Hulu Addis on Bisrat FM 101.1 ሁሉ አዲስ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

  • Home
  • Hulu Addis on Bisrat FM 101.1 ሁሉ አዲስ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Hulu Addis on Bisrat FM 101.1 ሁሉ አዲስ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ለወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች የሁሉ አዲስ ሬዲዮ ፕሮግራም ገፃችንን ላይክ ያድርጉ! Current, Hot news guaranteed!
ቴሌግራም ↘️
https://t.me/HuluAddi1

በሰላም ተጠናቋል !እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት ዓመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላምና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።ኮማንድ ፖስቱ የትራፊ...
26/07/2025

በሰላም ተጠናቋል !

እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት ዓመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላምና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ምንም ዓይነት ያጋጠመ ችግር እንዳልነበረ ገልጿል። ኤፍቢሲ ። እንዲሁም ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሯል ። በአዲስአበባ ግቢ ገብርኤልን ጨምሮ በተለያዩ አድባራት በድምቀት ተከብሮ ውሏል ።

የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ በጥበብ ልብስ አዲስ አበባ ገብተዋል ።_______________________ ለ2ተኛው  የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ለመሳተፍ የኡጋንዳ...
26/07/2025

የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ በጥበብ ልብስ አዲስ አበባ ገብተዋል ።
_______________________
ለ2ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ለመሳተፍ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

🇪🇹

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአሜሪካው ጨዋታ ዝግጅቱን ሲቀጥል ለአምስት አዳዲስ ተጫዋቾች ጥሪ  ተደርጓልበመጪው ቅዳሜ በዩናይትድ ስቴትስ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራ...
26/07/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአሜሪካው ጨዋታ ዝግጅቱን ሲቀጥል ለአምስት አዳዲስ ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል

በመጪው ቅዳሜ በዩናይትድ ስቴትስ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዲስ አበባ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ከስብስቡ ውጪ በሆኑ ተጫዋቾች ምትክ ለአዳዲስ ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

- አቡበከር ኑራ፣ ፍሬው ጌታሁን፣ አህመድ ረሺድ፣ አሥራት ቶንጆ፣ ራምኬል ጀምስ፣ ረመዳን የሱፍ፣ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየህ፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ጊት ጋትኮች፣ ሀይደር ሸረፋ፣ በረከት ወልዴ፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ቢንያም በላይ ከቡድኑ ጋር የሚገኙ ሲሆን በአንፃሩ ቢንያም ገነቱ፣ በረከት ደስታ፣ አብዱልከሪም ወርቁ፣ ወገኔ ገዛኸኝ፣ አህመድ ሁሴን፣ መሐመድ አበራ፣ ያሬድ ካሳዬ እና ቢንያም አይተን የአሜሪካ ቪዛ ማግኘት ባለመቻላቸው፤ ምኞት ደበበ እና ቸርነት ጉግሳ ደግሞ የቪዛ ጊዜያቸው በማለቁ ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆነዋል።

- ከስብስቡ ውጪ በሆኑ ተጫዋቾች ምትክ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾች የተካተቱ ሲሆን ከነዓን ማርክነህ፣ አንተነህ ተፈራ፣ አማኑኤል ኤርቦ፣ ሱሌይማን ሀሚድ እና ሻሂድ ሙስጠፋ ሌሎች በአዲስ መልክ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው።

- በአጠቃላይ 20 ተጫዋቾችን ያካተተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እስከ ማክሰኞ ሐምሌ 22 ዝግጅቱን ካከናወነ በኋላ በዛው ዕለት ምሽት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚያቀና ይሆናል።

መረጃ …ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ውስጥ በቪዛ ምክንያት ስምንት ተጫዋቾች ከስብስብ ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከቅዱስ...
25/07/2025

መረጃ …

ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ውስጥ በቪዛ ምክንያት ስምንት ተጫዋቾች ከስብስብ ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ለግራ መስመር ተከላካዩ ሻይዱ ሙስጠፋ እና ለፊት መስመር አጥቂው አማኑኤል ኤርቦ ጥሪ አድርገዋል ሁለቱም ነገ ሐምሌ 19 /2017 ቡድኑን የሚቀላቀሉ ይሆናል።
viva sanjaw

ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ።*** አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ...
25/07/2025

ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ።
***
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ያፌት አለማየው የተባለው ተጠርጣሪ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ትኬት ቆራጭ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው 7ኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ የቲኬት መሽጫ ቢሮ ነው፡፡

ተጠርጣሪው ከድርጅቱ ህጋዊ ቲኬት ጋር የሚመሳሰል ሀሰተኛ ትኬቶችን በማዘጋጀት ለደንበኞች ሲሸጥ በቲኬት ተቆጣጣሪዎች ጥቆማ ሰጪነት ከ553 ሀሰተኛ ትኬቶች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየጣራበት መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት የመንግስትና የህዝብ ሀብትን በህገ-ወጥ መንገድ ለግል ጥቅሙ ለማዋል በፈፀመው ወንጀል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም በአቋራጭ ሀብት ለማፍራት የሚጥሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ረገድ ሁሉም ዜጋ የኃላፊነት ድርሻውን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል።

በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ "ወደ ማዶ" የተሰኘ ትያትር ጉዞ ሊጀመር ነው።ትያትሩን ከማሳየት ጎን ለጎን ለልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ የገቢ ማሰባሰቢያ ይካሄዳል።የኪነ ጥበብ ስራዎች...
25/07/2025

በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ "ወደ ማዶ" የተሰኘ ትያትር ጉዞ ሊጀመር ነው።

ትያትሩን ከማሳየት ጎን ለጎን ለልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ የገቢ ማሰባሰቢያ ይካሄዳል።

የኪነ ጥበብ ስራዎችን በአለም አቀፍ መድረኮች ይዞ የመጓዝ እና የማሳየት የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ዋካ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እስካሁን ባልተለመደ መልኩ በ30 አለም አቀፍ መድረኮች የሚታይ ትያትር ፕሮዲውስ አድርጓል።

"ወደ ማዶ" የተሰኘው እና ኮሜዲ ዘውግ ያለው ትያትር በትወና ብቃቷ ከፍተኛ የተመልካች ፍቅርና አድናቆት ያላት ሃረገወይን አሰፋን ጨምሮ ሸዋፈራው ደሳለኝ እና የኋላእሸት ዘሪሁን ይተውኑበታል።

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተደርሶ በሴም አማኑኤል የተዘጋጀው "ወደ ማዶ" ትያትር ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሳ የሚሄስ፤ ሲሆን በህወታችን የሚገጥሙን ችግሮች ለማውጣት የሚደረግን ትንቅንቅ የሚያሳይ ሲሆን ከፍ ያለ ዝግጅትም የተደረገበት ነው።

ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ አህጉራት በሚገኙ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ30 በላይ መድረኮች ይታያል።

በተጨማሪም እስካሁን ባልተለመደ መልኩ ትያትሩ በሚታይባቸው ሀገራትና መድረኮች ከትያትሩ ጎን ለጎን ለ"የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል" የገቢ ማሰባሰቢያ ይካሄዳል።
ይህንንም በጎ አላማ ለማሳካት ከማዕከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል።

የትያትሩ ይፋዊ የመክፈቻ መርሃ ግብር ታላላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የጥበብ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በነሐሴ ወር በአፍሪካ የተለያዩ ሃገራት ይደረጋል።
ትያትሩን ፕሮዲውስ ያደረገው ዋካ ፕሮሞሽንና ኤቨንት በኪነ ጥበቡ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የረጅም ጊዜ ልምድ የካበተ ሲሆን ትያትርና ፊልሞችን ጨምሮ የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል።
ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ የስዕል አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል። በተጨማሪ በናይጄሪያ አቡጃ እና በጣሊያን (ሮም) ከተሞች የስዕል አውደ ርዕይ ከሙዚቃ ጋር የቀረበበትን ዝግጅት ሲያካሂድ፤ በፈረንጆቹ 2023 ደግሞ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ግሎባል ትሬድ ኔትወርክ ጋር በጋራ በመሆን በቤልቪው ሆቴል ትሬድ ሰሚት አካሂዷል።

ዋካ ፕሮሞሽንና ኤቨንት "ጥቅለ ኪነ ጥበባት" በሚል በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር የኪነ ጥበብ ስራዎችን አቅርቧል።

በተለያዩ የክልል ከተሞች በሚገኙ ቴአትር እና ሲኒማ ቤቶች የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎችን ከመከወን ባለፈ ለኩላሊት ህመምተኞች የገቢ ማሰባሰቢያ በጎ አድራጎት ስራንም ሰርቷል።

የኢትዮጵያ ልጆችየኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ ተመረቀየኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ መተግበርያ ይፋ ተደረገ።የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዠን ቻናል በመጀመር ፈርቀዳ...
25/07/2025

የኢትዮጵያ ልጆች

የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ ተመረቀ

የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ መተግበርያ ይፋ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዠን ቻናል በመጀመር ፈርቀዳጅ የሆነና በተለይም በልጆችና ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት በማግኘት በአወንታዊ የትውልድ ግንባታ ላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው ይህንን መተግበርያ ይፋ ያደረገው።

ተቋሙ አላማና ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት በማሰብ መተግበርያውን ማበልጸጉን ይፋ አድርጓል።

በባለፉት አስርት አመታት በልጆች ዙርያ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ የቆየው ተቋሙ በባለፉት ሰባት አመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን የልጆች ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ያስመረቀው ይህ መተግበርያ በውስጡ 10 የሚሆኑ ይዘቶችን ማካተቱን ነው የተገለጸው።

መተግበርያው ያበለጸገው መሁቡብ ቴክኖሎጂስ መተግበርያው ለልጆች አመቺ የሆነና አጠቃቀም ተብሎ ቀለል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ስራ አስኪያጅ ህብስት አሰፋ እንደተናገሩት በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ተሰልፈው ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይግባና ዛሬ ለዚህ በቅተናል ብለዋል።

ተቋማችን እዚህ ለመድረሱ ሚስጥር የልጆቻችን ወላጆች ናቸው ያሉት ስራ አስኪያጇ ስላደረጋችሁት ሁሉ ነገር እናመሰግናለን ብለዋል።
Sisay guzay

በአንድ ወቅት ነፃ ትግል ላይ ''የምር ትፋለማላችሁ ወይ'' ተብሎ ተጠየቅ ። ምላሹ ማወቅ የሚፈልግ ሪንግ ውስጥ ይግባና ይየው ነበር ።ዘነኛው የሬስትሊንግ ተፋላሚ ሀልክ ሆጋን ትላንት በ71 ...
25/07/2025

በአንድ ወቅት ነፃ ትግል ላይ ''የምር ትፋለማላችሁ ወይ'' ተብሎ ተጠየቅ ። ምላሹ ማወቅ የሚፈልግ ሪንግ ውስጥ ይግባና ይየው ነበር ።

ዘነኛው የሬስትሊንግ ተፋላሚ ሀልክ ሆጋን ትላንት በ71 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/HuluAddi1/3285?single

እርምጃ እየተወሰደ ነው !በሀዋሳ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአልን ምክንያት በማድረግ  በመኝታ አገልግሎት ላይ የተጋነነ ዋጋ የጨመሩት ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ ።ይህንን ትላ...
24/07/2025

እርምጃ እየተወሰደ ነው !

በሀዋሳ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአልን ምክንያት በማድረግ በመኝታ አገልግሎት ላይ የተጋነነ ዋጋ የጨመሩት ላይ እርምጃ መወሰድ ተጀመረ ።
ይህንን ትላንት ይፋ ያደረገው የሶከር ኢትዮጵያ ባልደረባ ቴዎድሮስ ታከለ ማስፈራሪያ ደርሶበት እንደነበር በገፁ አጋርቷል ።

ኔታኒያሁ ደምአፋሳሹን ካርታ አወጡ! የእስራኤል ጎረቤቶች ሊዋጡ ነው
24/07/2025

ኔታኒያሁ ደምአፋሳሹን ካርታ አወጡ! የእስራኤል ጎረቤቶች ሊዋጡ ነው



ኔታኒያሁ ደምአፋሳሹን ካርታ አወጡ! የእስራኤል ጎረቤቶች ሊዋጡ ነው #...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና አዲስ ስታንዳርድ ሌሎችም ገፃች  ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ ሰርተውብኛል ሲል ሰፋ ያለ መግለጫ አውጥቷል ። በትዕግሥት አንብቡት ። እኛም መንግ...
24/07/2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና አዲስ ስታንዳርድ ሌሎችም ገፃች ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ ሰርተውብኛል ሲል ሰፋ ያለ መግለጫ አውጥቷል ። በትዕግሥት አንብቡት ። እኛም መንግስታዊ ሚዲያ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በምንጭነት ተጠቅመን ከትላንት በስትያ መረጃውን አጋርተናችሁ ነበር ።
↘️
ክቡራን ደንበኞቻችን እና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፡-
==========================
ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ ስታንዳርድ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የተባሉና ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች በባንካችን ላይ ተቃጥቶ ከነበረው ብር 7.735 ቢሊየን ገንዘብ ከባንኩ የውስጥ ሂሳቦች ያለሕጋዊ ምክንያትና ሥልጣን በባንካችን በሚገኙ 10 የሌሎች ግለሰቦች ሂሳብ በማዛወር ገንዘቡን ለማይገባው ሰው ጥቅም ወይም ለራሳቸው ለተጠርጣሪዎች ለማዋል የማመቻቸት ተግባርን ባንኩ ባለው ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ደርሶበት ምንም አይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ገንዘቦቹን ከተላለፉባቸው ሂሳቦች ወደ ትክክለኛዎቹ የውስጥ ሂሳቦቹ ተመላሽ አድርጓል። ባንካችንም ለሚመለከተው የሕግ አካል ወዲያውኑ የወንጀል ተግባሩን ጥቆማ በማቅረቡ ምርመራዎች ሲካሄዱና ማስረጃዎች ሲሰባሰቡ ቆይቶ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ለራስ ወይም ለሌላ ሰው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት አስቦ ስልጣንን አላግባብ የመገልግል ከባድ የሙስና ወንጀል በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ወንጀል ተሳታፊነት በፌደራል ዓቃቢ ሕግ የሙስና ወንጀል ዳይሬክቶሬት በኩል በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ የወንጀል ክስ ተመስርቷል።
በሌላ በኩል ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በማለት ባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ፣ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ እና ባንካችንም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ የሐሰት መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ባንካችን ትክክለኛውን እውነታ በመግለፅ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፆቹ ባስተላለፈው መልዕክት:-
➢ ባንካችን ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በጠንካራው የውስጥ ቁጥጥር ስርዓታችን አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ስለደረሰበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ (ሳይመዘበር) ሙከራው ወዲያውኑ እንዲከሽፍ መደረጉን፣
➢ ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አለመሆኑን፣
➢ ባንካችን ሙከራ የተደረገበትን ገንዘብ ባለው ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት አማካኝነት ከጥቃት ከተከላከለ በኋላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉና የምርመራ ስራውም ተጠናክሮ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፖሊስ በኩል ተገቢው ምርመራ ተደርጎ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ በፌዴራል ዓቃቤ ህግ በኩል ክስ መመስረቱን ተከትሎም ገንዘቡ “በተጠርጣሪዎቹ ወጪ ተደርጎ እንደተወሰደ” በማስመሰል፤ “ባንካችን አጭበርብረውኛል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተ” እንዲሁም “ተመዘበረ የተባለው ገንዘብ ባንካችን ከፖሊስ ጋር በመተባበር ማሳገዱን” በመጥቀስ ሀሰተኛ መረጃዎች በጥቂት የማህበራዊ ሚድያዎች መሰራጨቱንና የዚህን መረጃ ትክክለኛነት ሳያጣሩ ሌሎች የተወሰኑ ሚዲያዎችም ይህንኑ ሀሰተኛ መረጃ ደግመው እያሰራጩ የሚገኙ እንዳሉም ተገንዝበናል።
ቀደም ብለንም እንዳሳወቅነው ባንካችን እንደማንኛውም የፋይናንስ ተቋም በተለይም እንደ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋምነቱ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አስበው ለሚንቀሳቀሱ አካላት ኢላማ መሆኑ እሙን ቢሆንም እንዲህ አይነቱን ሕገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓትና የዘመነ ሲስተም ያለው ለመሆኑ ይህ የሙከራ ድርጊት መክሸፉና ተጠርጣሪዎች ላይም ምርመራ ተጣርቶ የወንጀል ክስ መመስረቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በመሆኑም የባንካችንን መልካም ስምና ዝና ለማጠልሸትና ሀሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት ሆን ብለው የተዛባና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ላይ በአፋጣኝ ተገቢውን የእርምት ማስተባበያ ካልሰጡ ባንካችን ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን እያሳወቅን ክቡራን ደንበኞቻችንም ባንካችንን የሚመለከቱ መረጃዎችን ከታአማኒ የመረጃ ምንጮችና ከባንካችን ይፋዊ የመረጃ ምንጮች ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የመረጃዎችን ትክክለኛነታቸውን ሳያጣሩ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዳይቀበሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

አይዛክ ወደ ሲንጋፖር አልተጓዘም !አሌክሳንደር ኢሳክ የቅድመ ውድድር ዘመን ጉብኝት ለማድረግ ከኒውካስል ጋር ወደ ሲንጋፖር አልተጓዙም።በሊቨርፑል በጥብቅ የሚፈለገው ተጨዋቹ 125 ሚሊዮይ ዩሮ...
24/07/2025

አይዛክ ወደ ሲንጋፖር አልተጓዘም !

አሌክሳንደር ኢሳክ የቅድመ ውድድር ዘመን ጉብኝት ለማድረግ ከኒውካስል ጋር ወደ ሲንጋፖር አልተጓዙም።

በሊቨርፑል በጥብቅ የሚፈለገው ተጨዋቹ 125 ሚሊዮይ ዩሮ መሸጫ ዋጋው እንደሆነ ይነገራል ።
ኒውካስትል ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ወደ ሲንጋፖር ያላመራው በደረሰበት ቀላል የጭን ጉዳት ነው ። [ሜይል ስፖርት]
ለተጨማሪ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/HuluAddi1/3269

Address


Telephone

+251929141139

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hulu Addis on Bisrat FM 101.1 ሁሉ አዲስ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hulu Addis on Bisrat FM 101.1 ሁሉ አዲስ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share