EthioXpress

EthioXpress We love to learn more and more about the new technologies of this modern world.

19/09/2025

゚viralシfypシ゚

01/09/2025

100%

25/08/2025

የአፍሪካ ሀገራት የመንግስት ተቀጣሪዎች አማካይ ደመውዝ ንጽጽር።
**********************************
Countries Salary (USD) Salary(ETB)

1 South Africa 3,400$ 421,600 birr

2 Moroco 3,300$ 409,200 birr

3 Botswana 3,000$ 372,000 birr

4 Kenya 3,000$ 372,000 birr

5 Namibia 2,700 334,800 birr

6 Seychelles 2,600$ 322,400 birr

7 Libya 2,100 260,400 birr

8 Ethipia 85$ 10,540 birr

ሼር
ሼር

25/08/2025

22/08/2025

ርሑስ ባዓል ኣሸንዳ!

Ethiopia Records World’s Sharpest Tax-to-GDP Ratio Decline in a DecadeEthiopia has suffered the sharpest and sustained c...
22/08/2025

Ethiopia Records World’s Sharpest Tax-to-GDP Ratio Decline in a Decade
Ethiopia has suffered the sharpest and sustained crumble in tax-to-GDP ratio recorded anywhere in the world over the past decade, a new government-backed study reveals.

The joint report by the Ministry of Finance and the Institute for Fiscal Studies (IFS) revealed on August 15, 2025 shows that the country’s tax-to-GDP ratio has plunged from 12.4 percent in 2014 to just 7.5 percent a decade later.

“No other country in the world has experienced such a large relative decline in its tax-to-GDP ratio over this period,” reads the report.
https://www.thereporterethiopia.com/46481/

የሻይ ቅጠል ተክል በኢትዮጵያ ...በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የሻይ ቅጠልን ወደ እንግሊዝ፣ ሕንድ እና ጀርመን በመላክ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎቷን እየደጎመች ነው። ለመሆኑ የሻይ ቅጠል ተክል በኢትዮ...
20/08/2025

የሻይ ቅጠል ተክል በኢትዮጵያ ...

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የሻይ ቅጠልን ወደ እንግሊዝ፣ ሕንድ እና ጀርመን በመላክ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎቷን እየደጎመች ነው።

ለመሆኑ የሻይ ቅጠል ተክል በኢትዮጵያ ምድር መቼ ነው መብቀል የጀመረው?

የሻይ ቅጠል ተክል (Assam tea type) ወደ ኢትየጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው በፈረንጆቹ 1927 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ በነበሩት ጆርጅ ሆላንድ አማካኝነት እንደሆነ ይነገራል።

ጆርጅ ሆላንድ ከውጭ ያመጡትን የሻይ ቅጠል ተክል ዘር በቦንጋ ከተማ ቶንጎላ አካባቢ ለሚኖሩ አርሶ አደሮች እንዲያለሙት ማሠራጨታቸውን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ ይገልጻሉ።

በተጨማሪም በፈረንጆቹ 1928 የእንግሊዝ ቆንስል የነበሩት አብዱል መጅድ ከሕንድና ኬንያ የሻይ ቅጠል ተክል ፍሬዎችን በማስመጣት በኢሉአባቦር ዞን አሌ ወረዳ ጉመሮ አካባቢ ማሠራጨታቸውን ያወሳሉ።

እንዲሁም በኢትየጵያ ከ1950 እስከ 1960 ዓ.ም አማራጭ የግብርና ልማት ማስፋፋት ሥራዎች አካል በመሆን የሻይ ቅጠል ልማት እና ኢንቨስትመንት ሥራ መጀመሩን ይገልጻሉ።

ልማቱ በተጠናከረ መልኩ የተጀመረው ሁለቱ ሰፋፊ የሻይ ቅጠል ተክል እርሻዎች በሚገኙባቸው በውሽውሽ እና ጉመሮ አካባቢዎች ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በቡናና ሻይ ልማት ሚኒስቴር እየተመራ በተጠናከረ መልኩ ሲሠራበት መቆየቱንም ያስታውሳሉ።

ከመንግሥት ለውጥ በኋላ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመፍረሱ የሻይ ልማት ድርጅቶቹ ወደ ግል ይዞታ (ኢትዮ-አግሪሴፍት አ.ማ) ተዛውረው እየተመሩ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ጋምቤላ ክልሎች በአራት የሻይ ልማት ድርጅቶች (ውሽውሽ፣ ጉመሮ፣ ኢስት አፍሪካ (የጨዋቃ ኡቶ) እና ቨርዳንታ) እንዲሁም በአነስተኛ አርሶ አደሮች በአውት ግሮዎርስ ትስስር እና በኩታ ገጠም እየለማ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በዚህም መሠረት በእርሻ ልማቶች 3 ሺህ 829 ሔክታር እና በአነስተኛ አርሶ አደሮች 1 ሺህ 107 ሔክታር በአጠቃላይ 4 ሺህ 936 ሔክታር ላይ የሻይ ቅጠል ተክል ማልማት ተችሏል ብለዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የሻይ ልማት ኢኒሼቲቭ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በኢሉአባቦር፣ ቡኖ በደሌና ጅማ ዞን በልዩ ትኩረት ልማቱ እየሰፋ መሆኑንም አመላክተዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ከ3 ሺህ 729 ሔክታር ላይ 9 ነጥብ 8 ሺህ ሜትሪክ ቶን ደረቅ የሻይ ቅጠል ማምረት መቻሉንም አንስተዋል።

እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻ፤ በኢትዮጵያ በሰፋፊ እርሻዎች ውስጥ አምስት የሻይ ቅጠል ምርት ማዘጋጃ ፋብሪካዎች አሉ።

በሻይ ማዋሀድ/እሴት በመጨመር ላይ ተሰማርተው ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ ልዩ ምርቶችን እያቀረቡ ያሉ ኩባንያዎችም፤ ኢትዮ አግሪ ሴፍት (ውሽውሽና ጉመሮ ሻይ ልማት)፣ ኢስት አፍሪካ አግሪ ቢዝነስ፣ ሄሪቴጅ ሻይ ኢትዮጵያ እና መታድ የግብርና ልማት ናቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ለሻይ ቅጠል ልማት ተስማሚና ምቹ የሆነ 150 ሺህ ሔክታር መሬት መኖሩንም ለኢዜአ ተናግረዋል።

የሻይ ቅጠል ተክል አንድ ጊዜ ከተተከለ ለ30 እና 40 ዓመታት ምርቱ የሚቆይና በየ15 ቀኑ ምርቱን በመልቀም ገቢ ማግኘት የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል።

የሻይ ልማት ዘርፍ ለ80 ሺህ ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ያነሳሉ።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 882 ነጥብ 45 ቶን የሻይ ቅጠል ምርት ወደ እንግሊዝ፣ ሕንድ እና ጀርመን በመላክ 1 ነጥብ 61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን አረጋግጠዋል።

በ2018 የበጀት ዓመት ደግሞ 898 ቶን በመላክ 1 ነጥብ 72 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ነው የጠቆሙት።

#ኢዜአ

Address

Ethiopia
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioXpress posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share