
11/10/2023
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት
ETHIOPIAN VISIONARY CHURCHES FELLOWSHIP
GAMTAA WALDOOLE KIRISTIIYAANA VIIZHINARII ITIYOOPHIYAA
***
መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም፤ ቄስ አለሙ ሼጣ በስጋ ሞት ከዚህ ምድር መለየታቸውን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ፕሬዚደንት የተላለፈ የሃዘን መግለጫ መልዕክት፤
ቄስ አለሙ ሼጣ በአመራር ዘመናቸው፤ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ የመጀመሪያው የደቡብ ሲኖዶስ መሪና በዋናው ጽ/ቤት በቲዎሎጂና ሚሽንና መምሪያ ዳይሬክተር በመሆን፣ እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ጠ/ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል። በመካነ የሱስ ሴሚነሪ መምህርነት ዘመናቸው ብዙ አገልጋዮችን ያፈሩ በተማሪዎቻቸው የሚወደዱ ሰው ነበሩ።
ቄስ አለሙ ሼጣ በምድር ቆይታቸው ከሃምሳ ዓመታት በላይ በደማቅ አመራርና አገልግሎት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሲያገግሉ ቆይተው፣ በትጋት ወዳገለገሉት ወደሚናፍቁት ጌታ በስጋ ተለይተውን በመሄዳቸውን የተሰማንን ታላቅ የሐዘን ስሜት ለመግለጽ እንወዳለን።
ሐዋርያ ዘላለም ጌታቸው (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ፕሬዚደንት
መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።