Yeha Arts

Yeha Arts የሓ~ በዋናነት በድረ-ገጽ ላይ የተመሰረተ መጽሔትና አገናኝ ሲሆን፣ የተመረጡ መጻሕፍት እና ቴአትሮችንም ወደ ገበያ ያቀርባል።

አበበ ቢቂላ፣በዚያን ቀን!
10/09/2025

አበበ ቢቂላ፣
በዚያን ቀን!

ነፍሱን ይማርልን።
17/08/2025

ነፍሱን ይማርልን።

እኔን ብሎ ደሞ… (እውነተኛ ታሪክ)/\“ፍቅሪ” አለኝ፣ እንዳይነጋ የለም እድሜ ልክ ያከለብኝ ጨለማ አልፎ ረፋዱ ላይ ስልክ በመደወል።“ሙልዬ? የኔ ጌታ! … አለህልኝ ሙሌ? አለህልኝ ወይ?” ...
15/08/2025

እኔን ብሎ ደሞ…
(እውነተኛ ታሪክ)
/\

“ፍቅሪ” አለኝ፣ እንዳይነጋ የለም እድሜ ልክ ያከለብኝ ጨለማ አልፎ ረፋዱ ላይ ስልክ በመደወል።

“ሙልዬ? የኔ ጌታ! … አለህልኝ ሙሌ? አለህልኝ ወይ?” ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ መሬቱን ጨምጭሜ ሳምሁት። ደስታዬ የሚያደርገኝን አሳጣኝ። ዘልዬ ሰማዩን ብስመዉ እንኳን የልቤ መድረሱን እንጃልኝ። ተመስገን! በሕይወት አለ ማለት ነዉ? በአዛኚቱ! እኔማ ስንቱን ነበር ያሰብሁት? በዚያ ላይ ስልኩ ጭምር ዝግ ሆኖብኝ በጭንቀት ልሞት ነበር። ሥራዉም በጸባዩ ብዙ ጊዜ ከብዙ አይነት ሰዎች ጋር ስለሚያዳርሰዉ፣ ክፉ ክፉዉን ብቻ እያሰብሁ እንዲችዉ ስነፈርቅ እና ስንጨዋለል ነዉ ያደርሁት። እንዲያዉ አደርሁ አልሁት እንጂ እንደዋዛ፣ አዳሬስ አዳርም አይደል።

“በደህናህ ነዉ ግን?” አልሁት፣ ወደ ነፍሴ ለመመለስ ዐይኔን ጨፍኜ እየገለጥሁ።

“ምነዉ?”

“እህእ… ምነዉ ትለኛለህ እንዴ ደሞ?”

“ምነዉ ፍቅሪ?”

“ኧረ ሙሌ በማርያም! ጭራሽ መቀለድ ሁሉ ያምርሀል? ይልቅ ንገረኝ፣ ምን ገጥሞህ ነዉ?”

“እራት ምናምን ተባብለን ነበር እንዴ ፍቅሪ?”

“ረስቸዉ ልትለኝ?”

“አይገርምሽም ረስቼዋለሁ”

“ኧረ እንዳታስቀኝ”

“አንቺን ይንሳኝ! ምን አይነት ከንቱ ነኝ በናትሽ? እንዴት ረሳሁት ግን? ለነገሩ ባልረሳዉ ነበር የሚገርመኝ እንዲያዉም። ያዉ ሥራዬን ታዉቂዉ የለ? የትናንትናዉ ደግሞ የተለየ ነበር። ብታይኝ ትንፋሼን እንኳን እንደልቤ የምተነፍስበት ፋታ አልነበረኝም። ያ ከጀርመን እያስመጣሁት ነዉ ያልኩሽ እቃ… ስለሱ አልነገርሁሽም ወይ ፍቅሪ? ነግሬሻለሁ ኧረ።… አዎ፤ እሱ እቃ ሊስተጓጎልብኝ ሲል አይገቡ ገበቼ ነዉ ለትንሽ ያተረፍሁት ብታይ። ደስ አይልም?”

“ተመስገን! እዉነት በደህናህ ነዉ?”

“ኮራሽብኝ ኣ ፍቅሪ?” አለኝ፣ ረዥሙን የእፎይታ ትንፋሼን እየደጋገምሁለት ሳለ። “ምናለ በይኝ ኋላ… ክብረት የሚሏት ነገር መድረሻ ሰማይ ካላት፣ በዚያች ሰማይ ከእኔና ከአንቺ ቀድሞ ማንም አይደርስባትም። እኔና አንቺ ብቻ! ያኔ ነዉ እኛን ማየት። መነኩሴዎች ጭምር የሚቀኑበትን ሠርግ እናሠርግና፣ ሥፍር ቁጥር በሌላቸዉ ልጆች ቤታችንን ሞልተን… ይታይሻል ኣ ኑሯችን?”

“ይሁን”

“‹ይሁን›? ምነዉ ፍቅሪ፣ አላመንሽኝም እንዴ?”

“እህእ… አሁን አለማመንን ምን አመጣዉ እዚህ? አንተን የማምነዉን ያህል የፈጠረኝንስ አምነዋለሁ እንዴ? ተዉ እንደሱ አትጠይቀኝ እንጂ ሙሌ”

የምሬን ነዉ፤ በሰማይ በምድሩ እንደሱ የምተማመንበት የለኝም። በእኔ ቤት ሀይማኖተኛ ነኝ ባይ ነበርሁ። ግን የፈጣሪ ተዓምር የሚባለዉን ሁሉ አሜን አሜን አልለትም። የምጠራጠረዉ ይበዛል። ተዓምር ጠቅሰዉ ‹እልል በሉ› ሲሉ ቄሱ ‹ኧረ አታሞኙን› የምልበት ቀን አለ። ከሙሌ ጋር ግን ይኸዉ ሰባተኛ ዓመታችንን በፍቅር ስንጨልጥ፣ ለአንዳፍታም እንኳን ተጠራጥሬዉ አላዉቅም። የየዋሆች ሁሉ ምሣሌ እንደሆነ አዉቅለታለሁ። እነካዋለሁ ያለዉን ሳይጨብጥ የማይመለስ ቆራጥም ደፋርም መሆኑን አሳይቶኛል። ከተራ ተቀጣሪነት ወጥቶ ለብዙዎች የእንጀራ ቤት የሆነ የራሱን ድርጅት አቋቁሞ እጄን አፌ ላይ አስጭኖኛል። ጓደኞቹ ሁሉ እንዲያልፍላቸዉ ደፋ ቀና ሲል እያየሁት፤ ለፍትሕና ለህሌናዉ ያለዉን ታማኝነት እየነገረኝ ባላምነዉ ነበር የሚደንቀኝ።

“ንገሪኝ፤ ታምኚኛለሽ ኣ?”

“እያወቅኸዉ? በል ደግመህ አትጠይቀኝ”

“እመኚኝ ፍቅሪ። እምነትሽ ነዉ የእኔ ትጥቅ። ደግሞ ያንቺ ነገር፤ አያየኝም ብለሽ እኮ ይኸኔ ቁርስም አልበላሽ ይሆናል። አልበላሽም ኣ?”

“አይ- በልቻለሁ ኧረ” ስል ሸመጠጥሁት፣ ሐሳብ እንዳይገባዉ ብዬ። እዉነተኛ አዳሬን ብነግረዉ በጭንቀት እንዳይሞትብኝ ፈርቼ እንጂ፣ እንኳንስ እህል ወደአፌ የምልበት ወስፋት ይቅርና ለትናንትናዉ እራት በለበስሁት ስስ ቀሚስም የምደርብበት አቅም አልነበረኝም። እሱ ተጠቃብኝ ብዬ በየፖሊስ ጣቢያዉ እና በየሆስፒታሉ ስንከራተት፣ ከአሁን አሁን መርዶ ነጋሪ ደወለልኝ እያልሁ ስልክ ስልኬን እያየሁ… ብቻ ይኼን ለምን ብዬ ለሙሌ እነግረዋለሁ? የኔ ጌታ፤ እሱ ጭንቅ አይችልም። እንዲሳቀቅብኝም ሆነ ጥፋተኝነት እንዲሰማዉ አልፈልግም። በጭራሽ!

የሙሌን ደህና መሆን የምስራቹን ያገኘሁባት ስልኬን ስሜ ቀና ስል፣ ብቸኛዋ ጓደኛዬ ከፊቴ ከች አለች።

“ሙሌ ድረስ! ዳናም የለሽ እንዴ አንቺ? አስደነገጥሽኝ እኮ እናትዬ” አልኋት፣ እንደልማዴ ጨመቅ አድርጌ እያቀፍኋት። አቤት እንዴት እንደምወዳት! እንዲሁ በእቅፏ እንዳለሁ ቀኑ ቢመሽ ሁሉ አልጠግባትም። ከሙሌ አንጻር ምንም ብትሆንም፣ ከራሴ በላይ ስለምወዳት በስህተት እንኳን በስሟ ጠርቻት አላዉቅም። እናትዬ ነዉ የምላት እንደ እናቴ። ዋነኛዋን እናቴን ገና በጨቅላነቴ ቢወስድብኝም እሷን ጓደኛ አድርጎ ስለሰጠኝ፣ ፈጣሪን አምቼ አላማዉም። የምር እንደ እናቴ ነዉ የማያት። ምክንያቱም ከጓደኝነት የትና የት ታልፋለች። በልቤ ያለዉ ሁሉ ይታወቃታል። ለእኔ፤ የእሷም ልብ ወለል ያለ ነዉ። ሲከፋኝም ሆነ ሲደላኝ ማንም ምንም ትንፍሽ ሳይላት ገና ታዉቅልኛለች።

ልዩ ናት።

“ሥራ አልገባሽም እንዴ እናትዬ” አልኋት፣ ሠዓቴን ተመልክቼ።

“የኔ ይቆይና አንቺ ለምን አልገባሽም?”

“እኔማ… እኔ…” ስል ተንተባተብሁ፣ ሳልጠብቃት መምጣቷ ሳያንስ ባልጠበቅሁት ጥያቄ ስላፋጠጠችኝ።

“ቆይ ቆይ… ቆይ እሺ። እንዴት ሆነላችሁ?”

“ምኑ?” አልኋት፣ ምኑን ማለቷ እንደሆነ ባይጠፋኝም። ትናንትና ከሙሌ ጋር የፍቅረኛነታችንን ሰባተኛ ዓመት እናከብራለን ብያት ስለነበር፣ ስለሱ ነበር ጥያቄዋ። እንዲያዉም የጋብቻ ቀናችንን እዚያዉ ቆርጦ እንዲነግረኝ፤ ሙሌን እንድጠይቀዉ ቃል አስገብታኝ ሁሉ ነበር።

“ጭራሽ ሳይመጣ ቀረ አይደል?” ብላ ገላገለችኝ፣ ምን ብዬ እንደምዋሻት ስፍተለተል።

“ቆይ እንዴት አወቅሽ?”

“ሥራ በዝቶብኝ፣ ፋታ አጥቼ፣ የገዛ ትንፋሼ እንኳን ብርቅ ሆኖብኝ… ቅብጥርሴ ወለጥሴ አለሽ?”

“አዎ። ግን እኮ እዉነቱን ነዉ”

“ምንድነዉ እዉነቱን ነዉ ብሎ ጥብቅና ጓደኛዬ?! ጅልነትሽ እኮ ወደር አጣ! አሁን ከየት እየመጣሁ እንደሆነ አዉቀሻል? ከትምህርት ቤት! ልጄን ትምህርት ቤት አድርሼ እየመጣሁ ነዉ። ከኋላሽ ተነስቼ ነዉ እንግዲህ ልብ አድርጊልኝ። አንቺ ከዛሬ ነገ ከሙሌ ጋር ተጋብተን ልጅ ልንወልድ ነዉ ማለት ስትጀምሪ እኮ እኔ ገና ሌላ ታሪክ ዉስጥ ነበርሁ። ከዚያ በኋላ ወንድ ተዋዉቄ፣ አግብቼ ወልጄ፣ አሳድጌ ትምህርት ቤት አስገብቼ እየተመለስሁ ነዉ አሁን። ታዉቂያለሽ በአንቺ ምክር፣ ከምን አይነት ሕይወት ወጥቼ እዚህ እንደደረስሁ። ምናለበት አንቺስ ሰዉ የሚልሽን እህ ብለሽ ብትሰሚ? እድሜ እኮ እንደ ዕለት ጀንበር ነዉ። ተይ ጓደኛዬ፤ ተይ ግን ተይ። ተይ ዐይንሽን ግለጭዉ። ሙሌ ተብየሽን፣ ቀላል ቀላል ጥያቄዎችን እንኳን መጠየቅ ጀምሪ። ግድየለሽም ጠይቂዉ”

በሙሌ ነዉና የመጣችብኝ፣ ድንገት ጉሮሮዬ ላይ ደረሰች። ሰዉ በቅጽበት ክፉና ደግ አብራ የያች፣ ያዉም እንደ እናቴ ነሽ የሚላትን ጓደኛዉን እስከሚያቅለሸልሸዉ ድረስ ይጠላል እንዴ? አስጠላችኝ። ወዲያዉ ነዉ ሽቅብ ያስባለችኝ።

“በይ፣ ሂጅልኝ!” አልኋት፣ እርር ያለ አንጀቴን አበርትቼ። “ከዚህ በላይ ትርፍ ሳንነጋገር ሹልክ ብለሽ ዉጭልኝ በይ!” ብዬ ወደ በሩ አመላከትኋት። አንዲት ተጨማሪ ቃል ሳትተነፍስብኝ፣ ምስስ ብላ ወጣችልኝ።

በሙሌ የተነሳ ያልተቆራረጥሁት የለም። ብቻ እሱ ይኑርልኝ እንጂ፣ ማንም ሊሄድ ማንም ሊመጣ ይችላል ግድ የለኝም፣ እችለዋለሁ። እንኳንስ እንደእናቴ ነሽ የምላት ጓደኛዬ ትቅርና፣ ራሷ እናቴ እንኳን ከሞት ተነስታ ሙሌ እንዲህ ነዉ ብትለኝ በጭራሽ የምሰማት አይመስለኝም። ስለሙሌ መልካምነት ብቻ ነዉ መስማት የምፈልገዉ። አልባሌ ሰዎች ሳይቀር እየመጡ ‹የሰዉ ፍጹም የለዉም› ሲሉ ያሳዝኑኛል። ወይ ሙሌን አለማወቅ!

አንድ ቀን፣ ግሩም የተባለ የሙሌ ጓደኛ ‹ቡና ልጋብዝሽ› ብሎ ቀጠረኝ። ሙሌ፤ ሥፍር ቁጥር የሌላቸዉ ጓደኞች እንዳሉት ባዉቅም፣ ከአንዳቸዉም ጋር ቅርርብ የለኝም። ግሩምም ከእነሱ አንዱ ስለሆነ፣ መለሎ ይሁን ችፍርግ በአካል አላዉቀዉም። እንዲያዉም ከመሬት ተነስቶ ‹ሻይ ቡና እንበል› ማለቱን ስላልወደድሁለት በቀጠረኝ ቀን እንዲህ ነዉ ሳልለዉ ቀረሁ። አኩርፎ ይተወኛል ስል፣ ጭራሽ የሥራ ቦታዬ ድረስ መጣብኝ።

“ሙሌን surprise እንድናደርገዉ ብቀጥርሽ እኮ” ብሎ ጀመረለኝ፣ በጥሩ ትህትና።

“ይቅርታ ግሩም፤ ቀጥሬህ መቅረት አልነበረብኝም። ቢያንስ እንዳልተመቸኝ መንገር ነበረብኝ” አልሁት፣ የእዉነትም እንደማፈር ብዬ። “አንተስ ቡና ልጋብዝሽ እንጂ ሙሌን surprise እናደርገዋለን መቼ አልኸኝና? ቢሆንም ግን ይቅርታ በእናትህ”

“ችግር የለዉም፤ መቼ ይመችሻል ታዲያ?”

“አሁን” አልሁት፣ ብድግ ለማለት እየተሰናዳሁ። በሙሌ መጣብኛ! “አንተ አሁን አትችልም እንዴ?” አልሁት፣ አልችልም ቢለኝ አንቄ የምፈጠርቀዉ እየመሰለኝ።

“በአንድ ነገር ከተስማማን”

“በምን?”

“ይኼ የእኔ ሐሳብና እቅድ ነዉ። ስለዚህ እኔ የምልሽን ነዉ የምናደርገዉ። ሳያስበዉ እንዴት ጉድ እንደምንሰራዉ ለእኔ ተይልኝ፣ በደንብ አስቤበታለሁ። መቼም እንደተጫወትንበት ሲያይ እንዴት እንደሚሆን ይታየኛል” አለኝ፣ ጉጉቱን እያጋባብኝ። እንዴት ይሆን የሚደሰተዉ? ሞክሬዉ ስለማላዉቅ ጓጓሁለት። እንዲሁ ልቤ ከፍ እንዳለች፣ ተከትየዉ በግሩም መኪና ተሳፈርሁ።

“ወደ የት እንደመጣን እንኳን መጠየቅም አይቻልም?” አልሁት፣ ነድቶ ነድቶ ከአንድ የኮንዶሚኒየም ግቢ እንደገባን መኪናዉን ሲጥጥ አድርጎ ሲያቆም። ዐይኖቹን በእጆቹ ጨፍኖ ዝም አለኝ። በዝምታዉ ቀይቶ፤ የአባይን አቅጣጫ ሳይቀር የሚያስት ከባድ ትንፋሽ ተንፍሶብኝ፣ እየተንቀጠቀጠ ቀና ብሎ አየኝ።

“ምነዉ?” አልሁት፣ ለተለዋወጠ ፊቱ ምክንያት ባጣለትና ቢጨንቀኝ።

“አየሽ፤ አንቺ በጣም የዋህ ሴት ነሽ” አለኝ፣ እንባ ላዘሉ ዐይኖቹ መሸሸጊያ እያጣላቸዉ። እንደፈራሁት! ለሌላ ነገር ፈልጎኝ ነዉ በቃ? የገዛ ጓደኛዉ ፍቅረኛ አይደለሁ እንዴ? ‹የዋህ ነሽ› ብሎ ነገር፣ ቆይ ምን አባቱ አገባዉ ስለእኔ የዋህነት! ልዉጣ ልዉጣ የሚል ቁጣዬን እንደምንም አባብየ ላስጨረሰዉ ተበራታሁ።

“ሙሌም ቢሆን በጣም በጎ ሰዉ ነዉ። እንደሱ ያለ ቀና ሰዉ ሁሉ አላዉቅም”

ንግግሩ ላይ ምንም የሽሙጥ ቃና ባላገኝበትም፣ የባሰ ቅፍፍ አለኝ። በዚህ ሁኔታ ሳለን፣ ፊት ለፊታችን ወዳለዉ የኮንዶሚኒየም ህንጻ እንድከተለዉ በግንባሩ ለመነኝ። እንዲሁ አፌን ደም ደም እንዳለዉ ተከትየዉ ሁለተኛ ወለል ላይ ወዳለ አንድ ቤት ከመድረሳችን፣ ከጫፍ እስከጫፍ ይህ ቀረሽ ቢሏት የምታስቀስፍ ቆንጆ ሴት ብቅ ብላ በፈገግታ ተቀበለችን።

“እንዴ ግሩሜ? ሙሌን ሰርፕራይዝ እናደርገዋለን ብለኸኝ… የራስህን ሚስት በማስተዋወቅ እኔኑ ሰርፕራይዝ ማድረግ ነበር እንዴ እቅድህ? በል ተሳክቶልሀል” ብላ እርፍ! ምንድነዉ ያለችዉ? ጭራሽ ልታቅፈኝ ሁሉ ያምራታል ደግሞ? ወደኔ ያንከረፈፈቺዉን እጇን ሰብስባ፣ የቀደመዉን ንግግሯን እንድታብራራልኝ ልጠይቃት አፌን ሳሞጠሙጥ፤

“ሙሌን ምን ብለሽ ጠራሽዉ?” ብሏት ወደ ዉስጥ ለመዝለቅ በመሐላችን አለፈ - ግሩም።

“ራስ ምታት ሊገድለኝ ነዉ፣ ድረስልኝ ብየ ነዋ። መቼም መጨረሻህን ልይ ብየ፣ ዋሾ ሆኝልሀለሁ”

እኔ ምናቸዉም አልገባኝም። ምንድነዉ የሚያወሩት? ያም ሆኖ ግን እንግባ ሲሉኝ እምቢ አላልኋቸዉም፤ እግር በእግር ተከትያቸዉ ገባሁ። ልክ ሳሎኑን ስረግጠዉ፣ የሲዖልን ጦር የሚያስንቅ ነገር በሁለቱም ዐይኖቼ ተቀረቀረ። ጦሩ የተወረወረዉ የግድግዳዉን እኩሌታ ሸፍኖ ከተሰቀለዉ የሙሽሮች ፎቶግራፍ ነዉ። ይኼ ጦር ከፊት ለፊቴ እየተምዘገዘገ መጥቶ እስከሚወጋኝ ድረስ ያለዉን እንጂ ከዚያ በኋላ የሆነዉን አላዉቅም።

በሙሽሪት ቦታ እሷ፣ በሙሽራዉ ቦታ ደግሞ ሙሌ!

እንዲህ የተወጉ ዐይኖቼን ብዳብሳቸዉ፣ ደም ቀርቶ እንባ የሚባል ጠብ አላላቸዉም። በሞትና በሕይወት ድንበር ላይ ደንዝዤ ቆምሁ እንጂ ተዝልፍልፌ አልወደቅሁም። የኋላ ኋላ እንደምንም ነፍሴ መለስ ስትል፣ እስከ ጸሐይ ግባት ድረስ ወደግራም ወደቀኝም ሳልላወስ የወጋኝን ፎቶ ብቻ በዐይኖቼ እንደወጋሁ መቆሜን ነገሩኝ።

“ሙሌ?” አልሁት፣ በስንተኛዉ ቀን እንደሆነ እንጃለት የመንገድ ዳር ወንበር ላይ ተቀምጬ ወደእግረ ብርቱዋ ጸሐይ አፍጥጬ ሳለሁ። ከወደየት አቅጣጫ መጥቶ መቼ አጠገቤ እንደተቀመጠ ሁሉ እንጃለት።

“አቤት ፍቅሪ”

ፍቅሪ? አሁንም ፍቅሪ? ወኔዬ ሁሉ ሙጥጥ ባይልብኝ ኖሮ እስቅለት ነበር። ግን የመሳቂያ ቀርቶ እህ እህ የማለቱንስ አቅም ከየት ልዉለደዉ?

“ንገረኝ እስኪ ሙሌ፤ እንዴት ሆነልህ በማርያም? እንዴት ቻልህበት? ለሁለት ሰዉ መሳቁን፣ ለሁለት ሰዉ የሚበቃዉን ልብ፣ የሁለት ሴቶችን ሕይወት ማበላሸቱን እንዴት ቻልህበት? በማርያም ንገረኝ እስኪ”

ዝም።

“እንዴት እንዴት አወቅህበት?”

ጭጭ።

“እሺ፤ አሁንስ ለምን መጣህ? ነፍሷ አልወጣችም ብለህ ልትጨርሰኝ ነዉ? ስንት ነፍስ ያለኝ መስሎሀል? አንዴ ነዉ የምኖረዉ፣ እሱንም ገድለኸኛል እኮ”

ዝም። መሬት መሬት ማየት ብቻ። ለነገሩማ ልመልስልሽስ ቢል ምን ይመልስልኛል? ምንም። እኔ እንዲሁ በሰመመን ዉስጥ እንደወደቅሁ፣ ልዩነታቸዉን የማላውቅላቸዉ መዓት ቀንና ሌሊቶች አለፉ። ስንት እንደሆኑ ያልቆጠርኋቸዉ ወራት ነጎዱ። ድብርት፣ ብቸኝነት፣ መጠቃት፣ ተስፋ መቁረጥ ቀኑን ጨለማ - ጨለማዉን ደግሞ ድቅድቅ ጨለማ አደረጉብኝ።

ከእነዚህ በቀለኛ ቀናት በአንደኛዉ፣ የቆዩ ፎቶዎቼን ማገላበጥ አሰኘኝ። ያን ያህል ፎቶ ወዳጅ ሆኜ ብዙ ባይኖረኝም፣ አሁን የሚወሰዉሰኝን ስሜት ለማስታገስ ግን ይበቃሉ። ያቅማቸዉን ያህል ከተሸከሙት ትዝታ ጋር ገለጥ ገለጥ አደረግኋቸዉ። ትምሀርት ቤቶች፣ ሥራ ቦታዎች፣ ዘመዶች፣… ጓደኞች! ከጓደኛም ደግሞ ወንድሞቼ እላቸዉ የነበሩ ጓደኞች ዐይነ ልቦናዬ ላይ መጡብኝ።

ስልኬን አፈፍ አድርጌ ተነሳሁ።

ሴት ልጅ ነኝ። ያዉም የሐበሻ ሴት ልጅ። ምን? ልጅ? ሴትዮ ነኝ ኧረ! ሠላሳ አራት ዓመታትን ያህል እድሜ ያለትዳርና ያለልጅ ጭልጥ ያደረግሁ የሐበሻ ሴትዮ ነኝ። መፍጠን አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ጊዜ የሚባል የለኝም። ልብስ የምቀይርበት ቀርቶ ፊቴን እንኳን የማብስበት ጊዜ አልቀረኝም። የእድሜየ አመሻሽ ላይ ነኝ። ይኼን እያብሰለሰልሁ ወጣሁና ቀድሞ በወንድምነት ወደማዉቀዉ አንድ ስልክ ደወልሁ። ያለ ምንም መግቢያና መዉጫ ‹እንገናኝ› አልሁት አፌን ሞልቼ። አላሳፈረኝም፤ እሺ በሎ መጣልኝ። ከጥድፊያየ የተነሳ፣ ገና በቅጡ እንኳን ሰላም ሳንባባል ሊያገባኝ ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅሁት። አሃሃሃ ብሎ ከላይ ከሰማይ ነዉ ሳቁን የለቀቀብኝ። የሐምሌን ዶፍ የሚያስንቅ ሳቅ ያለ ፋታ አወረደብኝ። ልክ እንደዝናቡ ያለማቋረጥ ለግማሽ ሠዓት ያህል እኝኝ ብሎ አሽካክቶብኝ፣ በተጎለትሁበት ጥሎኝ እብስ አለ። ያዉም በቡና ቤት እኮ ነዉ፤ ሰዉ ባለበት! ማፈር አልነበረብኝም? መግቢያ ማጠት አልነበረብኝም? እኔ'ቴ! ጭራሽ ሌላ የወንድ ስልክ አዉጥቼ ደወልሁ። ነገር ግን፣

ባለስልኩ ከሀገር መዉጣቱን ወንድሙ ነኝ ብሎ ስልኩን ያነሳልኝ ነገረኝ። ድምጹን ስለወደድሁት፣ ‹አንተስ ብትሆን ለምን አትመጣልኝም› ልለዉ ሁሉ ነበር።

“Almost there!” ይል የለ ፈረንጅ? አብጃለሁ በቃ። ከእብደት የሚያተርፈኝ አለመኖሩን ሳዉቅ ደግሞ ጨርሶ ለየልኝ። ዝምታም መጮህም እኩል አማሩኝ። መቆምም መቀመጥም ያዉ ሆኑብኝ። ትኩስ ተብሎ የመጣልኝ ሻይ ለብ እንዳለ እንኳን አይሰማኝም። ደግሞ እኮ አያፍሩም ስኳር አለበት ይሉ ይሆናል! ኧረ ምንም ምንም አይልም። ግርም ድንቅ ያለኝ ግን፣ በዚህ ሁሉ ስሜት መሐል ሆኜ፣ አሁንም አሁንም ሙሌ ይሉት መንፈስ በሐሳቤ ሽዉ ማለቱ ነዉ። ብቻ መልሶ እሱ ላይ ባልጣለኝ፡፡ በቃ አብጄ የለ? ስለ ጨርቅ አጣጣሌ ሳወጣ ሳወርድ አንድ ለስላሳ እጅ ትከሻዬ ላይ አረፈ። ቀና ብዬ ማየት አላስፈለገኝም፣ ጥላዋን ሳይቀር አዉቀዋለኋ! እሷ ናት። እንደ እናቴ ነሽ ያልኋት፣ እንደ እናቴ የሆነችዋ ጓደኛዬ ናት ጨርቅ ከመጣል ልታተርፈኝ ከተፍ ያለችልኝ።

ታተርፈኝ ይሆን? እንጃልኝ ብቻ፡፡ እሷ ሆናብኝ፤ እሺ ብያታለሁ እንግዲህ፡፡

“እሺ፤ እስኪ ሞክሪኝ”
/\
ምንጭ
የሓ ቤተ ጥበብ (www.yehaarts.com)

የመጨረሻ እሁድ፣ ልዩ እድል!‹‹አለቃ ገብረሃና - ሸምጋይ›› ቴአትራችንን በርካታ ተመልካቾች እንደወደዳችሁልን በሰጣችሁን አስተያየት ተገንዝበናል፤ እናመሰግናለን!የፊታችን የካቲት 30/2017...
08/03/2025

የመጨረሻ እሁድ፣ ልዩ እድል!

‹‹አለቃ ገብረሃና - ሸምጋይ›› ቴአትራችንን በርካታ ተመልካቾች እንደወደዳችሁልን በሰጣችሁን አስተያየት ተገንዝበናል፤ እናመሰግናለን!

የፊታችን የካቲት 30/2017 በ8:00 ሰዓት የ"እሁድ" እይታውን ጨርሶ፣ ቀድሞ ወደነበረበት ወደ ሐሙስ ምሽት የሚዘዋወረውን ቴአትር ለመመልከት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንድትገኙልን ስንል በትህትና ጋበዘናል።
በተለይ ሐሙስ ሐሙስ ምሽት የማይመቻችሁ ተመልካቾቻችን ሁሉ፣ ይኸኛዉ እሁድ አያምልጣችሁ።



አ ለ ቃ ገ ብ ረ ሐ ና
ተጨዋች ፧ ብልህ ፧ ፭ ዐይና ፧ ሸምጋይ
ታሪክ ቀመስ ꕹ ዘወትር ሐሙስ በ11፡40 (የአሁኑ እሁድ 8፡00 እንዳለ ሆኖ)
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

ደራሲⴾ ታደለ አያሌዉ
አርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾ ሣሙኤል ተሥፋዬ
ረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬ
ተዋንያንⴾ እታፈራሁ መብራቱ፣ ብርሃን ተሥፋዬ፣ ፍቅሩ ወሠኔ፣ ሰላማዊት በዛብህ፣ ግርማ ተሾመ፣ ክብይናድ አሠፋ፣ ናትናኤል መኮነን፣ አማኑኤል ወርቁ፣ ኢዮብ ገረመዉ እና ሌሎቹም።

#ሸምጋይ
ተጨማሪ፡
yehaarts.com/theNewTheater
CC: Tadele Ayalew


‹‹ልጆቼ ምንም ቢቸግራችሁ ምን፣ የደናቁርት መጫዎቻ ግን እንዳትሆኑ! ያኛዉ ጊዜ በእኛም ጊዜ፣ እየታየ ነዉ!››

08/02/2025

ያኛዉ ጊዜ በእኛም ጊዜ፣ እየታየ ነዉ!

አ ለ ቃ ገ ብ ረ ሐ ና
ተጨዋች ፧ ብልህ ፧ ፭ ዐይና ፧ ሸምጋይ
ታሪክ ቀመስ ꕹ ዘወትር እሁድ በ8፡00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

ደራሲⴾ ታደለ አያሌዉ
አርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾ ሣሙኤል ተሥፋዬ
ረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬ
ተዋንያንⴾ እታፈራሁ መብራቱ፣ ብርሃን ተሥፋዬ፣ ፍቅሩ ወሠኔ፣ ሰላማዊት በዛብህ፣ ግርማ ተሾመ፣ ክብይናድ አሠፋ፣ ናትናኤል መኮነን፣ አማኑኤል ወርቁ፣ ኢዮብ ገረመዉ እና ሌሎቹም።

#ሸምጋይ
ተጨማሪ፡
yehaarts.com/theNewTheater
CC: Tadele Ayalew

‹‹ልጆቼ ምንም ቢቸግራችሁ ምን፣ የደናቁርት መጫዎቻ ግን እንዳትሆኑ››

መታየቱን ቀጥሏል! ፨አ ለ ቃ  ገ ብ ረ ሐ ናተጨዋች ፧ ብልህ ፧ ፭ ዐይና ፧ ሸምጋይታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ በ8፡00በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፨ደራሲⴾ ታደለ አያሌዉአርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾ ...
01/02/2025

መታየቱን ቀጥሏል!

አ ለ ቃ ገ ብ ረ ሐ ና
ተጨዋች ፧ ብልህ ፧ ፭ ዐይና ፧ ሸምጋይ
ታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ በ8፡00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

ደራሲⴾ ታደለ አያሌዉ
አርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾ ሣሙኤል ተሥፋዬ
ረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬ
ተዋንያንⴾ እታፈራሁ መብራቱ፣ ብርሃን ተሥፋዬ፣ ፍቅሩ ወሠኔ፣ ሰላማዊት በዛብህ፣ ግርማ ተሾመ፣ ክብይናድ አሠፋ፣ ናትናኤል መኮነን፣ አማኑኤል ወርቁ፣ ኢዮብ ገረመዉ እና ሌሎቹም።

#ሸምጋይ
ተጨማሪ፡
yehaarts.com/theNewTheater
CC: Tadele Ayalew

እስከአሁን ሐሙስ ሐሙስ ሲታይ የቆየዉ ‹ሸምጋይ- አለቃ ገብረሐና› ቴአትር፣ ከግንቦት 18 ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ዘወትር እሁድ በ8፡30 መታየቱን ቀጥሏል።

በሠላም ይረፉ ጋሼ።
19/01/2025

በሠላም ይረፉ ጋሼ።

አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡

አርቲስቱ የእግር እሳት፣ ሥርየት፣ ሰው ለሰው፣ መንጠቆ ቴአትር እና ሌሎች የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በትወና መሳተፉን የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

በአዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ የተወለደው አርቲስት እንቁስላሴ ÷በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጧል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ የሶስት ወንድ እና ሶስት ሴት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን÷አስራ ሁለት የልጅ ልጆችንም አይቷል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለአርቲስት እንቁስላሴ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

አለቃ ገብረሐና፧ሸምጋይ፧ታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ እሁድ በ8፡00በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፨ደራሲⴾታደለ አያሌዉአርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾሣሙኤል ተሥፋዬረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬተዋንያንⴾ እ...
04/01/2025

አለቃ ገብረሐና
፧ሸምጋይ፧
ታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ እሁድ በ8፡00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

ደራሲⴾታደለ አያሌዉ
አርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾሣሙኤል ተሥፋዬ
ረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬ
ተዋንያንⴾ እታፈራሁ መብራቱ፣ ብርሃን ተሥፋዬ፣ ፍቅሩ ወሠኔ፣ ሰላማዊት በዛብህ፣ ግርማ ተሾመ፣ ክብይናድ አሠፋ፣ ናትናኤል መኮነን፣ አማኑኤል ወርቁ፣ ኢዮብ ገረመዉ እና ሌሎቹም።

#ሸምጋይ
ተጨማሪ፡
yehaarts.com/theNewTheater

እስከአሁን ሐሙስ ሐሙስ ሲታይ የቆየዉ ‹ሸምጋይ- አለቃ ገብረሐና› ቴአትር፣ ከግንቦት 18 ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ዘወትር እሁድ በ8፡30 መታየቱን ቀጥሏል።

አለቃ ገብረሐና፧ሸምጋይ፧ታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ በ8፡00በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፨እስከአሁን ሐሙስ ሐሙስ ሲታይ የቆየዉ ‹ሸምጋይ- አለቃ ገብረሐና› ቴአትር፣ ከግንቦት 18 ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ...
31/05/2024

አለቃ ገብረሐና
፧ሸምጋይ፧
ታሪክ ቀመስ ꕹ እሁድ በ8፡00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

እስከአሁን ሐሙስ ሐሙስ ሲታይ የቆየዉ ‹ሸምጋይ- አለቃ ገብረሐና› ቴአትር፣ ከግንቦት 18 ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ዘወትር እሁድ በ8፡30 መታየቱን ቀጥሏል።

ደራሲⴾ ታደለ አያሌዉ
አርታኢ እና ዋና አዘጋጅⴾ ሣሙኤል ተሥፋዬ
ረዳት አዘጋጅⴾ ስናፍቅሽ ተሥፋዬ
ተዋንያንⴾ እታፈራሁ መብራቱ፣ ብርሃን ተሥፋዬ፣ ፍቅሩ ወሠኔ፣ ሰላማዊት በዛብህ፣ ግርማ ተሾመ፣ ክብይናድ አሠፋ፣ ናትናኤል መኮነን፣ አማኑኤል ወርቁ፣ ኢዮብ ገረመዉ እና ሌሎቹም።

#ሸምጋይ
ተጨማሪ፡
yehaarts.com/theNewTheater
CC:
Tadele Ayalew
Ethiopian National Theatre
ጉርሻ፡
የምሥራቹን ለብዙዎች ያጋሩና፣ የመግቢያ ካርዱን ይሸለሙ፡፡

27/05/2024

ቴአትር የእርስዎ የራስዎ የህይወትዎ ገጽ!
ይመልከቱ!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeha Arts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yeha Arts:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share