Maze Ethiopia

Maze Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Maze Ethiopia, Addis Ababa.

17/08/2025
17/08/2025
01/07/2025
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል።ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አ...
07/02/2024

ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ፤ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል።

ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ፤ ብፅዕነታቸው ፤ " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል።

ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው ፤ " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ፤ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ ፤ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጀል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተከለከሉ‼️ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ ...
06/02/2024

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተከለከሉ‼️

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኛሉ ሲሉ መረጃ ሰጭዎቻችን አድርሰውናል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ አስታውቋል።

ካዲስኮ አደባባይ አካባቢ የትራፊክ አደጋ ደረሰአዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከካዲስኮ አደባባይ አለፍ ብሎ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ...
20/01/2024

ካዲስኮ አደባባይ አካባቢ የትራፊክ አደጋ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከካዲስኮ አደባባይ አለፍ ብሎ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

በአደጋው በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በበዓል ወቅት የትራፊክ እንቅስቃሴው ስለሚጨምር ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ መክሯል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maze Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share