
26/12/2024
ታህሳስ 17/2017
👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን 🙏🙏🙏
👉የትውልድ ሀገሩ #ኢየሩሳሌም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች ዘመኑም የመጀመሪያው ምእተ ዓመት ነው
👉እንግዲህ በዘመነ ሐዋሪያት የማዕዱን እና የውስጡን አገልግሎት እንዲያስተናብሩ መንፈስ እና ጥበብ የሞላባቸው ሰባት ሰዎች ተመርጠው በሐዋሪያት አንብሮተ እድ ሆነው ከተሾሙት ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስቲያኖች አብነት የሆነው ሰማዕቱ ይገኝበታል እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም #አክሊል ማለት ነው
👉መፅሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል ምንም እንኳን ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው
👉ወላጆቹ ይህንን ስም የሰጡት ተብሎ የሚታመነዉ ወላጆቹ በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለ ነበር የግሪክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል
👉 በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር በእርሱም ታላላቅ ተአምራት ይፈፀሙ ነበር
👉ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ #እስጢፋኖስ ላይ በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም
👉ስለዚህም #እግዚአብሔርን ሙሴን ሲሳደብ ሰምተነዋል ሙሴ የሠራልንን ሥርዐት ይለውጣል በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን ቃል ይናገራል ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ ብሎአል እያለ ያስተምራል እያሉ ሕዝቡን ሽማግሌዎችንና ፀሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት
👉ቅዱስ #እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ #መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው
👉 #ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው #ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ ይህንን ራእይ የክርስቶስን ትንሣኤን ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ
👉እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት ነገር ግን ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ እንደ መምህሩ ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለ ክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ሆኖአል
👉በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ የነበረ ብላቴና ነበር
👉ነገር ግን ሐዋርያ ከሆነ በኋላ የሰማእቱ #የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቆአቸዋል ። ሰማያዊ ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት ና ምላጁ አይለየን 🙏🙏