
16/08/2025
የውሃ ማማው ጉና ተራራ !
▭▭▭▭
የጉና ተራራ ከደብረታቦር ከተማ ደቡብ ምስራቅ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ የተራራ ሰንሰለት ሲሆን አካባቢው በዋናነት በምዕራብና በሰሜን ከፋርጣና ጉና በጌምድር ወረዳ፣ከምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ከላይ ጋይንት ወረዳ፣ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ደግሞ ከእስቴ ወረዳ ጋር ይዋሰናል።
የተራራ ሰንሰለቱ ከባህር ወለል በላይ በአማካኝ ከ3 ሺ 400 ሜትር እስከ 4 ሺ 231 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ከውርጭና ውርጭ ቀመስ ከሆኑ ሥርዓተ ምህዳሮች ውስጥ ይመደባል።
የበርካታ ብዝኃ-ህይወት ሀብት መገኛና የውሃ ማማ የሆነ ረግረጋማ ቦታዎችን አቅፎ የያዘው የጉና ተራራ፦ ጣና ሐይቅን የሚመግቡትን ጉማራና ርብ ጨምሮ ከ40 በላይ ወንዞች መፍለቂያ የሆነው ጉና ነብስን የሚያረካ ውኃ የሚያመነጩ ከ77 በላይ ንፁህ ምንጮችም መፍለቂያ ነው።
ጉና ዓመቱን በአብዛኛው በደመና ተሸፍኖ የሚውል ዙሪያውን በጓሳ ሳርና በአጫጭር የደጋና ውርጭ እፅዋቶች የተሸፈነ ትልቅ ተራራ ነው። በውስጡ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮን ጨምሮ የተለያዩ የዱር እንሰሳት ይኖሩበታል።
ጉና ከተፈጥሯዊ ማራኪ መልክዓ ምድሩ በተጨማሪ በርካታ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ የመስህብ ቦታዎች በዙሪያው ስለሚገኙ ለጉብኝትም ተመራጭ መስህብ ነው።
▭▭▭▭
መረጃው የእስቴ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።