ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል

  • Home
  • ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል አላማችን በቀደምት የኢትዮጵያ ትላልቅ መሻኢኾችና ዑለማኦች ለሀገራችን ስላምንና አንድነትን መስበክ ነው።

17/07/2024

አልሐምዱ ሊላህ
ሸይኽ ሙሐመድ አብራርን አላህ አትርፏቸዋል:: የታሰበው የተሴረው ሳይሳካ ቀርቷል:: ሁሌም አላህ በጥበቃው ስር እንዲያደርጋቸው እንለምናለን:: በኝህ ትልቅ ሰው ላይ ይህንን የግድያ ሙከራ ያደረጉ ሰዎችና ከጀርባ ያሉ ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እንዲቀጡ የሚመለከታቸው የህግ አካላት ሊሰሩ ይገባል:: ሙስሊሙም መሻይኾቹን እንዲጠብቅ አደራ እላለሁ::

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ወ ያ ኔ(የቀጠለ...)ሲስቃይ የኖረው ሕዝቡ ሲማኩስህዝቡ መላው ጠፍቶት ተገዶ ሲያለቅስማቃጠል ጀመሩ ነገር መቆስቆስመቀርጠጥ ጀመረ ቁስሉ መናክስየቋጠረው መግል ...
07/07/2024

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ወ ያ ኔ(የቀጠለ...)

ሲስቃይ የኖረው ሕዝቡ ሲማኩስ
ህዝቡ መላው ጠፍቶት ተገዶ ሲያለቅስ
ማቃጠል ጀመሩ ነገር መቆስቆስ
መቀርጠጥ ጀመረ ቁስሉ መናክስ
የቋጠረው መግል ጀመረ መፍሰስ
ማሰር መግደል ሆነ አገሩን ማመስ፤

እየጠና ሄደ እየተባባሰ
ጠላት እየበዛ ወዳጅ እያነስ
ፍጅትማ አይቀርም ቡዙ ዴም ሳይፈስ
ሕዝቡ ቂም አርግዞ ታየኝ ሲላወስ
ሲወለድ ማን ያውቃል የት እንደሚደርስ
ወያኔ ኢትዮጵያን ጋልቦ እንደፈረስ
ሸገዳየ እያለ ሌተቀን ሲደንስ፤

አገር ሲሸነሽን እንዴ ቡና ቁርስ
ተቆርቋሪ ጠፍቶ ደም የሚመልስ
ተንቅልፉ የነቃ የሚንቀሳቀስ
የጋለውን ምጣድ በጁ የሚያስስ
እንጀራው ተጋግሮ ለቁርስ እንድደርስ
ተቦክቶ ኩፍ ያለ ሊጥ አለ የሚፈስ፤

ሸዋ ምግብ ሰርታ ሰው ጠርታ ድግስ
ትንሹን ትልቁን በጇ ስታጎርስ
ያጎረሰው እጇ ጣቷ ሲነከስ
ያለብሷት መስሏት ኩታና ቀሚስ
ደበሎ አለበሏት የደም ሸማ ልብስ
ጎዳናው በሬሳ እስቲልከሰክስ።
ይቀጥላል.....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit
Jibril Tube - ጅብሪል ቲዩብ ን ያድርጉ።
👉 https://www.youtube.com/channel/UCLkOv3Zuz5-P1qXmAxSyJ6Q?sub_confirmation=1

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ተውሒድ ከተናገሩት:-በዲን መከራከር ለሁሉም ይጠቅማልየማታውቀው ነገር በዙ ይታወቃልአንዳንዱ ዐላህ የት ነው ብሎ ይጠይቃልስለድን አያውቅም ግን ይከራከራልእንደዚህ ያለው...
04/07/2024

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ተውሒድ ከተናገሩት:-

በዲን መከራከር ለሁሉም ይጠቅማል
የማታውቀው ነገር በዙ ይታወቃል
አንዳንዱ ዐላህ የት ነው ብሎ ይጠይቃል
ስለድን አያውቅም ግን ይከራከራል
እንደዚህ ያለው ሰው ቡዙ ይሳሳታል
ውሸት በመናገር ሰውን ያታልላል
አዋቂነኝ ብሎ ቁራአን ይፈስራል
እሱ አዋቂ ሆኖ ሰውን ያጃጅላል
ያለስራው ገብቶ ድኑን ያዳክራል
ተፈለገ ደርሶ ትልቅ ሸህ ይሆናል
ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ይሾማል ይሽራል
ለንደዚህ ያለው ሰው ሌላ ምን ይባላል
እንደው አንተው ሁነን ማለቱ ይበልጣል።

የ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ወቅታዊና ሚስጢራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል:-
1) የቴሌግራም ቻናላችን JOIN ይበሉ።👇
👉 t.me/ShehHusenJibrilTinbit

2) Jibril Tube - ጅብሪል ቲዩብ ን ያድርጉ።👇
👉 https://www.youtube.com/channel/UCLkOv3Zuz5-P1qXmAxSyJ6Q?sub_confirmation=1

3) የFB ፔጃችንም Like & share ያድርጉ።👇
👉 www.fb.com/ShehHusenJibrilTinbit/

ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ከ200 አመታት በፊት ስለ አማርኛ ቋንቋ የተናገሩት ትንቢት በኛው ዘመን እውን ሆነ 🙏🙏🙏ወቅታዊና ሚስጢራዊ ትንቢቶች ለመከታተል:-1) የቴሌግራም ቻናላችን JOIN ይ...
01/07/2024

ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ከ200 አመታት በፊት ስለ አማርኛ ቋንቋ የተናገሩት ትንቢት በኛው ዘመን እውን ሆነ 🙏🙏🙏

ወቅታዊና ሚስጢራዊ ትንቢቶች ለመከታተል:-
1) የቴሌግራም ቻናላችን JOIN ይበሉ።👇
👉 t.me/ShehHusenJibrilTinbit

2) Jibril Tube - ጅብሪል ቲዩብ ን ያድርጉ።👇
👉 https://www.youtube.com/channel/UCLkOv3Zuz5-P1qXmAxSyJ6Q?sub_confirmation=1

3) የFB ፔጃችንም Like & share ያድርጉ።👇
👉 www.fb.com/ShehHusenJibrilTinbit/

አላህ ለዘላለም ብቻውን ሲኖርቀለምና ለሁን አርሽና ኩርስይን ገና ሳይፈጥርግራ ቀኝ የሚባል አቅጣጫ ሳይኖርቦታ ሳይከልለው ዳርቻ ድንበርመላይኮችን ሳይፈጥር ጅንና በሽርገና ሳይዘረጋ ሰማይና ምድ...
29/06/2024

አላህ ለዘላለም ብቻውን ሲኖር
ቀለምና ለሁን አርሽና ኩርስይን ገና ሳይፈጥር
ግራ ቀኝ የሚባል አቅጣጫ ሳይኖር
ቦታ ሳይከልለው ዳርቻ ድንበር
መላይኮችን ሳይፈጥር ጅንና በሽር
ገና ሳይዘረጋ ሰማይና ምድር
ስራ ሳይጀምሩ ጨረቃ ጀምበር
ምንም ፍጥረት ሳይኖር ከሱ በስተቀር
አላህ በዛን ጊዜ ከምን ላይ ነበር?
አሁንም መልሰን ጥያቄ እንጀምር
እኛም እንጠይቀው እንድናተኩር
ምንም ፍጥረት ሳይኖር ጌታችን ነበር
ይቀመጥ ይዘርጋ ይቁም ይገተር
ባቀማመጡ ላይ የለንም ችግር
እንዴት ይኖር ነበር ቦታ እንኳን ሳይኖር
አዘልይ ነው ብለን ገና ሲጀመር
መጀመሪያም የለው መጨረሻም የለው ብለን ሰናስተምር
ምን አይነት ጥበብ ነው ምን አይነት ሚስጥር
ለማሰብ ያቃተ ለመመራመር
ቤቱ ሳይሰራ ከቤት ውስጥ መኖር
ይሄ ሁኖ አያውቅም በየትም ሃገር
አርሽ አዘልይ ነው ወይ እስኪ ተናገር?
አርሽ ላይ መቀመጥ አርሽን ሳይፈጥር
ጥያቄው መልሶ ያመጣል ችግር
መልስ ያስፈልገዋል በግልጥ በዟሂር
ተጠንቅቀህ መልስ ሳትደናገር?
አላህ አርሽን ፈጥሯል ካለ ጥርጥር
ከሁሉም አብልጦ በስፋት በቀድር
ፍጥረት የተባለ ባንድ ቢደመር
ያርሽ ሩብ አይመጣም ለመወዳደር
አርሽ ባላህ ስር ነው በሱ ቁጥጥር
አንድ ነገር የለም ተሱ ሚሰወር
አዘልይ የሆነው ጌታችን ጀባር
አዘልይ ቦታ አለው የማይቀየር
ከሱ የማይለይ አብሮት የሚኖር
አላህ መጀመሪያ ቀለምን ሲፈጥር
አርሽን ይቀድመዋል በድሜ ሲፈጠር
1000 አመት ይሆን ወይንም 2 ወር
የጊዚያቱ መርዘም ወይንም ማጠር
ለክርክራችን አይፈጥርም ችግር
ግን እንደማመጥ ስንከራከር
በመካከላቸው ዘመናት ነበር
ከቀለም ጀምሮ አርሽን እስኪፈጥር
ይኖራል ብለናል ካለ ቦታ አይኖር
አላህ በዛን ጊዜ ከምን ላይ ነበር?
መልስ በማጣትህ እንዳትሸበር
ለመወያየት ነው ለመመካከር
በዲን መከራከር የለውም ነውር
ዝም ብልም እዳ ብናገር ችግር
በዚህ የተነሳ በዚሁ ነገር
አየሁት ሃበሻን ህዝቡ ሲማረር
ልጅ አባቱን ሲሰድብ እያለ ካፊር
ቤተሰብ ሲለያይ ሲፋታ ትዳር
እስላሙ ከስላሙ ጋር ለማውራት ሲያፍር
ይሄ ቀን ይመጣል ታዘበኝ ቢቀር?
ይቀጥላል ....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል (ከባለፈው የቀጠለ...)ሳይደክም ሳይለፋ ስልጣን ለመውረስተሆነ መልካም ነው ቢገጥመው በለስግን እንዴት ይሳካል ጠየቅኩህ መልስየቀማ ታልቀማ ስልጣን አያቀምስሄዴ የተ...
25/06/2024

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል (ከባለፈው የቀጠለ...)

ሳይደክም ሳይለፋ ስልጣን ለመውረስ
ተሆነ መልካም ነው ቢገጥመው በለስ
ግን እንዴት ይሳካል ጠየቅኩህ መልስ
የቀማ ታልቀማ ስልጣን አያቀምስ
ሄዴ የተባለው ታየኝ ሲመለስ
እሱ መች ይለቃል ሕዝቡን ሳይጨርስ
መሶበር ይሻላል ችሎ መታገስ
ተላይ ትዛዝ መጥቶ እስቲለው ተነስ
መለፍለፍ ታከተኝ ልረፍ ልተንፍስ
ችግሩ ቡዙ ነው አንድ አንዱን ልጥቀስ
ሲሽነገል አይተው እስላሙ ሲካስ
ቄሱ ነደዳቸው ትልቁ ጳጳስ
በስላምም ተቀና ወይ ወጉ ይድረስ
ለራሱ የማያውቅ ይህ ሞኝ ቄስ።
(ከላይ የተጠቀሱት ቄስና ጳጳስ ለትግራይ አባቶች ይመስላል።)

ሲለካለት አየሁ ሲያሰፋ ቀሚስ
እንደ መንገደኛ ስንቁ ሲደገስ
አጃቢው ተጠርቶ ምላሽ ሲመለስ
ሰርጉ ተሰናድቶ ቀጠሮው ሲደርስ
ተከታትለው ሄዱ ደብተራና ቄስ
ቦምብ ቢፈነዳ መድፍ ቢተኮስ
መንደሩ ቢንጫጫ ቤተሰብ ቢያለቅስ
ማነው የሚያስቀራት ለተጠራች ነፍስ
ስልጣን ለስው ልጆች መች ስትቀመስ
ለሱ ብቻ አድርጓት ስቡሁል ቁዱስ
እንዳ እየወደዳት ጥሏት አለ እብስ
አዝራኢል ሲመጣ ያዛለ ቀንጥስ።

ይቀጥላል.....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

ትትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል@

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል (የቀጠለ...)https://t.me/ShehHusenJibrilTinbitየወያኔን ጂራፍ ኦሮሞው ቲቀምስእንቅፋት ሲመታው ጫማው ሲበጠስግብዣ ጠራ ሕዝቡን እንዲንቀሳቀስየወ...
21/06/2024

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል (የቀጠለ...)
https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit
የወያኔን ጂራፍ ኦሮሞው ቲቀምስ
እንቅፋት ሲመታው ጫማው ሲበጠስ
ግብዣ ጠራ ሕዝቡን እንዲንቀሳቀስ
የወያኔን ትዛዝ ሕጉን እንድጥስ
መንግስቱን ሊፋለም እልህ ሊያስጨርስ
የወገኑን ጥቃት ደሙን ሊመልስ
በሰው አጥር ዘሎ ደንበር ለሚጥስ
ለኔ ብቻ ብሎ ጠቅሎ ለሚጎርስ
አጥብቀህ ታገለው እንዳትመለስ
ተፈለግከው ቦታ ስፍራ እስተምደርስ
ባለስልጣን ቢሾም ሕጉን ቢያሳድስ
ቡዙም አያራምድ የትም አያደርስ
አገር አያሻሽል ችግር አይቀንስ
ይሂንን እያለ ያዘ መገስገስ።

እንዳትረሳው ቃሌን እንድታስታውስ
ውነቱን እናውራ ወሬ አናድበስብስ
ሕዝቡ ተሰልፎ ድምጡን ሲለግስ
ሲሯሯጥ አየነው ሁሉም ለመንገስ
ስልጣን የጠማችው የያዛቸው ሱስ
በምርጫ መስሏቸው ደም የሚመለስ
ጉልበቱን ተመትቶ ሸዋ ቢያነክስ
ቀን እስቲያልፍ በሎ ትንሽ ቢታገስ
ባፉ አያላመጠ ከንፈሩን ቢነክስ
አልገመተም ነበር አጥሩ እንዴሚጣስ
ለሰው ይመስለዋል ደግና ለጋስ
ሸዋ አንዳይገርማችሁ ቃልኪዳን ቢያፈርስ።

ይቀጥላል.....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ቲክቶክ ላይ በሚለቃቸው ዳዕዋዎች የተነሳ ከሙስሊሙ አልፎ ብዙ የሌላ እምነት ተከታዮች የሚወዱት'ና የሚለውን የሚሰሙት ሰው ሆኗል።ደግሞ ለሁሉም የሃይማኖት...
20/06/2024

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ቲክቶክ ላይ በሚለቃቸው ዳዕዋዎች የተነሳ ከሙስሊሙ አልፎ ብዙ የሌላ እምነት ተከታዮች የሚወዱት'ና የሚለውን የሚሰሙት ሰው ሆኗል።

ደግሞ ለሁሉም የሃይማኖት ተከታዬች የሚሆኑ መልዕክቶችን በሚያምር መልኩ ማስተላለፍ'ና መግለፅ በሚገባ ይችላል።

ከማስተማሩ በተጨማሪ ኡስታዝ መሬት ላይም የተለያዩ የበጎ ስራዎች በመስራት ይታወቃል። የሆነ ጊዜ ራሱ ኡስታዝ ኑሩ 'ሰዎችን ስንረዳ ተረጂዎችን በማያሸማቅ መልኩ መሆን አለበት...' ምናምን ሲል ሰምቼው ነበር። መልዕክቱም ለብዙ ሰዎች ተዳርሷል !

ታዲያ ይሄ መልዕክቶቹ በብዙዎች የሚሰማ ኡስታዝ ፣ ለሌሎች እንረዳለን ለሚሉ ሰዎችም አርአያ ሊሆን የሚገባው ሰው ለምን በዚህ ልክ ወርዶ ተረጂዎችን በሚያሸማቅ መልኩ ለአረፋ ስጋ ሲያከፋፍል ፎቶ መነሳት እንደፈለገ ሊገባኝ አልቻለም !? የዚህ አይነት ተረጂዎችን ክብራቸው'ና ማንነታቸውን በሚነካ መልኩ ፎቶ እያነሱ መርዳት እንኳን አንድ ኡስታዝ ላይ አይተን ማንኛውም ሰው ሲያረገው ልንቃወመው የሚገባ ነገር ነው !

ከታች ፎቶ ላይ አንድ የበሬ እግር ሲቀበል የምናየው ሰው እናት አባት ፣ ከዛም ሲያልፍ ሚስት'ና ልጆች ይኖሩታል። ዘመድ ጎረቤት አለው። ትላንት ኖሮት ዛሬ ያጣ ሰውም ሊሆን ይችላል። ታዲያ የዚህን ሰው ስጋ ሲቀበል የሚያሳይ ያዩ የቅርቡ ሰዎች ስለሚደርስባቸው ጫና እንዴት ኡስታዝ ኑሩ መረዳት ከበደው ? ሌሎች ህፃናትስ የዚህን ሰው ልጆች ለማብሸቅ ይሄ ፎቶ ቢጠቀሙበት ለሚደርስባቸው የስነልቦና ጉዳት ተጠያቂው ማን ነው ? አባታቸው ? ድህነታቸው ወይስ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ?

ሴቶቹም እንደዛው። የሚኖሩበት ሰፈር ድህነታቸው ፣ ማጣታቸው እንዳይታወቅ ቢሆንስ ወደዚህ የእርዳታ ድርጅት የመጡት ? በዚህ ልክ ክብራቸው ተቀምቶ የሚሰጣቸው አንድ'ና ሁለት ኪሎ ስጋ ሲያልቅ ይሄ ፎቶ ግን ለዘላለም አብሯቸው ይኖራል። ነገ ድህነትን ቢያመልጡ በዚህ ፎቶ የማይብሰለሰሉ'ና የማይቆጩ ይመስልሃል ?

ሁሌ እንደዚህ አይነት የሞራል ጥያቄ ሲነሳ 'ለሰጪዎቹ እርዳታው መድረሱን ለማሳየት ነው...' ምናምን የሚል የተለመደ መከላከያ አለ። ሰጪው የተገዙ በሬዎችን'ና ደረሰኝ ማየቱ በቂ ነው። ከዛ ባለፈ ባረደው በሬ ልክ 'የሰዎች ክብር አብሮ ሲገፈፍም በፎቶ ማየት እፈልጋለሁ...''ካለ ለእሱ ብቻ መላክ ይቻላል። ከዛ ባለፈ ግን እንደዚህ አይነት ፎቶ ፣ ሊያውም በዓል በደረሰ ቁጥር ለምሳ የሚሆን ስጋ እየሰጡ ተረጂዎችን ፎቶ ማንሳት ነውር ነው ! ይሄ ተግባር በአንድ የሃይማኖት አባት ሲደረግ ደግሞ ከነውርም ያልፋል ! ሌሎች ሰዎች 'እንኳን እኛ እነ ኡስታዝ እከሌስ ያደርጉት የለ እንዴ ?' ብለው የዚህ አይነት ተግባርን እንዲለማመዱት በር ይከፍታል !

(C) ሙስተጃብ ነኝ

እንደዚህ አይነት አዋ ራጅ ስብእናን የሚጎዱ  እርዳታዎች ባይሰጡ ይሻላል ለዛውም ቋሚ ያልሆነ ተበልቶ ለሚታራ እርዳታ ሰዎችን በዚህ ልክ ማዋረድ ተገቢ አይደለም እነዚህ ፎቶዎች ፋይል ሆነው እ...
20/06/2024

እንደዚህ አይነት አዋ ራጅ ስብእናን የሚጎዱ እርዳታዎች ባይሰጡ ይሻላል ለዛውም ቋሚ ያልሆነ ተበልቶ ለሚታራ እርዳታ ሰዎችን በዚህ ልክ ማዋረድ ተገቢ አይደለም

እነዚህ ፎቶዎች ፋይል ሆነው እድሜ ልክ የሚቀመጡ ናቸው አንድ አጥንት ሰጥተው በዚህ ልክ መጀነነ ተገቢ አይደለም

ፎቶ የግድ አስፈላጊ ከሆነ በዚህ ልክ ሳያዋርዱ ከጀርባ በኩል ወይም ፊት ሸፍኖ ይሁን
(C) Maulana Ramzi

Address


Telephone

+251936289629

Website

http://tiktok.com/@jibril_tube, https://www.youtube.com/channel/UCLkOv3Zuz5-P1qXmAxSy

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share