ዮኒ-ሶከር Yoni-Soccer

ዮኒ-ሶከር Yoni-Soccer For the love of the game ዕለት ዕለት ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎች

✅ጆሹዋ ዘርክዚ የማን.ዩናይትድ ቆይታውን እያጤነበት እንደሆነ ዴይሊ ሜል ዘግቧል፤ከቤንጃንሚን ሴሽኮ መምጣት እና ሌሎች ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ የጨዋታ ጊዜው መገደቡ ጋር ተያይዞ እየተሰላቸ መ...
07/10/2025

✅ጆሹዋ ዘርክዚ የማን.ዩናይትድ ቆይታውን እያጤነበት እንደሆነ ዴይሊ ሜል ዘግቧል፤

ከቤንጃንሚን ሴሽኮ መምጣት እና ሌሎች ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ የጨዋታ ጊዜው መገደቡ ጋር ተያይዞ እየተሰላቸ መምጣቱን ተገልጿል፤

በመጪው ክረምት ለሚደረገው የአለም ዋንጫ ውድድር የኔዘርላንድ ስኳድ አካል መሆን የሚፈልግ ከሆነ ሰፊ የጨዋታ ማግኘት እንደሚኖርበት ተማምኗል፤

ይህንንም ተከትሎ በመጪው የጥር ዝውውር መስኮት አዲስ ነገር ሊሰማ እንደሚችል ገልጿል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅የሳምንቱ ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል፤በኤምሬቴስ በተደረገው ይህ ፍልሚያ ኤርሊንግ ሃላንድ ለሲቲ ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ ደግሞ ለአርሰናል...
21/09/2025

✅የሳምንቱ ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል፤

በኤምሬቴስ በተደረገው ይህ ፍልሚያ ኤርሊንግ ሃላንድ ለሲቲ ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ ደግሞ ለአርሰናል አስቆጥሯል፤

አርሰናል በጨዋታው ሙሉ ብልጫ መውሰድ ችሎ የነበር ቢሆንም በ9ኛ ደቂቃ ኤርሊንግ ሃላንድ ባስቆጠረው ጎል እስከ 92ኛው ደቂቃ ሲመራ ቆይቶ ነበር፤

በሳምንቱ አጋማሽ አትሌቲክ ቢልባዎ ላይ ተቀይሮ ገብቶ ጎል አስቆጥሮ የነበረው ማርቲኔሊ ዛሬም ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ 92ኛ ደቂቃ ላይ ክለቡን መታደግ ችሏል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅10:00 ላይ የተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች: #ቦርንማውዝ 0-0  #ኒውካስትል #ሰንደርላንድ 1-1  ➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8
21/09/2025

✅10:00 ላይ የተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች:

#ቦርንማውዝ 0-0 #ኒውካስትል
#ሰንደርላንድ 1-1

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ማን.ዩናይትድ አሸነፈ!ከአምስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሀ ግብሮች አንዱ የነበረው የማን.ዩናይትድ እና ቼልሲ ጨዋታ በማን.ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቋል፤አስገራሚ ክስተቶች በታዩበት ጨዋታ ማን....
20/09/2025

✅ማን.ዩናይትድ አሸነፈ!

ከአምስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሀ ግብሮች አንዱ የነበረው የማን.ዩናይትድ እና ቼልሲ ጨዋታ በማን.ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቋል፤

አስገራሚ ክስተቶች በታዩበት ጨዋታ ማን.ዩናይትድ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፤

ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ካዛሚዬሮ የማን.ዩናይትድን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ትሬቮ ቻሎባህ የቼልሲን ጎል አስቆጥሯል፤

ከሁለቱም ቡድኖች በኩል በቀይ ካርድ የተሰናበቱ ተጨዋቾች የነበሩ ሲሆን ግብ ጠባቂው ሳንቼዝ ከቼልሲ በኩል ካዛሚዬሮ ደግሞ ከዩናይትድ በኩል ቀይ የተመለከቱት ናቸው፤

ውጤቱን ተከትሎም ዩናይትድ በ7 ነጥብ ወደ 9ኛ ደረጃ ከፍ ማለት ችሏል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ማድሪድ በድል ቀጥሏል!በ5ኛው ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሀ ግብር ሪያል ማድሪድ በሜዳው ኤስፓኞልን ገጥሞ አሸንፏል፤2-0 በተጠናቀቀው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ እና ኤደር ሚሊታዎ ጎሎቹን አስቆጥረ...
20/09/2025

✅ማድሪድ በድል ቀጥሏል!

በ5ኛው ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሀ ግብር ሪያል ማድሪድ በሜዳው ኤስፓኞልን ገጥሞ አሸንፏል፤

2-0 በተጠናቀቀው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ እና ኤደር ሚሊታዎ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፤

ውጤቱን ተከትሎ ማድሪድ 5ኛ ተከታታይ የላሊጋ ድሉን አስመዝግቦ በ15 ነጥብ የላሊጋው መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፤

ኪሊያን ምባፔ የውድድር አመቱን አስደናቂ ጅማሮ የቀጠለበት ሲሆን በ6 ጨዋታዎች 7ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ፓላስ ሲያሸንፍ ቶተንሃም ነጥብ ጣለ!11:00 ላይ በተደረጉ 4 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ እና ሊድስ ድል ቀንቷቸዋል፤ክሪስታል ፓላስ ከሜዳው ውጪ ዌስትሃምን 2-...
20/09/2025

✅ፓላስ ሲያሸንፍ ቶተንሃም ነጥብ ጣለ!

11:00 ላይ በተደረጉ 4 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ እና ሊድስ ድል ቀንቷቸዋል፤

ክሪስታል ፓላስ ከሜዳው ውጪ ዌስትሃምን 2-1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ጃን ፊሊፕ ማቴታ እና ታይሪክ ሚቼል ለፓላስ ቦዌን ደግሞ ለዌስትሃሜ አስቆጥረዋል፤

ቶተንሃም በበኩሉ ወደ አሜክስ ስቴዲየም ተጉዞ ከብራይተን ጋር 2-2 ሲለያይ ያንኩባ ሚንቴ እና አያሪ ለብራይተን ሪቻርሊሰን እና የብራይተኑ ቫን ሄካ ለቶተንሃም አስቆጥረዋል፤

ኖቲንግሃም ከሜዳው ውጪ በርንሌይን ገጥሞ 1-1 የተለያየ ሲሆን ኒኮ ዊሊያምስ ለኖቲንግሃም ጄይደን አንቶኒ ደግሞ ለበርንሌይ አስቆጥረዋል፤

አዲስ አዳጊው ሊድስ በሞሌኒዩ ስቴዲየም ዎልቭስን 3-1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ካልቨርት ሌዊን፣ አንቶን ስታች እና ኖሃ ኦካፎር ለሊድስ ላዲስላቭ ክሬቺች ደግሞ ለዎልቭስ አስቆጥረዋል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ባየር ሙኒክ መሪነቱን አጠናከረ!በ4ኛ ሳምንት የቡንደስ ሊጋው መርሀ ግብር ባየር ሙኒክ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሆፈኒየምን አሸንፏል፤ሃሪ ኬን በደመቀበት ጨዋታ ሙኒክ 4-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ች...
20/09/2025

✅ባየር ሙኒክ መሪነቱን አጠናከረ!

በ4ኛ ሳምንት የቡንደስ ሊጋው መርሀ ግብር ባየር ሙኒክ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሆፈኒየምን አሸንፏል፤

ሃሪ ኬን በደመቀበት ጨዋታ ሙኒክ 4-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፤

ሃሪ ኬን ሀትሪክ መስራት የቻለ ሲሆን ሰርጅ ጊናብሪ የተቀረውን አስቆጥሯል፤ ቭላድሚር ኩፋል ደግሞ የሆፈኒየምን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፤

ኬን በባቫሪያኑ ቤት አስገራሚ አቋሙን የቀጠለ ሲሆን በዘንድሮው ውድድር አመት ባደረጋቸው 7 ጨዋታዎች 13 ጎሎችን አስቆጥሮ 3 አሲስት አድርጓል፤

በጠቅላላው የባየር ሙኒክ ቆይታው ደግሞ በ67 የቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸውን ጎሎች 70 አድርሷል፤

ከቡንደስ ሊጋው በተጨማሪ ኬን በሁሉም ውድድሮች ላይ ለሙኒክ 103 ጨዋታዎች አድርጎ 98 ጎሎች አስቆጥሮ 29 አሲስት አድርጓል።

የዛሬውን ሀትሪኩን ተከትሎም ደግሞ በቡንደስ ሊጋው ላይ 9ኛ ሀትሪኩ ሲሆን በሁሉም ውድድሮች ላይ ደግሞ 10ኛው የሙኒክ ሀትሪኩ ሆኖ ተመዝግቧል፤

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል!በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ኤቨርተንን ገጥሞ አሸንፏል፤2-1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ለሊቨርፑል ራየን ግራቨንበርች እና ሁጎ ኤኪቲኬ ሲያስቆጥሩ ኢድሪስ ...
20/09/2025

✅ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል!

በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ኤቨርተንን ገጥሞ አሸንፏል፤

2-1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ለሊቨርፑል ራየን ግራቨንበርች እና ሁጎ ኤኪቲኬ ሲያስቆጥሩ ኢድሪስ ጋና ጉዬ ለኤቨርተን አስቆጥሯል፤

ጎል አስቆጣሪው ራየን ግራቨንበርች ለኢኪቲኬ አሲስት ያደረገው እሱ ነበር፤

በዚህም በመርሲሳይድ ደርቢ ጎል አስቆጥሮም አሲስት ማድረግ የቻለ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኗል።

ሊቨርፑል 5ኛ ተከታታይ የሊግ ጨዋታውን አሸንፎ በ15 ነጥብ የሊጉን መሪነቱን አጠናክሯል፤

ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ባደረጋቸው ያለፉት 5 የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታዎች ድል የቀናው ሲሆን ይህ ማድረግ የቻለው ከ88 አመታት በኋላ ነው፤

የኤቨርተኑ አሰሰልጣኝ ዳቪድ ሞይስ በአንፊልድ ያለው የውጤት ድርቀት የቀጠለ ሲሆን ለ23ኛ ጊዜ ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

⌚️ | ተጠናቀቀ |✅   2-0  ⚽️ማኔ 52'⚽️ማርቲኔዝ 81'📌 አል ናስር 2ኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገቡን ተከትሎ ሊጉን በጎል ልዩነት በልጦ መምራት ጀምሯል።➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-ht...
14/09/2025

⌚️ | ተጠናቀቀ |
✅ 2-0
⚽️ማኔ 52'
⚽️ማርቲኔዝ 81'

📌 አል ናስር 2ኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገቡን ተከትሎ ሊጉን በጎል ልዩነት በልጦ መምራት ጀምሯል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ከ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብሮች በኋላ ያለው ደረጃ ሰንጠረዥ ይህን ይመስላል።➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8
14/09/2025

✅ከ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብሮች በኋላ ያለው ደረጃ ሰንጠረዥ ይህን ይመስላል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ማንቺስተር ሰማያዊ ሆናለች!በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ተጠባቂ የነበረው የማንቹሪያን ደርቢ በሲቲ የበላይነት ተጠናቋል፤በኢትሃድ በተደረገው ይህ ጨዋታ ሲቲ 3_0 በሆ...
14/09/2025

✅ማንቺስተር ሰማያዊ ሆናለች!

በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ተጠባቂ የነበረው የማንቹሪያን ደርቢ በሲቲ የበላይነት ተጠናቋል፤

በኢትሃድ በተደረገው ይህ ጨዋታ ሲቲ 3_0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፤

ለሲቲ ሁለቱን ኤርሊንግ ሃላንድ ሲያስቆጥር የተቀረውን ፊል ፎደን አስቆጥሯል፤

ሃላንድን በ150ኛ የማን.ሲቲ ጨዋታው ያስቆጠራቸውን ጎሎች 129 አድርሷል፤

ውጤቱን ተከትሎ ሲቲ ነጥቡን 6 በማድረስ ወደ 8ኛ ከፍ ሲል ማን.ዩናይትድ ደግሞ በ4 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ተቀምጧል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

✅ሊቨርፑል በ95ኛ ላይ አሸነፈ!ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በርንሌይን የገጠመው ሊቨርፑል በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠረው ግብ 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል፤90 ደቂቃውን በበርንሌይ ተፈትኖ ከሰዓቱን ያሳለ...
14/09/2025

✅ሊቨርፑል በ95ኛ ላይ አሸነፈ!

ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በርንሌይን የገጠመው ሊቨርፑል በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠረው ግብ 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል፤

90 ደቂቃውን በበርንሌይ ተፈትኖ ከሰዓቱን ያሳለፈው ሊቨርፑል 95ኛ ደቂቃ ላይ ባገኘው ፍፁም ቅጣት ምት 1-0 አሸንፏል፤

የተገኘችዋን ፍፁም ቅጣት ምት ሞሀመድ ሳላህ ወደ ግብ የቀየረው ሲሆን ፍፁም ቅጣት ምቱ የተገኘው የበርንሌይው ሃኒባል ሜጅብሪ በ16.50 ውስጥ በእጅ በመንካቱ ነበር፤

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል 4ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቦ የሊጉን መሪነቱን አጠናክሯል፤

ታሪክ መሰራት የማይሰለቸው ሞሀመድ ሳላህ ዛሬ ያስቆጠረውን ግብ ተከትሎ አዲስ ሪከርድ ይዟል፤

ይህም በፕሪሚየር ሊጉ 188 ግቦች በመድረስ በምንጊዜም የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ ላይ 4ኛ ተቀምጧል።

➲ ቻናላችንን ይቀላቀሉ:-https://t.me/+kUjmDXP-cqA2N2Y8

Address

Addis Ababa

Telephone

+251940617388

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዮኒ-ሶከር Yoni-Soccer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዮኒ-ሶከር Yoni-Soccer:

Share