amir bilgu

amir bilgu اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

06/03/2024

ድሀ ማለት ሀብት ንብረት ገንዘብ የሌለው ማለት አይደለም ድሀ ማለት . . .
👉አላህን የማይፈራ
👉ተስፋ የሌለው! ፣
👉ህልም የሌለው! ፣
👉አላማ የሌለው! ፣
👉ራእይ የሌለው! ፣
👉እምነት የሌለው! ፣
👉ሰብአዊነትን ያጣ!
👉ፍቅር የማይገባው! ነው፡፡

02/03/2024

በገንዘብህ ምታስበው ጀለሴ ሆይ
ምንም እንኳን ሚሊዮን መኪናዎች ቢኖሩህ መኝታ ቤት በእግርህ ነው ምትሄደው እና እየሄድክ🚶‍♂️🚶🚶‍♀️

02/03/2024

የጎረቤታችን ልጅ ጠዋት አባትየው አትሂድ እያለው እንቢ ብሎት አድዋጋ ሄዶ ማታ ሲመጣ
አባት 🗣️ምን ቤት አለህና ትመጣለህ እዛው ከአርበኞቹ ጋር እደር እንጂ😡
😂😂😂😂

27/02/2024

አቃቃምሽ ያምራል እንዳልጠላው
በለውዝ መቃምሽ ግን ልቤን ጎዳው
ሱሰኛ መሆንሽ ቢያስከፋኝም
ዱርዬ ከመሆን አይብስም
✍️by amir 🥱👽

17/02/2024

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የደረሰበት ትልቅ ግኝትi
~
በጥናትና ምርምር ለሃገር ተስፋ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው ባለ ትልቅ ስሙ ዩኒቨርሲቲ ''ጀለቢያ በመልበስ እና ኢማማ በመጠምጠም እጅ ከፍንጅ ተይዘሃል'' እያለ ነው። ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ ማለት እዚህ ላይ ነው። ትልልቅ ብሄራዊ ተቋማት ያረገዙትን የሃይማኖት ጥላቻ የሚያወራርዱ ግለሰቦች የሚፈነጩባቸው ሲሆኑ ማየት የሚገርም ነው። አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሆይ! ይሄው ነው ቁመትህ? ይሄው ልኬትህ?

ASTU_Official በነውራችሁ አታጊጡ። በሚያሳፍር ነገር ራሳችሁን አታስተዋውቁ። ዲሲፕሊንን ለፅንፈኛ አካሄድ ሽፋን ማድረግ የነቀዘ ስልት ነው። ውስጣችሁን ፈትሹ። ተቋማችሁን በክፉ ከሚያስጠሩ ኋላቀሮች አጥሩ።
=
"ሼር" ብታደርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

🫡ክብር ለአባቶች😢😭ለምንድነው ብዙ ግዜ ለአባቶች ክብር የማይሰጠው ወይም አንድ ሰው ስኬት ላይ ስደርስ አባቴን አኮራዋለው የማይለው❓አባቶች ችግራቸውን ስለማይናገሩ ቸግሯቸው እንኳን ስለማይጠይ...
12/02/2024

🫡ክብር ለአባቶች😢😭

ለምንድነው ብዙ ግዜ ለአባቶች ክብር የማይሰጠው ወይም አንድ ሰው ስኬት ላይ ስደርስ አባቴን አኮራዋለው የማይለው❓

አባቶች ችግራቸውን ስለማይናገሩ ቸግሯቸው እንኳን ስለማይጠይቁን ለኛ ብለው ሳይለብሱ ስላለበሱን ብንቀርባቸው እና ችግራቸውን ብንካፈል በጣም ትልቅ ሸክም እንደተሸከሙ ይገባን ነበር❗

ነብር🐆ዥጉርጉርነቱን አባት አባትነቱን መቼም አይቀይርም❕ለቤታችሁ እራስ ለሆነው አባት ክብር ስጥ ምክኛቱም አንተም አንድ ቀን አባት ትሆናለህና‼️
👉 መስዋዕትነት ቆሞ ሲሄድ ካየህው እሱ አባትህ ነው‼️
🎗️ አስታውስ ወንድሜ ምንጊዜም ከሱ ተሽለህ ስትገኝ የሚደሰት ሰው ቢኖር አባትህ ነው‼️

ስልጤዎች ንቁ ህዝባችሁም አንቁእኛ ሙስሊሞች ተኝተናል የአkf ሮት ሀይላት ምን ያህል እርቀት እየተጓዙ መሆኑን እንመልከት ከተማዎች ላይ የሚሰሩት በጣም በትንሹ መሆኑንና በገጠር ማህበረሰብ ላ...
12/02/2024

ስልጤዎች ንቁ ህዝባችሁም አንቁ
እኛ ሙስሊሞች ተኝተናል የአkf ሮት ሀይላት ምን ያህል እርቀት እየተጓዙ መሆኑን እንመልከት ከተማዎች ላይ የሚሰሩት በጣም በትንሹ መሆኑንና በገጠር ማህበረሰብ ላይ ምን ያህል እንደዘመቱበት እንመልከት
እና ስልጤዎች እባካችሁን ንቁ እናንተን ማጣት ትልቅ ዋጋ ያስከፍለናልና
👉 ይሄ ምታዩት በስልጥኛ ቋንቋ ጴንጤዎች ለአክfሮት ያዘጋጁት መፅሐፍ ነው
በማድረግ ማህበረሰባችንን እናስጠንቅቅ

10/02/2024

ጡት እንዳየ ሕፃን ወተት እንዳማረው
ደውይልኝ ውዴ ድምፅሽ ሕይወቴ ነው🫤

09/02/2024
የኡስታዝ  ሙሀመድ ኸድርን ዳእዋ ለማገዝ ዘመቻው ተጀመሯል እነሆ የእካውንት ቁጥሩ  Muhammed Khedr Essa         CBE  1000258086857  \\ Zamzam Bank  000...
07/02/2024

የኡስታዝ ሙሀመድ ኸድርን ዳእዋ ለማገዝ ዘመቻው ተጀመሯል
እነሆ የእካውንት ቁጥሩ
Muhammed Khedr Essa
CBE 1000258086857 \\
Zamzam Bank 000+19768+20101 .\\....Hijra Bank
1000771510001 ስልክ ቁጥር +251953379500

በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ 5:2

ሰዉ ሁሉ ነገረኛ ሆኖዋል እንዴ🙄😳🤣🤣😂🤣😂
06/02/2024

ሰዉ ሁሉ ነገረኛ ሆኖዋል እንዴ🙄😳🤣🤣😂🤣😂

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!~ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ንግግር ነው። የውሸት እርከኑን በዚህ መጠን ከፍ አድርጎታል። ውሸቱን ሲለማመደው ጊዜ "አንባቢ ይታዘበኛል" የሚለውንም ትቶታል። እንዲያው ...
03/02/2024

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
~
ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ንግግር ነው። የውሸት እርከኑን በዚህ መጠን ከፍ አድርጎታል። ውሸቱን ሲለማመደው ጊዜ "አንባቢ ይታዘበኛል" የሚለውንም ትቶታል። እንዲያው አንድ ሰው መስሎት ተሳስቶ ቢናገር ይሁን። ይሄ ሐያእ የቀለለው ፍጡር ግን በምን መልኩ ሰው ላይ እንደሚዋሽ ተመልከቱ። ሳዳት ነው ወደነዚህ አካላት የሚጣራው? በሐዲሥ እንደመጣው ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ ሲያወሩ መዋሸት እና በሙግት ላይ አመፀኝነት ወይም ገልብጦ መወንጀል ነው። በነዚህ አጥፊዎች ላይ ረድ መስጠት ነው ወደነሱ መጣራት ተብሎ የሚገለፀው? ጥላቻ አናቱ ላይ ወጥቶ በትክክል ማየት እንዳይችል ጋርዶታል። በረድ ስም እየዋሸ መለጠፍ ጣፋጭ ምግብ ሆኖለታል። እጅ እጅ የሚል ፅሁፉን ውሸት ጣል ሲያደርግበት ውበትና ጥንካሬ የሚጨምር ይመስለው እንደሁ አላውቅም። "የሰካራም ግጥም ሁሌ ቅዳ ቅዳ" እንዲሉ ወጥሮ የውሸት አውቶማቲክ መተኮሱን ተያይዞታል። ረድ ማለት የጠሉት ሰው ላይ የፈለጉትን መለጠፍ ሆኗል ባህሩ ዘንድ። ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ውሸትን ስራዬ ብሎ አጥብቆ ይይዛል? ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
وإِيَّاكُمْ والْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، ومَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ ويَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللَّهِ كَذَّابًا
“አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽና ውሸትም ላይ ሲያተኩር አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል።” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ሳዳትን በማጠልሸት ላይ እንቅልፍ ከምታጡ ራሳችሁን ከዚህ የውሸት ሱስ አውጡ። ሳዳት እናንተን ከነ ንዝንዛችሁ እርግፍ አድርጎ ትቶ አነሰም በዛም የራሱ ስራ ላይ ነው ያለው። ደግሞም በተለይ ተራውን ህዝብ በማንቃት ላይ ባለው አስተዋፅኦ አንዳችሁ እንኳ የሚስተካከል ቀርቶ የሚቀርብ ነገር የላችሁም። የራሳችሁን ድርሻ ባግባቡ እንደመወጣት ሰዎች የሱን ትምህርት እንዳይከታተሉ ጥላሸት መቀባትን ጂሃድ አድርጋችሁታል። ይሄ ነው የናንተ ስኬት።
ባህሩ ተካ እንደምታዩት ወንድማችን ሳዳትን ወደ "ቲክ – ቶክ መንደር ወርዶ ወጣቱን ወደ ዮኒ ማኛና ኢክራም አውቶሞቲቭ" ይጣራል እያለ ነው።
* ሳዳት ከአጥፊዎች ነው ያስጠነቀቀው። ባህሩ ደግሞ አጥፊዎቹን ጥሎ ሳዳትን መዝለፍ ላይ ነው የተጠመደው። ከአጥፊዎች ማስጠንቀቅ ወደነሱ መጣራት ከሆነ እንዳበደ ውሻ ሁሉን የምትናከሱት እናንተ አጥፊዎች ወደምትሏቸው እየተጣራችሁ ኖሯል ለካ? መቼም በራሳችሁ ጩኸት ስለደነቆራችሁ ሂሳባችሁ ምን እንደሚሰጥ አይገባችሁም።
* ምናልባት አጥፊዎቹን ፊት ለፊት ተገኝቶ መምከሩን ከሆነ ወደነሱ መጣራት የምትለው ይሄ ምን ያህል በልብህ ያረገዝከው ጥላቻ ነገሮችን የመረዳት አቅምህንም እንዳሽመደመደው ነው የሚያሳየው። እንዲያው አቀራረቡ ላይ ሂስ አለኝ ብትል እንኳ እንዳንተ አይነቱ በቆሻሻ የብሄር ካባ ተጀቡኖ የጉራጌ ካፊ'ሮች ጋር አንድነት ስለማድረግ የሚሰብክ ሰው ሂስ የመሰንዘሩን ድፍረት እንዴት ነው የሚያገኘው? የጥላቻ ብቅል ይህን ያክል ያሰክራል ለካ! የሚገርመው በዚህ መልኩ አይኑን በጨው አጥቦ እየዋሸ "ውሸታም" ተባልኩ ብሎ ሲብሰው ማየት ነው። የእውነት ህሊና ካለህ ከመባልህ ይልቅ መሆንህ ባስጨነቀህ ነበር። ያለበለዚያ ነገሮችን እየገለበጥክ ማየትህን ትቀጥላለህ። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ ምን እንደሚሉ ተመልከት:-
إياك وَالْكذب فَإِنَّهُ يفْسد عَلَيْك تصور المعلومات على مَا هِيَ عَلَيْهِ وَيفْسد عَلَيْك تصورها وَتَعْلِيمهَا للنَّاس فَإِن الْكَاذِب يصور الْمَعْدُوم مَوْجُودا وَالْمَوْجُود مَعْدُوما وَالْحق بَاطِلا وَالْبَاطِل حَقًا وَالْخَيْر شرا وَالشَّر خيرا فَيفْسد عَلَيْهِ تصَوره وَعلمه عُقُوبَة لَهُ.
"ውሸትን ተጠንቀቅ። እሱ መረጃዎችን ባሉበት ሁኔታ (በትክክለኛ ቅርፃቸው) የመረዳት አቅምህን ይበክልብሃል። በተጨባጭ መሳልና ማሳወቅንም እንዲሁ ያበላሽብሃል። ውሸታም የሌለውን እንዳለ፣ ያለውን እንደሌለ፣ እውነቱን ሃሰት፣ ሃሰቱን እውነት፣ ኸይሩን ሸር፣ ሸሩን ደግሞ ኸይር አድርጎ ገልብጦ ያቀርባል። በውሸቱ ይቅቀጣ ዘንድ የመረዳት አቅሙም እውቀቱም ይበላሽበታል።" [አልፈዋኢድ፡ 135]
ውሸትን እንደ ፅድቅ ማየት የሚመጣው በዚህ ምክንያት ነው። "የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል
IbnuMunewor

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
AMIRELWANS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when amir bilgu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to amir bilgu:

Share