
18/07/2025
በዐቢቹ ሥራ አቧራዋን አራግፋ በአስደናቂ የለውጥ ጎዳና ላይ ያለች ደሴ ከተማ
የአብሮነት እና የመዋደድ ተምሳሌት በሆነችዉ ውቢቷ የደሴ ከተማ አስደማሚ የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ነው። የደሴ ከተማ ከቀደምት ስልጡን የኢትዮጵያ ከተሞች ተርታ የምትመደብ እና በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑት ከተሞች መካከል በዋናነት የምትጠቀስ ታሪካዊ ከተማ ናት። የደሴ ከተማ ህዝብ ፒያሳ ላይ ተሰባስቦ የኢትዮጵያውያን ባንድራ በመስቀልና በማክበር ያለምንም መቆራረጥ ከ85 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ፅኑ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ነው። ይህ ትልቅ አርአያነት ያለዉ ምስጉን ተግባር ነዉ፡፡ በቀድሞው ጊዜ የሲራራ ንግድ መዳረሻ የነበረችው ጥንታዊቷ የደሴ ከተማ በመጀመሪያ ምዕራፍ የኮሪደር ልማቷ የብልፅግና ብርሃን ወጋገን ፈንጥቃለች፡፡ በነዋሪዎቿ ልብ ውስጥ የተስፋ ችቦን ለኩሳለች፡፡ ደሴ ለኗሪዎቿ የምትመች ፣ የንግድ፣ የገበያ፣ የምርምርና የቱሪዝም ማዕከል ወደመሆን የሚያስጉዛትን የተስፋ ጎዳና ተያይዛለች። ልማትና ሰላሙን እንደ አይኑ ብሌን የሚጠብቀው የደሴ ከተማ ነዋሪ ለብልፅግናው መረጋገጥ ጊዜና ገንዘቡን ያለስስት በመስጠት፣ አበረታች የሞራል ስንቅ እና የልማት ደጀን ሆኗል። በዚህም ሌላኛዉ የኢትዮጵያ ኩራት ሁናችኋልና ለአመራሩ፣ ሰራተኛው እና ለነዋሪዎቿ የላቀ ምስጋና ይገባል፡፡
#ከእዳወደምንዳ
#የኢትዮጵያብልፅግና
#ኮሪደርልማት