29/09/2022
ለ13 አመታት ባለቤት ያጣው የከርሰ ምድር ውሃ
ቆቦ ወይም የ06 ቀበሌ በሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች አንዱ ሲሆን በደርግ ዘመነ መንግስት ተበታትነው የነበሩ ገበሬዎችን በመንደር ምስረታ በአንድ አካባቢ አንዲሰፍሩ በማድረግ የተመሠረተች ውብ ቀበሌ ነች::
የአካባቢው ማህበረሰብ በዋናነት በግብርና የሚተዳደር ሲሆን ሌት ከቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚሰራ እንደሆነ ይታወቃል:: ደግ ና ቀና ማህበረሠብ ነው::
የቆቦ ወንዝ በመጥለፍ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለገበያ በማቅረብ ይታወቃል::
ይህ ወንዝ ታዲያ በጣም ትንሽ ና በበጋ የሚደርቅ በመሆኑ የእግዜር ውሀ ካልተጨመረ በስተቀር ከፍተኛ ጉልበት ና አቅም ቢኖርም በአመት ከአንድ ጊዜ በላይ ለማምረት አልተቻለም:: አብዛኛው ወጣት በየፑል ቤት ጫት ቤት ና ጆተኒ ሲጫወት ወዘተ ይውላል:: የወጣትነት ጉልበቱም በመባከን ላይ ይገኛል::
ነገር ግን ከሸዋሮቢት ከተማ በአራት ና አምስት ኪሎ ሜትር ላይ ከሦሥት ቦታ ከገበሬው ማሣ ላይ ተቆፍሮ ከአስራ ሶስት አመት በፊት ማለትም በ2003 ዓ.ም የተመረቀ ሦሥት የከርሰ ምድር ውሃ ወደ ስራ አለመግባቱ እጅግ ያሳዝናል::
ባጠቃላይ 3ቱም የከርሰምድር ውሃዎች ከ2000 ስኩየር ኪሎሜትር በላይ መሬትን የማልማት አቅም ያላቸው ሲሆን ላለፋት 13 አመታት በስራ ላይ ባለመዋሉ ምክንያት 2,496,000,000,000.00 ብር በላይ ገቢ አሳጥቶናል::
ይህ ውሃ ወደስራ ቢገባ ማህበረሰቡ በአመት አራት ጊዜ ማምረት ይችላል በሰፋት በማምረት ለገበያ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል ሰፊ የስራ ዕድል ይፈጥራል:: ማህበረሰቡ በራሱ አምርቶ በመሸጡ በከፍተኛ ተጠቃሚ ይሆናል:: ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ ያለውን ሀብት አሟጦ መጠቀም እየቻለ ባላቸው የጥገኝነት አስተሳሰብ ምክንያት አስራሶስት አመት ሙሉ በማፈን እስካሁን ያለምንም ግልጋሎት አስቀምጠውታል::
መራዊ አካባቢ ያለው የቆጋ መስኖ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ነው የተጀመረው መራዊ አካባቢ ያለው ገበሬ በማህበር ተደራጅቶ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በማምረት ለማህበረሰቡ ያቀርባል ሰፊ የስራ ዕድል ተፈጥሯል አልፎ ተርፎም ወደውጭ በመላክ ከፍተኛ ምንዛሬ አስገኝቷል:: ይህ ግን ባለቤት እንደሌለው የህዝቡን ድምፅ በማፈን ትርፍ አንጀቱ የብአዴን/ብልፅግና
በማህበረሰቡም በሀገረም ላይ ከፍተኛ ኪሳረ አድረሷል እያደረሰም ይገኛል::
የአካባቢዉ አመራሩ ምን አስቧል
የመስኖ ውሃው ከመለቀቁ በፊት ለኢንቨስትመንት ለገበሬው ዝቅተኛ የካሳ ክፍያ በመስጠት ና የኢንቨስተር ቅጥረኛ ማድረግ ና ትንሽ ፍርፋሪ በማግኘት መጠቀሚያ ዘዴ ለማድረግ እንደሆነ የውስጥ አዋቂዎች ያስረዳሉ::
የአካባቢውን ገበሬ በማህበር በማደራጀት የስራ እድል እንዲፈጥር እነዲያመርት ለገበያ እንዲያቀርብ ና ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ መስራት ለበአዴን/ብልፅግና መራሹ የቅጥረኝነት ና ጥገኛነት መፍለቂያ ማዕከል የሆነ አመራር ፈፅሞ በአምሮው የማይታሰብ ሆኖ መታየቱ ህዝቡን የሚጠቅም ሳይሆን አመራሩ በህዝቡ ተጠቃሚ የሆነ ላም የሌለበት ኩበት የሚለቅም አመራር መፈጠሩ እጅግ ያስገርማል!!! ያሳዝናል!!!
በመጨረሻም መንግስት የማህበረሰቡን ማነቆ የሆነበትን ችግር ፈቶ መስኖውን ወደስራ በማስገባት የአካባቢው ማህበረሰብ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ እንዲመቻች ስል ለማስገንዘብ እንፈልጋለን
ከይፋት ሸዋሮቢት