን በመቀየር ወይም ትንሽ በመቁረጥ ብቻ መልቀቅ።

🛑በዋናነት በ AI የተሰሩ ድምፆች (AI-generated voices)። አንድን ጽሑፍ በ AI ድምጽ ብቻ በማንበብ የተሰራ ቪዲዮ፣ ምንም አይነት የፈጣሪው ኦሪጅናል አስተያየት፣ ትንተና ወይም የፈጠራ ስራ ከሌለበት። ለምሳሌ፣ የዜና ዘገባዎችን ወይም የብሎግ ጽሑፎችን በ AI ድምጽ ብቻ የሚያቀርቡ ቻናሎች።

🛑በ AI የተፈጠሩ አምሳያዎች (avatars) ወይም ስክሪፕቶች ብቻ የሚጠቀሙ ቪዲዮዎች፣ ከኋላው የሰው ልጅ እውነተኛ ስሜት ወይም አስተያየት ከሌለበት።

🛑የሌላ ሰውን ይዘት ያለ በቂ "መለወጥ" (transformation) መጠቀም:

"React" ቪዲዮዎች (የሌላ ሰው ቪዲዮ ላይ አስተያየት የሚሰጡ)። የቪዲዮው ፈጣሪ የራሱን አስተያየት፣ ትንተና ወይም የፈጠራ እሴት በግልጽ ማሳየት አለበት።

🛑ቪዲዮውን ብቻ መልቀቅ እና ጥቂት አስተያየት መስጠት በቂ አይደለም።

🛑ከሌሎች ምንጮች (ለምሳሌ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ ፊልሞች) የተወሰዱ ክሊፖችን በመጠቀም አዲስ እና ኦሪጅናል ይዘት ካልተፈጠረ።

♨️ለምን ይህ ለውጥ መጣ?

ዩቲዩብ ይህን ለውጥ ያመጣው በፕላትፎርሙ ላይ "ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው" (low-value) እና "አጠራጣሪ" (inauthentic) ይዘቶች በመብዛታቸው ነው።

እነዚህ ይዘቶች ተመልካቾችን ስለሚያሰለቹ እና ለዩቲዩብ አስተዋዋቂዎችም ጥሩ ስላልሆኑ፣ ዩቲዩብ ተመልካቾች የሚወዱትን እና የሚያምኑበትን ኦሪጅናል እና ጥራት ያለው ይዘት ማበረታታት ይፈልጋል።

በአጠቃላይ ዩቲዩብ ሰዎች እውነተኛ ጥረት የሚያደርጉበትን እና አዲስ ነገር የሚፈጥሩበትን ይዘት ብቻ መክፈል ይፈልጋል ማለት ነው።

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን ቪዛ ቆይታ ወደ ሦስት ወር አሳጠረችበኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታወቀ።ኤምባ...
10/07/2025

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን ቪዛ ቆይታ ወደ ሦስት ወር አሳጠረች

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታወቀ።
ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም. በኤክስ ገፁ ባሰፈረው መረጃ፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ገልጿል።
በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ "ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ" እንደሚኖረው አስታውቋል።
ኤምባሲው በዚሁ የኤክስ ገጽ ልጥፉ ላይ ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።
ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውስጥ ይካተታል።

እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።
አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።
በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም

አሜሪካ የቪዛ አሰጣጥ ፖሊሲዋን በመከለሷ ምክንያት ለጉብኝት፣ ለትምህርት እንዲሁም ለሥራ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ መንገደኞች የሚያገኙት የሦስት ወር ቪዛ ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
ከዚህም በተጨማሪ የያዙት ቪዛ አንድ ግዜ ብቻ መግባት የሚያስችላቸው ይሆናል።

አሜሪካ የቪዛ ፖሊሲዋን ዳግም የከለሰችው የትራምፕ አስተዳደር እአአ ሰኔ 5/2025 የደህንነት ስጋት ናቸው ባሏቸው 12 አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ ክልከላ ማድረጓን ካስታወቀች በኋላ ነው።
ከእነዚህ 12 አገራት መካከል ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኤርትራ፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ይገኙበታል።
ከሳምንት በኋላም ኢትዮጵያን ጨምሮ የ36 አገራት ዜጎች አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ ሃሳብ እንዳለው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጣዊ ሰነድን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር።
ጋና፣ ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ እገዳው ሊጣልባቸው ይችላል ከተባሉ አገራት መካከል ተጠቅሰውም ነበር።

Via BBC

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን አረፈበኢትዮጵያ ቴሌቪዠን የሚድያ ዳሰሳ የሚል ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ታደሰ ሚዛን በትግራይ ክልል ውቕሮ ከተማ በ...
10/07/2025

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን አረፈ

በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን የሚድያ ዳሰሳ የሚል ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ታደሰ ሚዛን በትግራይ ክልል ውቕሮ ከተማ በ1963 ዓ.ም ተወልዶ ፣ ሃምሌ 2/2017 ዓ.ም ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ከጀማሪ ጋዜጠኝነት ጀምሮ እስከ ዳይሬክተርነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ታደሰ በትምህርትም በኢትዮጵያና በአሜሪካ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች እሰከ ዶክትሬት ደረጃ ተምሯል።

ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidame News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kidame News:

Share