Ethiopian Verified News

Ethiopian Verified News We bring you information from verified sources

 #ነዳጅ : ከትላንትና ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ ላይ 10 ብር ገደማ ጭማሪ ተደርጎ በ122 ብር ከ53 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።አንድ ሊትር ናፍጣ ደግሞ 8 ብር...
09/05/2025

#ነዳጅ : ከትላንትና ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ ላይ 10 ብር ገደማ ጭማሪ ተደርጎ በ122 ብር ከ53 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።

አንድ ሊትር ናፍጣ ደግሞ 8 ብር ከ56 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበት 116 ብር ከ49 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

" ግንቦት 15/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ እንጠይቃለን " -  ባለሥልጣን መ/ቤቱየትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት ከግንቦት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋ...
09/05/2025

" ግንቦት 15/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ እንጠይቃለን " - ባለሥልጣን መ/ቤቱ

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት ከግንቦት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ እንደሚጠይቅ አሳውቋል።

የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልጉ የባለሥልጣኑ ተገልጋዮች የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር ሊኖራችሁ ይገባል ተብሏል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ኢትዮ ቴሌኮም "ዘመን ገበያ" የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ አስጀመረኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል የግብይት ሥርዓትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል  "ዘመን ገበያ" የተሰኘ የዲጂታል ...
09/05/2025

ኢትዮ ቴሌኮም "ዘመን ገበያ" የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል የግብይት ሥርዓትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል "ዘመን ገበያ" የተሰኘ የዲጂታል ገበያ በይፋ አስጀመረ።

ዘመን ገበያ ንግድን በማቀላጠፍና ከአነስተኛ ንግድ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በማገናኘት፣ የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) እንዲያድግ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ዘመን ገበያ ለነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ዕደ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና ለንግድ ድርጅቶች ሰፊ የገበያ ተደራሽነት፣ የስራ ማስኬጃ ወጪ በመቀነስ እና ምርቶችን በስፋት በአንድ መስመር ማሳየት እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚችሉበት መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ በከተሞችና በገጠር ያሉ ሸማቾች ሰፊ የምርት እና አገልግሎት አማራጭ እንዲኖራቸው፣ ምቹና ተደራሽ አገልግሎት ለማግኘት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ የዲጂታል ክፍያ አማራጭ አገልግሎት እንዲያገኙም የሚያስችል ነው ተብሏል።

ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት ለመስራት ኩባንያው ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከ42 በላይ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች እና ሎጀስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። EBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

እስራኤል በየመን ዋና አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት ሰነዘረችየእስራኤል መከላከያ ኃይል የየመን ዋና አውሮፕላን ማረፊያ በሆነው ሰነዓ አየር ማረፊያ ላይ የዓየር ጥቃት የፈጸመ ሲሆን፤ በጥቃቱ የሶስ...
08/05/2025

እስራኤል በየመን ዋና አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት ሰነዘረች

የእስራኤል መከላከያ ኃይል የየመን ዋና አውሮፕላን ማረፊያ በሆነው ሰነዓ አየር ማረፊያ ላይ የዓየር ጥቃት የፈጸመ ሲሆን፤ በጥቃቱ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

የዓየር መንገዱ ዋና ዳይሬክተር ካሊድ አል-ሼፍ “ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ነው“ ሲሉ ጥቃቱን ገልፀው፤ በጥቃቱ ሳቢያ ማንኛውም የበረራ አገልግሎት መቋረጡን ተናግረዋል።

በአየር መንገዱ ውስጥ የሚገኘው አዳራሽ፣ የማኮብኮቢያ እና የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም በሃውቲ ቁጥጥር ስር ነው ተብሎ የሚገመተው የወታደራዊ አውሮፕላኖች ማረፊያ ስፍራ ዒላማ መደረጉን አያይዘው ጠቅሰዋል።

የእስራኤል ጦር በበኩሉ "አየር መንገዱ የሃውቲ አማፂ ቡድን የጦር መሳሪያዎችን እና ኦፕሬተሮችን ለማዘዋወር የሚጠቀምበት ማዕከል ነበር" ሲል አስታውቋል።

እንዲሁም “ከቀናት በፊት የፀደቀው የጋዛ ሰርጥን የመቆጣጠር እቅድ ሲሳካ የመን ለፍልስጤም የምታደርገው ጥቃት ያበቃል” ብሏል።

በየመን የሚደገፈው የሀውቲ አማፂ ቡድን በእስራኤል አየር ማረፊያ ቤን ጉሪዮን ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ሀገሪቱ ያለፉትን ሁለት ቀናት የአፀፋ ምላሽ እየሰጠች ትገኛለች ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ትራምፕ በፍቃደኝነት አሜሪካን ለቀው ለሚወጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች የ1 ሺህ ዶላር ማበረታቻ አቀረቡየአሜሪካ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች አሜሪካን ለቀው ለመውጣት...
07/05/2025

ትራምፕ በፍቃደኝነት አሜሪካን ለቀው ለሚወጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች የ1 ሺህ ዶላር ማበረታቻ አቀረቡ

የአሜሪካ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች አሜሪካን ለቀው ለመውጣት ከወሰኑ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚሰጥ እና የጉዞ ክፍያቸውን እንደሚሸፍን አስታውቋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ጉዳዩ ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ ህገወጥ ስደተኞች የቀረበላቸውን አማራጭ የሚቀበሉ ከሆነ አንድ ቀን ወደ አሜሪካ የሚመለሱበት ህጋዊ መንገድ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተናግረዋል።

እንዲሁም የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት (ዲ.ኤች.ኤስ) ፀሃፊ ክሪስቲ ኖም፤ ከአሜሪካ በራስ ፈቃድ መውጣት ከእስር ለመዳን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወጪ ቆጣቢው መንገድ ነው ብለዋል።

የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት አክሎም፤ እቅዱ የገንዘብ ወጪን እንደሚቀንስ ገልፆ፤ እስካሁን ስደተኞችን ለመያዝ፣ ለማሰር እና ከሀገር ለማስወጣት በአማካይ ከ17 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ እንደተደረገ አስታውቋል።

በእቅዱ መሰረት የመጀመሪያው ሕገወጥ ስደተኛ ከቺካጎ ወደ ሆንዱራስ ለመብረር አማራጩን እንደተቀበለ ዲፓርትመንቱ መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የጤና ባለሙያዎች ላቀረቡት ጥያቄ መንግስት በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የ  #ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር አሳሰበየጤና ባለሙያዎች ከደሞዝ ጭማሪ እና ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ ለሚያነሱት ጥ...
07/05/2025

የጤና ባለሙያዎች ላቀረቡት ጥያቄ መንግስት በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የ #ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር አሳሰበ

የጤና ባለሙያዎች ከደሞዝ ጭማሪ እና ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ ለሚያነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የቅድመ ስራ ማቆም አድማ ሰልፎችን በመላው ኢትዮጵያ እያካሄዱ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር፤ መንግስት ለጥያቄያቸው በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ። የባለሙያዎቹ ንቅናቄም "አገሪቱን እና ማህበረሰቡን በማይጎዳ መልኩ" መከናወን እንዳለበት አፅንዖት ሰጥቷል።

ማህበሩ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ፤ "በጤና ባለሙያዎች የተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸው መንግስት አፋጣኝ መፍትሄዎችን መስጠት አለበት" ብሏል። “መንግስት በጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ለሀገሪቱ ችግር ከመፍጠሩ በፊት ተገቢውን ትኩረት እና ምላሽ እንዲሰጥ” አጥብቆ አሳስቧል።

ማህበሩ እነዚህን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እና ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተገቢው ህጋዊ መንገድ ማቅረቡን ገልጾ፤ ይሁን እንጂ "የጤና ባለሙያዎች የሚያነሱት ጥያቄ በአፋጣኝና በተገቢው መንገድ ምላሽ ስላልተሰጠው የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ መንገዶች መብታቸውን እየጠየቁ ነው" ሲል ገልጿል። Addis Standard

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን እና ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች ላይ ሶስት ክሶች ተመሰረተበኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥንና እህት ኩባንያው ላይ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል ...
07/05/2025

ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን እና ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች ላይ ሶስት ክሶች ተመሰረተ

በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥንና እህት ኩባንያው ላይ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል ክስ ሲመሰረት፤ መዓዛ መሓመድና ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትናንት መጋቢት 28/2017 ዓ/ም ክስ የመሰረተባቸው ግለሰቦች በአሜሪካና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ መዓዛ መሐመድ፤ ተስፋዬ ወልደሰላሴ፣ ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን ኃ.የተ.የግ/ማህበርና እህት ኩባንያው ሲልቨር ስፕሪንግ ፕሮዳክሽንና ፕሮሞሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር፣ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ አመራሮችንና ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ 16 ግለሰቦች ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች ለጊዜው በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ሌሎች ግብራበሮቻቸው ጋር በመሆን “የፖለቲካ ዓላማን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ በህገ መንግስት የተቋቋመውን የፌደራልና የ #አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን በኃይል በማስወገድ ስልጣን ለመያዝ፤ ይህ ካልተሳካ ደግሞ መንግስትን በሀይል በማስገደድ ለድርድር እንዲቀመጥ ማድረግ የሚል ዓላማን በመያዝ መንቀሳቀሳቸው” በክሱ ተመላክቷል።Addis Standard

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

“ ነገ ከ40 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ” - ቤተሰቦቻቸውበማይናማር ታግተው የቆዩና መንግስት ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው ሲማጸኑ ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ40 በላይ...
07/05/2025

“ ነገ ከ40 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ” - ቤተሰቦቻቸው

በማይናማር ታግተው የቆዩና መንግስት ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው ሲማጸኑ ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት ነገ ረቡዕ እንደሚመለሱ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ነገ ይመለሳሉ ተብለው የሚጠበቁት ልጆች ዲኬቢኤና ቢጂኤፍ ካምፓች የነበሩ፣ በቅርቡ ማይዋዲ ተጉዘው የነበሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

ከማይዋዲ ወደ ባንኮክ የነበራቸውን የትራንስፓርት ወጪ የኢትዮጵያ መንግስት፣ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡበትም የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤንጂኦዎች የበረራ ወጪያቸውን እንደሸፈኑላቸው ቤተሰቦቻቸው ነግረውናል።

ሰሞኑንም ሌሎች ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል።

ታግተው ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ700 በላይ የሚሆኑት የተወሰነ መስፈርት በማሟላታቸው መንግስት እንዲመልሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሚልኩት መልዕክት ደጋግመው ሲማጸኑ ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከ20 ቀናት በፊት፣ “ በቀጣይ 10 ቀናት ወደ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው ” ብለው ነበር።

በወቅቱ፣ ወደ 130 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታውሰው፣ ወደ 700 ኢትዮጵያውንን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነበር የጠቆሙት።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

" በ9 ወራት ብቻ 102,604 ሰዎች የአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና ተሰጥቷል " - ሆስፒታሉበዘጠኝ ወራት ብቻ 102,604 ሰዎች የአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና መስጠቱን...
06/05/2025

" በ9 ወራት ብቻ 102,604 ሰዎች የአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና ተሰጥቷል " - ሆስፒታሉ

በዘጠኝ ወራት ብቻ 102,604 ሰዎች የአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና መስጠቱን አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ሆስፒታሉ ከእነዚህ ታካሚዎች መካከል 98, 803 የሚሆኑት በተመላላሽ የህክምና አገልግሎት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም፣ ለ1, 421 ለሚሆኑ ህሙማን በአስተኝቶ የአዕምሮ ህክምና፣ በድንገተኛ የአዕምሮ ህክምና ደግሞ ለ2,380 ሰዎች አገልግሎት ተሰጥቷል።

ይህም በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለ124,800 ዜጎች በአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ካቀደው ውስጥ መሆኑን ሆስፓታሉ ገልጿል።

በ9 ወራት ውስጥ 371 የሚሆኑት የህፃናት የአእምሮ፣ 597 ደግሞ የሱስ ህክምናዎች እንዳገኙም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የፎረንሲክ ህክምናን በተመለከተም፣ "የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ተመርማሪዎች በተመላላሽና በተኝቶ 570 ለሚሆኑት አገልግሎቱ ተሰጥቷል" ተብሏል።

በሌላ በኩል፥ በሆስፒታሉ አማካኝ የአስተኝቶ የቆይታ ግዜ በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው 36 ቀን በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወራት ወደ 33 ቀን፣ አልጋ የመያዝ ምጣኔንም 84% ማድረስ እንደተቻለ ሆስፒታሉ ገልጿል።

የዕለቱ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!Follow our page… share our storie...
06/05/2025

የዕለቱ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

" ትእግስትና ማስተዋል ይቅደም " - ፖሊስበትግራይ ክልል፤ በእንደርታ ወረዳ መሰረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር መንጨልፎ በተባለ መንደር በጥበቃ ሙያ የተሰማራ ግለሰብ በሚሰራበት ቦታ ከተዋወቃት ሴ...
05/05/2025

" ትእግስትና ማስተዋል ይቅደም " - ፖሊስ

በትግራይ ክልል፤ በእንደርታ ወረዳ መሰረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር መንጨልፎ በተባለ መንደር በጥበቃ ሙያ የተሰማራ ግለሰብ በሚሰራበት ቦታ ከተዋወቃት ሴት አንድ ልጅ ይወልዳል።

የተወለደው ልጅ በተለይም ጀሮው አከባቢው አብሮት የጥበቃ ሙያ ከሚሰራው የስራ አጋሩ ጋር የመመሳሰል ጉደይ ደጋግሞ ይከነክነዋል።

ይባስ ብሎ ደግሞ ልጅ የወለደችለት ሴት በልጁ መመሳሰል የጠረጠረውን የስራ ባልደርባ " ሊደፍረኝ ሞክሮ ነበር " ትነግረዋለች።

ይህን የነገረችውን ቂምና ነገር ቋጥሮ የስራ ባልደረባውን በአህልህና በብስጭት ደግጋሞ በገጀራ በመውጋት መግደሉ ለፓሊስ ቃሉ እንደሰጠ ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የዞኑ ፓሊስ ግድያ ፈፃሚው ከህብረተሰብ ጥቆማ በመነሳት ባደረገው ክትትል በቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሎታል።

" ካንተ ነው የወለድኩት ያለችኝ ልጅ በተለይ ጆሮው አካባቢ ከኔ ሳይሆን አብሮኝ ከሚሰራ ሰው ስለሚመስል አባቱ እሱ ነው ብዬ በመጠርጠሬ በገጀራ ደጋግሜ በመውጋት ገድየዋለሁ " ሲል ቃል መስጠቱ ፓሊስ አስታውቀዋል።

" በራስ አእምሮ ያለን ጥርጣሬ እንደ ፍፁም እውነት በመቆጠር ጉዳዩ በህክምና መረጃና ማስረጃ ሳይረጋገጥ በሌሎች ሰዎች ላይ ይህን መሰል የጭካኔ እርምጃ መውሰድ ለማያባራ የህሊና ፀፀት ይዳርጋል " ያለው ፓሊስ " ትእግስትና ማስተዋል ይቅደም " በማለት መክሯል።TIKVAHETHIOPIA

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የብራዚል ፖሊስ በአሜሪካዊቷ ድምጻዊት ሌዲ ጋጋ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የቦምብ ጥቃት አከሸፈበብራዚል የሪዮ ዲ ጄኔሮ የሲቪል ፖሊስ እና ፍትህ ሚኒስቴር በጋራ በቤት ውስጥ የተሰራ ተቀጣጣይ ፈንጂ...
05/05/2025

የብራዚል ፖሊስ በአሜሪካዊቷ ድምጻዊት ሌዲ ጋጋ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የቦምብ ጥቃት አከሸፈ

በብራዚል የሪዮ ዲ ጄኔሮ የሲቪል ፖሊስ እና ፍትህ ሚኒስቴር በጋራ በቤት ውስጥ የተሰራ ተቀጣጣይ ፈንጂን በመጠቀም ጥቃት ለማድረስ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ዕውቅና ለማግኘት አስበው የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገለፁ።

የድምጻዊት ሌዲ ጋጋ ቡድን ስለጥቃቱ ከሙዚቃ ዝግጅቱ በኋላ ማለዳ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን መስማታቸውን ገልጸዋል።

በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ ካፓካባና የባሕር ዳርቻ የሌዲ ጋጋን የሙዚቃ ድግስ በነጻ ለመታደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ጥቃቱን ለመፈፀም ያሰበው ቡድን በሕጻናት፣ አዋቂዎች እና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ላይ የጥላቻ ንግግር ሲያሰራጭ ነበር ብሏል።

ጥቃቱን አቀነባብሯል በሚል በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ በሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል ደቡባዊ ግዛት ሕገወጥ የጦር መሳርያ ይዞ በመገኘት በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።

ታዳጊው ደግሞ በሪዮ ሕጻናት የሚታዩበት የወሲብ ፊልም በማከማቸት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ያውቃል።

ጥቃቱን ለመፈጸም ያቀዱት ግለሰቦች ታዳጊዎችን አክራሪ እንዲሆኑ በመቀስቀስ እንዲሁም "የአንድ ቡድን አባል መሆናቸውን ለመግለጽ እና ሌሎች ወጣቶችን ለማነሳሳት" በሚል ራሳቸውን እንዲጎዱ እንዲሁም ጸብ ቀስቃሽ ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ተወንጅለዋል።

የሌዲ ጋጋ ቃል አቀባይ ለ ዘ ሆሊውድ ዘጋቢ "ሊደርስ ነበር ስለተባለው ጥቃት የሰማነው ዛሬ ማለዳ ከመገናኛ ብዙኃን ነው።

ከትርዒቱ አስቀድሞም ሆነ በሚታይበት ወቅት ምንም ዓይነት የታወቀ የደህንነት ስጋት አልነበረም።

እንዲሁም ለሌዲ ጋጋ ከፖሊስም ሆነ ከባለስልጣናት ሊኖር ስለሚችል ጥቃት የደረሰ መረጃ የለም" ብሏል።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

Address

Ghana Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Verified News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share