31/03/2020
በጊዜያዊነት መስጂዶች እንደሚዘጉ ከጋዜጣዊ መግለጫው ይጠበቃል።
✔©ሙጂብ አሚኖ ዘ ኢስላም
═════ ═════ ═════ ═════ ═════ ═════
መጋቢት 22/2012ማክሰኞ
የፌደራል፣የአዲስ አበባ፣ የኦሮሚያ መጅሊስን ጨምሮ ተጋባዥ ዑለሞች በተገኙበት በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ዙሪያ መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ።
የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጅሊስ መጋቢት 10/2012 ሐሙስ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ከኃይማኖታዊ አስተምርሆ አኳያ ሊያደርግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።
በዐለምም ይሁን ሀገራችን በወረርሺኝ መልኩ እየተዘመተ ስጋት እየሆነ የመጣው የኮሮና ቫይረስን (covid-19) ለመቆጣጠር አገራችን ኢትዮጲያ በተለያዩ አከባቢዎች በቂ ባይሆንም ሕዝባዊ የትራንስፖርት አገልግሎት የማቋረጥ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።
ከቤተ እምነት አኳያም የኢትዮጲያ ኦርቶዳክስ ቤ/ክ የኃይማኖት ማስተማሪያ ማዕከላትን የዘጋች ሲሆን በሙስሊሙ ማሕበረሰብ በኩል የቤተል ተቅዋ ና የባዩሽ መስጂድ ቀዳሚ የመዝጋት ትግበራ አከናውነዋል።
በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጅሊስ መሪነት በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በመግለጫውም ላይ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ መጅሊስን ጨምሮ ተጋባዥ ዑለሞች በተገኙበት በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ዙሪያ መስጂዶች ላይ ስለሚተላለፈው ሁኔታ ይገልፃሉ። በመግለጫውም ላይ በሽታን ለመግታትና የመተላለፊያ መንገዶችን ለመገደብ ሲባል በጊዜያዊነት መስጂዶች ይዘጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሏህ በሽታውን አንስቶልን፣ መሳጂዶች በጊዜ ይከፈቱ ዘንድ ዱዓችን ነው።
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!
አዲሱ ገፄ ይህ ነው...https://m.facebook.com/MujibAminoThe.Islam/
https://m.facebook.com/mujib.amino.the.islam1/
ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!