አሀድ

አሀድ ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና አስተያየቶች የሚቀርብበት ገጽ ነው ።

ሀገራዊ አደራን ቡድናዊ በማድረግ ሀላፊነትን አለመወጣት ነውር ነውየህዝብን አደራና እምነት ወደ ጎን በመተው በቡድተኝነት መንቀሳቀስ፣ አስታራቂ ሀሳብ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የግልን አቋም ብቻ ማ...
16/08/2026

ሀገራዊ አደራን ቡድናዊ በማድረግ ሀላፊነትን አለመወጣት ነውር ነው

የህዝብን አደራና እምነት ወደ ጎን በመተው በቡድተኝነት መንቀሳቀስ፣ አስታራቂ ሀሳብ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የግልን አቋም ብቻ ማራመድና ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር ቡድናዊ ማድረግ ሀላፊነትን አለማወቅ እንዲሁም የተሰጠን አደራ በትክክል አለመወጣት ነው። ከዚህም በላይ በጀርባ ማሴርና አላስፈላጊ ግሩፕ እየከፈቱ መንቀሳቀስ ለሀገርና ለወደፊት ትውልድ ከመጨነቅ ይልቅ የግልንና የቡድንን ጠባብ ፍላጎት ማደላደልን ያሳያል።

ከምክክሩ አዳራሽ ቡድን ውጪ እውቅና የሌለውና ወገንተኛ የሆነ ሀሳብ ለማራመድ ቡድን ከፍቶ ለብቻ ተሰባስቦ መዶለት ለነገ አለማሰብንና የሌላን ሀሳብ ለማድመጥ ዝግጁ አለመሆንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በተመሳሳይ መልኩ በምክክሩ ሂደት ገና ከውጪ አቋም ይዞ መግባትና ግትር ሆኖ የሌላውን ሀሳብ አስቀድሞ መጣል ለስኬታማና አካታች ውይይት በሩን የሚዘጋ ጎጂ አካሄድ ነው።

14/08/2026

ዛሬም የተለየ ነገር አልተፈጠረም፤ የ35 ዓመቱ ጤናማ አብሮነት ይቀጥላል!
"አዲስ አበባን በተመለከተ አዲስ አጀንዳ መጣ" እያሉ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ አካላት አንድ መካድ የማይችሉት ሀቅ አለ። ይኸውም አዲስ አበባ ላለፉት 35 ዓመታት የኦሮሚያ ክልል መንግስት መቀመጫ ሆና ቆይታለች የሚለው እውነታ ነው። ታዲያ ዛሬ የተለየ ነገር ምን ተፈጠረ?
ሕገ-መንግስቱ "ልዩ ጥቅም ያገኛል" ብሎ ደንግጎ በነበረባቸው በእነዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ እንኳ፣ ክልሉ የሌላውን ኢትዮጵያዊ መብት የሚጋፋ የተለየ ጥቅም ይገባኛል ብሎ የጠየቀውም ሆነ ያገኘው ነገር የለም። አዲስ አበባ ሁሌም የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መዲና፣ የፌዴራል ማዕከል፣ እንዲሁም የውበትና የልማት ተምሳሌት ሆና ነው የኖረችው።
የአሁኑ የሕግ ማዕቀፍ ምክረ-ሐሳብ የሚያደርገው ይህንኑ በተግባር ሲሰራበት የነበረውን ተፈጥሯዊ ቁርኝት፣ ይበልጥ ግልጽ በሆነ የ"ጋራ ተጠቃሚነት" መርህ ማጠናከር ብቻ ነው። የመኖሪያ ቤት፣ የውሃ፣ የመንገድና የጸጥታ ጉዳዮችን በጋራ ማስተዳደር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ለሆኑት ለከተማዋና ለክልሉ የጋራ ብልጽግና ወሳኝ ነው። የ35 ዓመቱ አብሮነታችን ዛሬም በማይነጣጠል የጋራ ተጠቃሚነት ይቀጥላል እንጂ አዲስ የተፈጠረ ስጋት የለም!

12/08/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!

የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው።

‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል።

የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።"

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

11/08/2026
06/08/2026

Address

Bole Street

1000

Telephone

+954621425

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሀድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share