Ethio Lehulu

Ethio Lehulu รεε ИΘ ξปไ£
HξAЯ ИΘ ξปไ£
∫℘ξAK ИΘ ξปไ£ ረጅም እድሜ ለኢትዮጵያ����

16/12/2025

ኢትዮ ለሁሉ ትሁን ብለናል፨🌟🌟☀️🧐😏🤪😘🥰

16/12/2025

➡️🤲🤲🏾🧎🧎‍♀ምንጮች እንዳሉት ወንድማችን ማስተር አብነት ከታመም ትንሽ ቆይቷል ነገር ግን ህመሙን ደብቆ በጎ ስራውን እየሰራ ነበር

➡️🤲🤲🏾🧎🧎‍♀አሁን ግን ይህን በጎ ስራውን ለጊዜው አቁሞ በአፋጣኛ ህክምና እንዲጀምር ጏደኞቹ ቤተሰቦቹ ና የቅርብ ሰዎች ማስተር አብነትን መገፋፋት አለባቸው ባይ ነን

Addis media Network ይሄ ዘገባ ሰርቷል :👇

ማስተር አብነት ከበደ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን እንደሚቻል ካስተማሩ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። በሚሠራው የበጎ አድራጎት ሥራ የተቸገሩ ሰዎችን ሕይወት መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ሰው ነው።

ከሚያለቅሱ እናቶች ጋር ሲያለቅስ፣ ከታማሚዎች ጋር አብሮ ሲታመም፣ በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ የሚታወቀው ማስተር አብነት ማኅበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ እርዳታዎችን በማሰባሰብና በመለገስ የብዙዎችን እንባ አብሷል።

አሁን ግን ማስተር አብነት ራሱ በከባድ ሕመም ላይ መውደቁን ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበረው ቆይታ ይፋ አድርጓል።

“ችግረኞችን ለመርዳት ገንዘብ እያሰባሰብኩ ዝም ብዬ መቀመጥ አልችልም” የሚለው ማስተር አብነት የሕመሙን ምንነት ለይቶ ባያስቀምጥም ስለመታመሙ ለማንም መናገር እንደማይፈልግ ገልጿል።

ማስተር አብነት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ 5 ሰዎችን ለሕክምና ወደ ሕንድ ሀገር ሔደው እንዲመለሱ ማድረግ ችሏል።

“እኔ አሁን ባልተመረመረ በሽታ ውስጥ ነው ያለሁት፣ የሚያስጨንቀኝ ይሄ ሕመም በምርመራ አይገኝም፣ ራሴን እያጣሁ፣ በሥነ-ልቦናም እየተጎዳሁ ነው” ብሏል።

ማስተር አብነት ማንንም ሰው ማስጨነቅ ስለማይፈልግ ብቻ ስለሕመሙ ጉዳይ ባይገልጽም የለበሰው ልብስ የሸፈነውና በህክምና ይህ ነው የማይባል ሕመም እያስጨነቀው ይገኛል።

አሁን ላይ ግን መታመሙ ከእሱ አልፎ በሌሎች ዘንድ እየታወቀ በመምጣቱን ብዙዎች እየጠየቁት እንደሆነ ተናግሯል።

የእናቶችና የአባቶች እንባ ሲታበስ ማየት፣ ወንድሜ አንገቱን ቀና አድርጎ ሲሄድ ማየት፣ የኩላሊት ሕመም የነበረባት እህቴ ተሽሏት ፈገግታዋ ሲመለስ ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም። ያንን አይቼ እጽናናለሁ” ብሏል።

ማስተር አብነት “የውስጤን በሽታ ፈጣሪ እንደሚያድነኝ አምናለሁ” በማለት ከዚህ ውጪ ሰው ማስጨነቅ ስለማልፈልግ የኢትዮጵያ ሕዝብ፥ አባቶች እና እናቶች እንዲጸልዩለት ጠይቋል

ከጊዜ በኋላ የሕይወቱን ትርጉም በበጎ አድራጎት ሥራ ውስጥ ያገኘው ማስተር አብነት ዛሬ ላይ ለተቸገሩ ድምጽ እና የተስፋ ድልድይ በመሆን በፌስቡክ ላይ ከ1.7 ሚሊዮን፥ በቲክቶክ ደግሞ ከ4.8 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ማፍራት የቻለ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን ችሏል።

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክም ለማስተር አብነት ሙሉ ጤንነቱ እንዲመለስለትና ወደሚወደውና ለብዙዎች ሕይወት ተስፋ ወደሆነበት የበጎ አድራጎት ሥራው እንዲመለስ ይመኛል።

Via AMN

🙏🏿🙏🏿

💔💔 ገነቴዋ  💔😭💔💔ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አላህ ይዘንላቸው አላህ በራህመቱ ጀነተል ፊርደውስን ይመንዳቸው 🌴🌴🌴የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር...
20/10/2025

💔💔 ገነቴዋ 💔
😭💔💔ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አላህ ይዘንላቸው
አላህ በራህመቱ ጀነተል ፊርደውስን ይመንዳቸው

🌴🌴🌴የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ🌴🌴🌴

ዋርካ ሳሉ እንደ ችፍርግ መሬት ያዙ። ክቡድ ሆነው እንደ ማንም ለመኖር "ይከብደኛል" አላሉም። ደግሞ የአንዱ እምነት መሪ ሆነው ሁሉን ለመሰብሰብ አልጠበቡም። ልባቸው ሰፊ፣ እውቀታቸው ጥልቅ፣ ሞገሳቸው ልብ አርድ።

💔ኢትዮጵያ በእርግጥም አባት አጣች። አባታችን የምንለው የወል ምልክት ስናጣ ተከሰቱ። ሳንጠግባቸው ዘወር አሉ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ትሁቱ ሰው።

💔አባት ተርበን ነበር። በዚያ የወል ምልክት ባጣንበት ምድረ በዳ ዘመን ተሰጡን። ለዚያ ነው ሀዘናችን እንጂ አሳዝነውንስ አይደለም። ሀዘናችን መነሾው ፍቅራችን ነው። አባት ማጣት ይጎዳል፤ ሀገር አባት አጣ።

💔መተናነስ የሞላበት ዕውቀት የተሞሉ፤ መወደድ ከመደመጥ የተሰጣቸው። በሀገራቸው የእኛ ተብለው ከሚቆጠሩ አንዱ፤ እሳቸው አዎ እሳቸው አባታችን፤ ይህ ሀዘን እንደ ህዝብ ብሔራዊ ሀዘናችን ነው።

💔ፊታቸው ሰላም የሚሰጥ፣ ሳቃቸው የሽሙጥ ሳይሆን የእረፍት፤ እንዲሁ የሚታመኑ፤ ቅቡልነትን የተሞላ እሳቸው አዎ እሳቸው ነገ "አይተናቸው ነበር" ለምንል የሚያስጠረጥሩ። ልጆቻችን "በዚያን ጊዜ እንዴት እንዲህ ያለ ሰው ታየ" ይሉናል።

💔እንኳን በእምነት ልዩነት በአንድ ቤተ እምነት የወል አባት ባጣንበት ጨለማ ውስጥ የሁላችን ሆነው የበሩ ኮከብ። እንደ ፈነጠቁ ያልደበዘዙ፣ እንደ ደመቁ ያደመቁን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ።

💔ኢትዮጵያ ታላቁን አንድ የእምነት መሪ ደግሞ የጋራ አባት ደግሞ የዘመን ምልክት አጣች። ሀገሬ ሆይ እንዲህ ያሉ ምልክቶችን አያሳጣሽ።

🙏አላህ መልካም አበርክቷቸውን ይቀበላቸው፣ ምህረቱን ይለግሳቸው፣ በጀነተል ፊርዶስ ይመንዳቸው

የሀገሬው ዋርካ ወደቁ
ለምለም ስንቆች ደረቁ።💔

ኢትዮጵያ በእርግጥም አባት አጣች። አባታችን የምንለው የወል ምልክት ስናጣ ተከሰቱ። ሳንጠግባቸው ዘወር አሉ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ትሁቱ ሰው።
💔 የሀዘን፣ የትካዜ እና የጥበብ ቃል!

እኛ ያልተረዳነው የአባት ለቅሶ... ዛሬ እሳቸው ሲያልፉ መልዕክቱ ይብሱን ይጎረጉረናል!

💔የክብር ዶክተርና ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በሕይወት ዘመናቸው ስለ ሀገራቸውና ስለ ሕዝባቸው አዝነው የተናገሩት ይህ ልብ የሚሰብር ቃል ዛሬም የሁላችንም ሰንሰለት ሆኖ ይቆማል፦

"ለሊት እንቅልፍ የለኝም!"

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ለሊት እንቅልፍ የለኝም ፥ ለ 2 ሠዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ።

ለምንደነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው!?

ለምንስ ነው የምንጫረሰው!?
በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል!"

ታላቁ የአባት ጥሪ፦ "ሰውነት ይቀድማል!"
ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለዘመናት ዘር እና ሃይማኖት ቀድሞ ሰውን የገፋ ሁሉ የሚሰማው ጥብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፦

❣️❣️ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል!
ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል!
ከዘር ሰውነት ይቅደም! ❣️❣️

አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል:: ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁት በማለት አዟል››

ዛሬ እሳቸው በሞት ሲለዩን፣
ይህንን የእንባ ቃል ልብ ብለን እንስማ!

ለእኚህ ታላቅ አባት ከሁሉ በላይ የሚከብር መታሰቢያ የምንሰጠው ለቅሶአቸውን በስራ ስንተረጉመው እና የጠየቁንን ሰውነት ስናስቀድም

⭕️የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ያቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ የግብፅ ፌዴሬሽን ምላሽ ሰጠ!➖️ የግብፅ ሜዲያዎች የኢትዮጵያን ክስ በሰፊው እየዘገቡት ይገኛል!የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ...
08/09/2025

⭕️የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ያቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ የግብፅ ፌዴሬሽን ምላሽ ሰጠ!

➖️ የግብፅ ሜዲያዎች የኢትዮጵያን ክስ በሰፊው እየዘገቡት ይገኛል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ ዕለት ከግብጽ ጋር ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ የግብጽ ደጋፊዎች የፈፀሙትን ያልተገባ ተግባር ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ይፋዊ ቅሬታውን አቅርቧል።

ፌዴሬሽኑ ለፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በላከው ደብዳቤ፣ ተፈፅመዋል ያላቸው ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።

የመጀመርያው ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅት የግብፅ ደጋፊዎች ክብረ ነክ በሆነ መልኩ ጩህት እና ረብሻ ሲያሰሙ እንደነበር አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም ደጋፊዎች በፊፋ በፍጹም ክልክል የሆነውን የሌዘር ጠቋሚ በማንጸባረቅ ተጫዋቾች ላይ በተለይ ደግሞ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ፍጹም ቅጣት ምቶቹ ሲመቱ ትኩረቱን እንዲያጣ አድርገዋል በማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

የተፈጸሙት ሁለቱም ጉዳዮች በፊፋ የስነ ምግባር ደንብ መሰረት በአባል ሀገራቱ ፈጽሞ የተከለከሉ በመሆናቸው ክስተቶች ላይ ግልጽ ምርመራ እንዲያደርግ እና ፊፋ ባስቀመጣቸው የዲሲፕሊን ደንቦች መሠረት የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደጋፊዎቹ ላሳዩት ያልተገባ ባህሪ ተጠያቂ እንዲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋ ጠይቋል።

ይህን ተከትሎ የግብፅ ሜዲያዎች የተለያዩ መረጃዉን በሰፊው መዘገብ ይዘዋል::
ባለፈው አርብ በ2026 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉትን ጨዋታ ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር በግብፅ ላይ ላቀረበው ቅሬታ የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙስጠፋ አዛም ምላሽ ሰጥተዋል።
ሙስጠፋ አዛም ለአል-መስሪ አል ዩም በሰጡት መግለጫ "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የግብፅ ደጋፊዎች በተለይ የፍፁም ቅጣት ምቶች ላይ የሌዘር ጠቋሚዎችን በስፋት መጠቀማቸውን እና የብሄራዊ መዝሙር ሲጫወቱ ደጋፊዎቹ ይሰሙት የነበረውን የጥላቻ ጩኸት ደርሶብኛል ብሏል አያይዘውም ማንም ሰው ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጥ ልንከለክለው አንችልም ነገርግን የዕለቱ ጨዋታ የጨዋታው ታዛቢ ዘገባ አለ ያንን ነው መታየት ያለበት " ብሏል።

አያይዘውም "በኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ከፊፋ የተሰጠ መግለጫም ሆነ ምላሽ ከደረሰን ይፋዊ ምላሽ እንሰጣለን፤ ከዚህ ውጪ ግን ማድረግ አያስፈልገንም" ብለዋል።

ለ2026 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ በሰባተኛው ዙር የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ኢትዮጵያን 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል::

24/06/2025
24/06/2025
ethio  ኢትዮን ለወደዱ ሁሉ ክብር
07/02/2025

ethio
ኢትዮን ለወደዱ ሁሉ ክብር

ሊጀመር ደቂቃዎች ቀርተዋል ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ የወንዶች የ5000 ሜትር ፍጻሜ ይካሄዳል። በውድድሩ አትሌት ሐጎስ ገ...
10/08/2024

ሊጀመር ደቂቃዎች ቀርተዋል ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ

ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ የወንዶች የ5000 ሜትር ፍጻሜ ይካሄዳል። በውድድሩ አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት፣ አትሌት ቢኒያም መሐሪና አትሌት አዲሱ ይሁኔ ይወዳደራሉ።

አትሌት ሐጎስ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በኖርዌይ ኦስሎ በተከናወነው ዳይመንድ ሊግ 12 ደቂቃ ከ36 ደቂቃ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። አትሌቱ የገባበት ጊዜ በርቀቱ የዓመቱ የዓለም ፈጣን ሰዓት ነው።

ሐጎስ በኦሊምፒክ የተሳተፈው እ.አ.አ በ2012 በለንደን በተካሄደው 30ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ነበር። እ.አ.አ በ2016 በሪዮ ዴጄኔሮ በተደረገው 31ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

በኦሊምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎውን የሚያደርገው አትሌት ቢኒያም መሐሪ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተካሄደ ውድድር 12 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ ከ10 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።

ሌላኛው ተወዳዳሪ አዲሱ ይሁኔ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በኖርዌይ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር 12 ደቂቃ ከ49 ሴኮንድ ከ65 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓት ማስመዝገቡ የሚታወስ ነው።

በተያያዘም ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ የ1500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል። አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ይሳተፋሉ።

ጉዳፍ በሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም በቻይና ዢያሜን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር 3 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ከ30 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ የወጣችበት ጊዜ የርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷ ሆኖ ተመዝግቧል። የገባችበት ሰዓት በርቀቱ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ነው።

ጉዳፍ ትናንት በተካሄደው የ10000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ስድስተኛ እንዲሁም በ5000 ሜትር ዘጠነኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

ድርቤ ወልተጂ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአሜሪካ ኢውጅን በተካሄደ ውድድር 3 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ከ75 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዘግባለች።

በፍጻሜው የኢትዮጵያ አትሌቶች ከኬንያውያኑ አትሌቶች ፌዝ ኪፕዬጎንና ሱዛን ሎካዮ ኢጆሬ ጋር የሚያደርጉት ፋክክር የተመልካቾችን ቀልብ ስቧል።

ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ እስካሁን 3 ሜዳሊያዎችን ይዛለች።

ጀምሯል መልካም እድል የፓሪስ 2024  ውድድሮች ዛሬም ይቀጥላሉ።   | ዛሬ የሚደረጉ የኢትዮጵያዊያን አትሌቲክስ ውድድሮች !  የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ሁሉም ወደቀጣዩ ዙር ...
05/08/2024

ጀምሯል መልካም እድል የፓሪስ 2024 ውድድሮች ዛሬም ይቀጥላሉ።

| ዛሬ የሚደረጉ የኢትዮጵያዊያን አትሌቲክስ ውድድሮች !



የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ሁሉም ወደቀጣዩ ዙር አልፈዋል

ተወዳዳሪዎች
አትሌት ጌትነት ዋለ
አትሌት ሳሙኤል ፍሬው
አትሌት ለሜቻ ግርማ

⏰ ማታ 04:10

የሴቶች 5000 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
አትሌት እጅጋየሁ ታዬ
አትሌት መዲና ኢሳ

⏰ ማታ 04:45

የሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች
አትሌት ወርቅነሽ መሰለ
አትሌት ፅጌ ድጉማ

አትሌት ወርቅነሽ መሰለ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን 1:58.06 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ፅጌ ዱጉማ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን 1:57:47 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኛነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ኢትዮጵያ በውድድሩ እስካሁን አንድ የብር ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን ! 🇪🇹
መልካም እድል ለኢትዮጵያችን ! 🇪🇹

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Lehulu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share