Ethio Truth 24

  • Home
  • Ethio Truth 24

Ethio Truth 24 በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮ የራሳችንን እይታ የምንገልጽበት ገጽ ነው!

16/03/2026
01/02/2026



ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረ።ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህር...
21/11/2025

ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረ።

ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

21/11/2025
14/07/2025
ከ230 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ***************የሕንድ የመንገደኞች አወሮፕላን ከአህመዳባድ ኤርፖርት ተነስቶ ወደ ለንደን በመብረር ላይ እያለ ባ...
12/06/2025

ከ230 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ
***************

የሕንድ የመንገደኞች አወሮፕላን ከአህመዳባድ ኤርፖርት ተነስቶ ወደ ለንደን በመብረር ላይ እያለ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ከ18 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይነት እንደሚሰጥ አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

"ስልጣን ሃሳብን ሽጦ በህዝብ ሲገዛ ብቻ የሚገኝ ነገር ነው!! ከዚህ ውጭ ያሉ ወንድሞቻችን ግዜ እንዳያባክኑ መክራቸዋለሁ!! ትርፉ ድካም ብቻ ስለሆነ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)...
08/06/2025

"ስልጣን ሃሳብን ሽጦ በህዝብ ሲገዛ ብቻ የሚገኝ ነገር ነው!! ከዚህ ውጭ ያሉ ወንድሞቻችን ግዜ እንዳያባክኑ መክራቸዋለሁ!! ትርፉ ድካም ብቻ ስለሆነ"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)

ተወዳጁ የድሬ ከንቲባ🥰 የሚወደው ላይክ ሼር ያድርግ
07/06/2025

ተወዳጁ የድሬ ከንቲባ🥰
የሚወደው ላይክ ሼር ያድርግ

ኢትዮጵያ እየመከረች ነውበሀገራዊ ምክክሩ የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሁለተኛ ቀን ውሎ በምስል፡-   # #ምክክር
31/05/2025

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው

በሀገራዊ ምክክሩ የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሁለተኛ ቀን ውሎ በምስል፡-

# #ምክክር

የቤንዡ አለም አቀፍ የከተሞች ወዳጅነት ቀን በቻይና ሻንዶንግ ግዛት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ በዚህ ዝግጅት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር እና ከትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ...
30/05/2025

የቤንዡ አለም አቀፍ የከተሞች ወዳጅነት ቀን በቻይና ሻንዶንግ ግዛት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በዚህ ዝግጅት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር እና ከትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እንዲሁም ከሌሎች አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች የመጡ ልዑካን ተሳታፊ ሆነዋል።

በወቅቱ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ድሬዳዋ ከቻይናዋ ቢንዡ ከተማ ጋር ያላትን የወዳጅነት ትብብር ማደስ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

Address

Ethiopia

96

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Truth 24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share