28/04/2025
✍️ በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች የአለም ክብረ ወሰኖች በተከታታይ እየተሰበሩ ይገኛሉ:: ይህንን ተከትሎ ቴክኖሎጂ የአትሌቶችን ብቃት በማሳደግ ረገድ ስላለው ሚና የሚነሱ ክርክሮች እየበዙ መጥተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ዋና ዋና አስተሳሰቦች የሚንፀባረቁ ሲሆን: የመጀመሪያዎቹ ለውጥ የማይቀር የተፈጥሮ ሂደት ነው ብለው የሚያምኑ እና አነሰም በዛም እያንዳንዱ ትውልድ ከቀደመው ጋር ሲነፃጸር የተሻለ ተጠቃሚ ነው በዚህም ምክንያት የቴክኖሎጂ ተፅእኖ ደረጃን በትክክል ለመለካት አስቸጋሪ ነው ብለው ያምናሉ።
ሌላኛው አስተሳሰብ በበኩሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተመዘገቡት መመንደጎች (በመሮጫ ጫማ: በስልጠና: ህክምናና ህጋዊ እንክብሎች ወዘተ...) ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን በመጥቀስ የዛሬዎቹ አትሌቶች ካለፉት ዘመናት መሰሎቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ የላቀ ጥቅም አስገኝቶላቸዋል ብለው የሚያምኑት ናቸው:: እንዲያውም በዚህ ጎራ የሚመደቡ አንዳንዶች: የዘመኑ አትሌቶችን ጥረት እስከማጥላላትም ይደርሳሉ።
የሚከተለው ቀረጻም አትሌት ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሊምፒክ ማራቶን ማሸነፉን ተከትሎ በሱፐር ስፖርት ስቱዲዮ ልዩ የኦሊምፒክ ሽፋን በተመሳሳይ ርእሰ ጉዳይ ላይ የተደረገውን ውይይት ያሳያል።
በፓናሉ ላይ የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ማራቶን ተወዳዳሪው ሄንድሪክ ራማላ፣ የ2004 እና 2008 ኦሊምፒያኗ ጄራልዲን ፒላይ ከደቡብ አፍሪካ እና ሃይለእግዚአብሔር አድሃኖም ከኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ሆነዋል።
እርስዎ ቴክኖሎጂ በዘመናዊ አትሌቶች ውጤታማነት ላይ እያሳደረ ስለሚገኘው ተፅእኖ ምን አስተያየት አለዎት?
©️ሱፐር ስፖርት
✍️ As world records continue to fall across various athletics events around the globe, debates about the role of technology in enhancing athlete performance are becoming more frequent.
There are two main schools of thought on this issue. One believes that change is inevitable, and that each generation naturally holds an advantage over its predecessors, making it difficult to fairly measure the level of technological influence.
The other argues that recent advancements in technology are unprecedented, giving today's athletes a significantly greater advantage compared to those of previous eras. Some even go so far as to discredit the efforts of contemporary athletes.
The following footage captures a discussion from SuperSport’s special Olympic coverage, following Tamirat Tola’s victory at the Paris Olympic Marathon. The panel features four-time Olympic marathoner Hendrick Ramaala, 2004 and 2008 Olympian Geraldine Pillay from South Africa, and Haileegziabher Adhanom from Ethiopia.
What are your thoughts on how technology is influencing the performance of modern-day athletes?
©️SuperSport