20/10/2025
♨️አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ወደ ቡድሃ ቀርቦ ፦
“በህይወቴ በጣም ተቸግራለሁ፣ እባክህ ከዚህ ችግር ለመውጣት መፍትሄውን ንገረኝ” አለው።
ቡድሃ እንዲህ አለ፡- “አንድ እፍኝ ጨው በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምረው እና ጠጣው…” ወጣቱም እንዲሁ አደረገ።
"እንዴት ነው ጣዕሙ?" ቡድሃ ጠየቀ።ወጣቱም፦ "በጣም መጥፎ እና በጣም ጨዋማ " አለ ምራቁን እየተፋ።
ቡድሃ ፈገግ አለና “በድጋሚ አንድ እፍኝ ጨው በእጅህ ይዘህ ተከተለኝ"አለው። ሁለቱም ቀስ ብለው ወደፊት መሄድ ጀመሩ እና ጥቂት ርቀት ከተጓዙ በኋላ በጠራ እና ንፁህ በሆነ ውሃ በተሰራ ሀይቅ ፊት ለፊት ቆሙ።
“ና፣ አሁን ይህን ጨው በውሃ ውስጥ አኑረው” በማለት ቡድሃ አዘዘ። ወጣቱም እንዲሁ አደረገ።
"አሁን የዚህን ሀይቅ ውሃ ጠጣ"አለ ቡድሃ። ወጣቱ ውሃ መጠጣት ጀመረ፣ አሁንም ቡድሃ “ጣዕሙ እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ አሁንም ጨዋማ ሆኖ አገኘኸው?"ብሎ ጠየቀው።
"አይ ይህ ጣፋጭ ነው።በጣም ጥሩ ነው" አለ ወጣቱ
ቡድሃ ከወጣቱ አጠገብ ተቀምጦ እጁን ይዞ፦“የህይወት ችግር ልክ እንደ ጨው ነው፣ ብዙም ያነሰም አይደለም። በህይወት ውስጥ ያለው የችግር መጠን ተመሳሳይ ነው በትክክል ተመሳሳይ ነው።
ነገር ግን ምን ያህል ሀዘኑን ውስጣችንን መራር እንደሚያደርገው በምንቀመጥበት ዕቃ ላይ ይወሰናል።
ስለዚህ ስታዝን ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር እራስህን ትልቅ ማድረግ ነው።በብርጭቆ አትቆይ ችግር ህይወትን መራር ያደርገዋልና ፣ሐይቅ ሁን እራስህን ከችግሩ በላይ ጉዝፍ አድርግ።
🗣ኦሾ
t.me/Usefulexpression