EthioWorld

EthioWorld ETHIOWORLD:Is news channel's,entertainment ,sport and others....
Like,share,comment ETHIOWORLD

19/06/2024

የ21 አመቷ ቢሊሴ አለሙ የልብ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋታል። ሁለቱም የቢሊሴ የልብ ቫልቮች የተበላሹ ናቸው መተካት አለባቸው። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ህይወቷን ለማትረፍ በተቻ...

************አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ **********የ 21ዓመቷ ወጣት ቢሊሴ አለሙ የልብ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋታል።የቢሊሴ ሁለቱም የልብ ቫልቮች አይሰሩም እና መተካት አለባቸው።የህክምና...
09/06/2024

************አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ **********

የ 21ዓመቷ ወጣት ቢሊሴ አለሙ የልብ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋታል።የቢሊሴ ሁለቱም የልብ ቫልቮች አይሰሩም እና መተካት አለባቸው።የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ህይወቷን ለማዳን የልብ ቀዶ ጥገናውን በፍጥነት ማድረግ አለባት።
ህይወቷን ሊታደግ የምችለውን አስፈላጊውን ቀዶ ጥገና ለማድረግ 950,000 ብር ማግኘት እንዳለባት ተነግሮአታል።
የእርስዎ ልገሳ አስተዋፅኦ በቢሊሴ ህይወት ላይ ትልቅ ለውጥ የመጣል።
ስለዚህም እባካችሁን እህታችንን ታደጉልን።እናመሰግናለን!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000379074808 BILISE ALEMU TEBELU

Share share share

********** URGENT CALL FOR HELP **********21-year-old Bilise Alemu needs heart surgery. Both of Bilise's heart valves ar...
09/06/2024

********** URGENT CALL FOR HELP **********

21-year-old Bilise Alemu needs heart surgery. Both of Bilise's heart valves are malfunctioning and need to be replaced. According to medical experts, she needs to undergo heart surgery as soon as possible to save her life.
She was told that she would have to get 950,000 Birr to undergo the necessary surgery that could save her life.
Your donation will make a big difference in Billie's life.
So please save our sister. Thank you!

Commercial Bank of Ethiopia (CBE)
1000379074808 BILISE ALEMU TEBELU

Share share share

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን  ከአለም ዋንጫ ዉጭ ሆነ+++++++++++++++++++++++++++++++++++ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ለምታስተናግደዉ ከ17 አመት በታች የሴቶች...
19/05/2024

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአለም ዋንጫ ዉጭ ሆነ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++

ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ለምታስተናግደዉ ከ17 አመት በታች የሴቶች የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዉን እያደረገ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዉድድሩ ዉጭ ሆኗል፡፡

ዛሬ የመልስ ጨዋታዉን ከኬንያ አቻዉ ጋር በናይሮቢ ያደረገዉ ብሄራዊ ቡድኑ 3ለ0 በሆነ ዉጤት ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

የኬኒያን የማሸነፊያ ግቦች ኤልዛቤት ኦቻካ፤ሼልማ አዉር እና ሎርና ፌዝ አስቆጥረዋል፡፡

በመጀመሪያዉ ጨዋታ 0ለ0 መለያየታቸዉ የሚታወስ ሲሆን ኬኒያ በድምር ዉጤት 3ለ0 በማሸነፍ ለመጨረሻዉ ምዕራፍ ደርሳለች፡፡

ኬኒያ በቀጣይ ጅቡቲን ካሸነፈችዉ ቡሩንዲ ጋር የምትጫወት ሲሆን አሸናፊዉ ሀገር ከ17 አመት በታች የሴቶች አለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለዉ ከሚካፈሉ ሀገራት መካከል ይሆናል፡፡

According to the report of Tehran Times, a military helicopter crashed in East Azerbaijan. They are helicopters and the ...
19/05/2024

According to the report of Tehran Times, a military helicopter crashed in East Azerbaijan. They are helicopters and the two landed at their destination. On the other hand, there are speculations that "Iranian President Ibrahim Raisi, Foreign Minister Amir Abdollahian, Imam of Ayatollah Al Hashem Mosque and Governor of East Azerbaijan Province Malek Rahmati were not on board the crashed helicopter." However, in the crashed helicopter. The Times of India reports that there is no clear information about who was on board and that there is no explanation of the cause of the helicopter accident. President Raisi was in East Azerbaijan province today to inaugurate the Qiz Qalasi Dam and was on his way back to Tehran.

 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ - የ25ኛ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ- የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ደረጃ- የ25ኛ ሳምንት ውጤቶች- የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር (ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት ወደፊት ይገለፃ...
16/05/2024


የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

- የ25ኛ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ
- የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ደረጃ
- የ25ኛ ሳምንት ውጤቶች
- የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር (ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት ወደፊት ይገለፃል)

በባህር ዳር ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት ለማሳደግ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ  ተገለጸ+++++++++++++++++++++++++++++++++++ባህር ዳር፤ ግንቦት 8/2016(ethio...
16/05/2024

በባህር ዳር ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት ለማሳደግ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++

ባህር ዳር፤ ግንቦት 8/2016(ethioworld)፦ በባህር ዳር ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ የማምረት አቅም ለማሳደግ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ገለጹ። “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት“ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

የከተማው አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በዚሁ ወቅት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለምርታማነት እድገት ክፍተት የፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የተጠናከረ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም የብድር፣ የሃይልና ሌሎችንም የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን በመፍታት አምራች ኢንዱስትሪዎች የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ኢንዱስትሪዎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የተጀመረው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እንዲሳካ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ አስተዳደሩ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የሚሰሩበት መሬት ከተላለፈላቸው ባለሃብቶች ውስጥ 197 ወደ ማምረት መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

እንዲሁም ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ ለመግባት የተዘጋጁ 217 ባለሃብቶች መኖራቸውን ያመለከቱት አቶ ጎሹ ፤ ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በአማራ ክልል ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ናቸው።

አምራች ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋትም በሦስት ሺህ 300 ሄክታር መሬት ላይ 28 የኢንዱስትሪ መንደሮችን በማልማት ለስራ ምቹ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፍ ችግሮችን በመፍታት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የ “የኢትዮጵያ ታምርት” አገራዊ የንቅናቄ ግቡን እንዲመታ ክልሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመደገፍ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በክልሉ በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉ የንቅናቄ መድረኮች ተስፋ ሰጪ ለውጦች መምጣታቸውን አብራርተዋል።

በውይይቱ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ የአመራር አባላት ፣ ባለሀቶችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ ባለሃብቶቹ የኢንዱስትሪ ምርቶቻቸውን የሚመለከት ዝግጅት አቅርበዋል።

 #ኤለን-መስክ በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን+++++++++++++++++++++በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ው...
16/05/2024

#ኤለን-መስክ
በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን
+++++++++++++++++++++

በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ውስጥ ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ እንደሚገነባ የስፔስ ኤክስ መስራች ኤለን መስክ ገልጿል።

የማርስ ከተማ ግንባታን እውን ለማድረግ ስፔስ ኤክስ በርካታ የቅኝት ሳተላይቶችን በቅርቡ እንደሚልክ ማስታወቁን የዴይሊ ስታር ዘገባ ያመላክታል።

"በጥቂት አመታት ውስጥ ሰዎችን በማርስ ላይ የማስፈር ዕቅዳችንን ዕውን እናደርጋለን" ብሏል የ52 ዓመቱ ቢሊየነር ኤለን መስክ።

"ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን፤ ከበረታን እስከ 20 ዓመት፣ በእርግጠኝነት ግን በ30 ዓመት ውስጥ ዘመናዊ ከተማ በማርስ ላይ እንገነባለን" ብሏል ኤለን መስክ።

እ.አ.አ 2002 የተመሰረተው ስፔስኤክስ ወደ አለማቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ መንኮራኩር እና ጠፈርተኞችን የላከ የግል ኩባንያ ነው።

Russian President Putin has accused the West of risking a global conflict and said no one would be allowed to threaten t...
09/05/2024

Russian President Putin has accused the West of risking a global conflict and said no one would be allowed to threaten the world’s biggest nuclear power as Russia marked the Soviet Union’s victory over N**i Germany in WW2.

 የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና  የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በ  #ኢትዮጵያታምርት ንቅናቄ  ያገኘናቸውን ውጤቶች ይበልጥ ማስቀጠል አለብን። አምራች ኢንደስትሪዎችም በግብዓት፣ በ...
09/05/2024


የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በ #ኢትዮጵያታምርት ንቅናቄ ያገኘናቸውን ውጤቶች ይበልጥ ማስቀጠል አለብን። አምራች ኢንደስትሪዎችም በግብዓት፣ በኢነርጂ፣ በገበያ እና በሰው ሀይል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተሻለ ወደ ውጤት ለመለወጥ መትጋት ይኖርባቸዋል።

We must uphold the achievements of the movement by championing local producers and utilising domestic products. Furthermore, manufacturing industries should harness Ethiopia's vast resources, energy, markets, and human capital to maximise outcomes and drive sustainable growth.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioWorld posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EthioWorld:

Share