የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page

የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page ✅ የወቅታዊ ፣የጤና ፣ የጉዞ እና የማህበራዊ ጉዳይ መረጃ ምንጭ/ source of current & social affaire working For Peace
(1)

ትንሽ የቆየ ዜና ቢሆንም ግን ወንዶች ንቁ ተብሏልባል ሚስቱን ያለ ሜካፕ አይቶ ፈታት! 💔ዱባይ፡ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) አንድ አዲስ ተጋቢ ባል፣ ሚስቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ሜካ...
07/10/2025

ትንሽ የቆየ ዜና ቢሆንም ግን ወንዶች ንቁ ተብሏል

ባል ሚስቱን ያለ ሜካፕ አይቶ ፈታት! 💔

ዱባይ፡ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) አንድ አዲስ ተጋቢ ባል፣ ሚስቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ሜካፕ አይቶ ሊፈታት መወሰኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ባልና ሚስቱ በድባይ ከተማ በሚገኘው አል ማምዛር የባህር ዳርቻ ለመዋኘት ከሄዱ በኋላ ነበር ይህ ያልተጠበቀ ክስተት የተከሰተው።

እንደ ጎልፍ ኒውስ ዘገባ፣ የ28 ዓመቷ ሙሽራ ሜካፕዋ በባህር ውሃ ታጥቦ ሲጠፋ፣ የ34 ዓመቱ ባል "መልኳ እንደተለወጠ" በመመልከቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ደርሶበታል። ለሴትየዋ የምክር አገልግሎት የሰጡት የስነ-ልቦና ባለሙያ እንደገለጹት፣ ባልየው ሚስቱ ከሠርጉ በፊት የነበራትን ያህል ውብ እንዳልሆነች ተሰምቶታል።

ባልየው ሚስቱ ከመጠን ያለፈ ሜካፕ በመጠቀም፣ የሐሰት የዐይን ሽፋሽፍቶችን ጨምሮ፣ እንዳታለለችው በመክሰስ ለፍቺ ጥያቄ አቅርቧል።

ይህ ክስተት ትዳር ከመመሥረቱ በፊት ባልና ሚስቶች እርስ በእርስ ያላቸው እውነተኛ ማንነት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ የሚያሳይ አሳዛኝ ምሳሌ ሆኗል።

ይህ አስገራሚ ፍቺ በብዙ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስነሳ ይገኛል።

Source :- Gulf News

እናንተ ሚስታችሁን ያለ ሜካብ አይትችሁ
ነው ያገባችሁት ?

 #ተቀበረ😭 አውሬዎቹን ለመያዝ ፖሊስ እየጣረ ነው‼️አንጀት የሚበላው ህፃን አብዱጀሊል አስክሬን ወንዝ ዳር ከመገኘቱ በፊት ወደ ቤተሰብ አንድ ስልክ ተደውሎ:- "እናቱን አገናኘኝ በማለት በ3...
07/10/2025

#ተቀበረ😭

አውሬዎቹን ለመያዝ ፖሊስ እየጣረ ነው‼️

አንጀት የሚበላው ህፃን አብዱጀሊል አስክሬን ወንዝ ዳር ከመገኘቱ በፊት ወደ ቤተሰብ አንድ ስልክ ተደውሎ:- "እናቱን አገናኘኝ በማለት በ30ደቂቃ ውስጥ 50,000ብር እንዲያስገቡ አስጠንቅቆ ለሰው ከተናገራችሁና ብሩን ካለስገባችሁ አንገቱን ነው የምቆርጠው ብሎ ዝቶ ልጃቸውን ለማትረፍ ብለው እንደምንም 25000ብር ልከውለት ነበር

በፍለጋ ሲንከራተት የነበረው አጎቱ ልቡ ተሰብሮ ሲነግረን
"ብሩ ከደረሰው በኋላ በሰላም ነበር ያወራኝ፣ለማንም እንዳትናገሩ ስላለን ህፃኑን ለማትረፍ ብለን ደብቀን ነበር ግን ቀደሙን😭ገድለው ሰጡን"አለኝ 😭

የዚህን ምስኪን ህፃን ገዳይ ፖሊስ እንደሚደርስበት ተስፋ አለን! ለሚያሳዝኑት እናትና አባትም ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጣቸው!!

07/10/2025
ሰበር ዜና ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች!ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በኤርትራ ላይ ለተመድ በላከችው ደብዳቤ ክስ አሰምታለችኢትዮጵያ ከወራት በፊት ኤርትራ በውስጥ ጉዳዮ...
07/10/2025

ሰበር ዜና

ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች!

ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በኤርትራ ላይ ለተመድ በላከችው ደብዳቤ ክስ አሰምታለች

ኢትዮጵያ ከወራት በፊት ኤርትራ በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው በማለት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረበችው ሰሞታ ምላሽ ሳይጥበት፣ ሁለተኛ ደብዳቤ ማስባቷ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤርትራ ላይ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ነው የሚል ክስ ለሁለተኛ ጊዜ በደብዳቤ ማቅረቡን፣ ለመንግሥት ቅርበት ያለው ሆርን ሪቪው ዘግቧል፡፡ ከአራት ወራት ገደማ በኋላ ለሁተኛ ጊዜ ለመንግሥታቱ ድርጅት የገባው ድበዳቤ ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግሥት ተፋላሚዎችን በማስታጠቅና ከህወሓት ጋር በማበር የሚከስ ነው፡፡

ለተባበሩት መንግስታት የተላከ ደብዳቤ ኤርትራ ታጣቂዎችን በማስታጠቅ ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ ተጠምዳለች በማለት ይከሳል፡፡ ይሁን እንጂ ኤርትራ የትኛዎቹን የታጠቁ ኃይሎች እንደምታስታጥቅ ደብዳቤው በስም ጠቅሶ ያቀረበው ዝርዝር መረጃ የለም፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች ከመንግሥት ጋር የሚፋለሙ የታጠቁ ኃይሎች ያሉ ሲሆን፣ የአማራ ፋኖ ኃይሎች እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት-ኦነግ ሸኔ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በግልጽ በደብዳቤው ላይ ባይገለጸም ኤርትራ የፋኖ ኃይሎችን እንምታስታጥቅ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኩል በተለያዩ አጋጣዎች ይገለጻል፡፡

የክስ ድብዳቤው ኤርትራ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለማፍረስ ከህወሓት ጋር በአጋርነት እየተንቀሳቀስች መሆኑን ይገልጻል፡፡ ኤርትራ ከህወሓት ጋር የጀመረችው ግንኙነት ስምምነቱን ከማፍረስ በሻገር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እየከመጣስ የዘለቀ መሆኑም በድብዳቤው ተመላክቷል፡፡

ኤርትራ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ለመንግሥታቱ ድርጅት ባስገባችው ደብዳቤ ለቀረበባት ክስ በሰጠችው ክስ በኢትዮጵያ የውስጥ ግጭት እጄ የለበትም ማለቷ ይታወሳል፡፡ ኤርትራ ታጣቂ ኃይሎችን በማስታጠቅም ይሁን የፕሪቶሪያውን ሰላም ስምምነት በማስተጓጎል ምንም አይነት ሚና እንደሌላት በማስታወቂያ ሚኒስትሯ የማ ገብረ መስቀል በኩል ገልጻ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ለመንግሥታቱ ድርጅት ባቀረበችው ድብዳቤ ኤርትራ እያደረገች ነው የተባለውን ጣልቃ ገብነት በሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ አደጋ ነው ብላለች፡፡ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና በውስጥ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን ለመመከከት፣ ሕጋዊ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች ሊወስድ አንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ምንም እንኳን ኤርትራ በኢትዮጵያ የውስጥ ግጭቶች እጄ የለበትም ብትልም፣ በተለይም ከህወሓት ጋር የጀመረችው ግንኙነት በተናጠል ድንበር እሰከመከፈት የዘለቀ ሆኖ ታይቷል፡፡ የህወሓት እና ኤርትራ መንግሥት የሚዲያና የፕሮፖጋንዳ ሰዎች ስም የጀመረው “ጽምዶ” የተሰኘው ግንኙነት በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሽፋን እየተሳለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡

በዚሁ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በታባለው “ጽምዶ” ወይም ጥምረት የኢትዮ-ኤርትራን ድንበር መከፈቱ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እሰከመጣስ የዘለቀ ነው፡፡ ይሄንኑ ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ ህወሓት ከኤርትራ ጋር በጋራ የመሰለፍ ጥሪ ከሰሞኑ ባወጣው የአቋም መግለጫ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከፋኖ ታጣቂዎች ጋርም በይፋ የወጣ ማረጋገጫ ባይኖርም ኤርትራ ከጀርባ ድጋፍ ታደርጋለች የሚሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ይወጣሉ፡፡via Andafta
Wasu Mohammed - Mereja

ታጣቂ ቡድኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ‼ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ተከታዩን ብሏል።📌ህዝባችን ዋጋ የሚከፍለው በሁለት ቢላ በሚበሉ ...
07/10/2025

ታጣቂ ቡድኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ‼

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ተከታዩን ብሏል።

📌ህዝባችን ዋጋ የሚከፍለው በሁለት ቢላ በሚበሉ ሁለት-ረገጥ የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮቹ እና ከውጭ ጠላት ጋር በሚተባበሩ አካላት ሴራ በመሆኑ መንግስት በእነዚህ ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ አጥብቀን እንጠይቃለን።

ታጣቂ ቡድኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ የሚያበረታታ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጥርና የመልሶ ማቋቋም ስትራቴጅዎችን አስቀድሞ እንዲያዘጋጅ።

አንጻራዊ ሰላም በሰፈነባቸው አካባቢዎች የተቋረጡ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እንዲቀጥሉና አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲጀመሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን።

📌ለታጠቁ ኃይሎች የቀረበ ጥሪ
በልዩ ልዩ ምክንያቶች እንዲሁም የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስመለስ በሚል ወደ ትጥቅ ትግል የገባችሁ ወንድምና እህቶቻችን የአሁኑ የትጥቅ እንቅስቃሴ ህዝባችን በእጅጉ የጎዳና ለታሪካዊ ጠላቶች ጥቃት በር እንደሚከፍት በመገንዘብ እንዲሁም‎ አሁን ባለው አደገኛ ሁኔታ መቆየት የሕዝቡን ክብር እንደማይመጥን በመገንዘብ ወደ ድርድርና ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ በመምጣት ለአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ውለታ እንድትውሉለት አብን አጥብቆ ይጠይቃል።

📌ለአማራ ሕዝብ የቀረበ ጥሪ
በስሙ የሚደረግን የፖለቲካ ንግድና የባንዳነት ተግባር በቃኝ ብሎ ዘላቂ ጥቅሞቹን የሚያከብርበትን መንገድ እንዲከተል። በጥቂት ልጆቹ የባንዳነት ተግባር ታሪኩንና ህልውናውን ሊያጠፋ ለሚችል እንቅስቃሴ መተባበር እንደሌለበት አውቆ፣ በመሠረታዊ ጥያቄዎቹ ላይ ትኩረት ካደረጉ ሐቀኛ የትግል እንቅስቃሴዎች ጎን ጸንቶ እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን ብሏል ንቅናቄው።

ፖሊስነቴን በጣም ነው የምወደው መርጬው ነው የገባሁት ኮንስታብል እስከዳር | የድሬዳዋ ፖሊስ
05/10/2025

ፖሊስነቴን በጣም ነው የምወደው መርጬው ነው የገባሁት ኮንስታብል እስከዳር | የድሬዳዋ ፖሊስ

በደቡብ አፍሪካ  አባቶች ከእናቶች እኩል የወሊድ እረፍት ተፈቀደላቸው "ለደቡብ አፍሪካ የወደፊት አባቶች ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው"   | የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሁሉም ወላጆ...
05/10/2025

በደቡብ አፍሪካ አባቶች ከእናቶች እኩል የወሊድ እረፍት ተፈቀደላቸው

"ለደቡብ አፍሪካ የወደፊት አባቶች ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው"

| የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሁሉም ወላጆች እኩል የወሊድ እረፍት እንዲኖራቸው ወሰኗል።

ውሳኔው ትልቅ ውሳኔና ለፆታ እኩልነትና የቤተሰብ መብት ግዙፍ አሸናፊነት ተደርጎ ተወስዷል።

በቀደመው ሕግ እናቶች የአራት ወር የወሊድ ፈቃድ ያላቸው ሲሆን፤ አባቶች ደግሞ 10 ቀናት ብቻ ይሰጣቸው ነበር።

የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ፣ ሕጉን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ያለው ሲሆን፤ ለአባቶች አድሎአዊ ነው ብሏል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ወላጆች እንደፈቀዱ የሚጠቀሙበት እኩል የወሊድ እረፍት እንዲያገኙ በይኗል።
'ሲንግል ዳድስ ኔትወርክ' የተባለ ድርጅት መስራች የሆኑት ሴትምቢሶ ፓኪቲ፤ "ይህ ለእኩልነት፣ ለቤተሰብ ደኅንነትና ለደቡብ አፍሪካ የወደፊት አባቶች ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው" ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ2023 የአገሪቱ የታችኛው ፍርድ ቤት፣ የአገሪቱ ሁለት ሕጎች የተወሰኑ ክፍሎች ፍትኃዊነት የጎደላቸው መሆናቸውን እንዳገኘና የበርካታ የቤተሰብ መብቶችን የሚጥሱ ናቸው ብሏል።

ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሊድ ፈቃድና የሥራ አጥ ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘትን በተመለከተ ለወላጆች ፍትኃዊ አለመሆኑን ወስኗል።

ጉዳዩ በብቸኝነት በሴቶች ላይ የሚጣለውን ማኅበረሰባዊ ጫና ፍትኃዊ ለማድረግ በወጠኑ በሁለት ጥንዶች፣ በፆታ እኩልነት ኮሚሽንና በሌሎችም ወደ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፤ የወላጅነት ኃላፊነት የጋራ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

ቢቢሲ

ይህን ወጣት አወቃችሁት⁉️✍️ ሙዓዝ ነዚፍ ይባላል። ከመዲና ዩኒቨርስቲ ተመርቋል። በፊት ጀምሮ ብዙዎቻችሁ ቲክቶክ ላይ በዳዕዋዎቹ ታውቁታላችሁ ብዬ አስባለሁ።በዳዕዋዎቹ ላይ ለስለስ ባለ መልኩ...
05/10/2025

ይህን ወጣት አወቃችሁት⁉️

✍️ ሙዓዝ ነዚፍ ይባላል። ከመዲና ዩኒቨርስቲ ተመርቋል። በፊት ጀምሮ ብዙዎቻችሁ ቲክቶክ ላይ በዳዕዋዎቹ ታውቁታላችሁ ብዬ አስባለሁ።

በዳዕዋዎቹ ላይ ለስለስ ባለ መልኩ ስለነበር የሚያቀርበው፤ ጠንከር ብሎ ይወያያል ብሎ ስላላሰበ ባለፈ ኢስሐቅ እሸቱ ሙዚቃን ሐላል ካለው አደም ጋር ለውይይት አቅርቦት ነበር።

ነገር ግን ውይይቱ ወደ መሃል እንደደረሰ ሙዓዝ ተቀየሰባቸው መሰል¡
ምን እንደተፈጠረ ተወያዩ አደምም፣ አወያዩ ኢስሐቅም ግራ ገብቷቸዋል። (ክስተቱን የሚያሳይ አንድ ቪድዮ አካፍላችኋለሁ።)

ወንድም ሙዓዝ ገና ወደ ውይይቱ ሲገባ በመወያያ ርዕሱ ዙሪያ ያሉ መረጃና ማስረጃዎችን «አላህ እንዲህ አለ፣ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ…» እያለ መረጃን ከሥር መሠረቱ ከምንጩ እየጠቀሰ ሲያስረዳ፤ ኣደም እንደለመደው የሆነ ያልሆነውን እያቀራመተ ከወገቡ ጀመረና በአንድ ደካማ ሐዲሥ ላይ መከራከሪያ ነጥቡን ገነባ። የርሱ የመናገር ተራ በተሰጠው ቁጥር ሐዲሥ ጥቀስ ሲባል ያቺን ሐዲሥ እየጠቀሰ ለመከራከሪያ ሃሳቡ ብይን መገንቢያ አደረጋት።

ወንድም ሙዓዝ ሆነ ብሎ አውቆ ዝም ብሎ አልፎት ሲያበቃ፤ አደም ጉዳዩን ከመሠረቱ ይዞ ገንብቶ ግንባታውን ሊያጠናቅቅ ሲደርስ፤ ሙዓዝ ብድግ ብሎ «ሐዲሡን ግን አይተኸዋል ኣደሜ?» አለው ፈገግ እያለ በጨዋ ደንብ። «ምነው? ችግር አለበት?» አለ ኣደሜ ቅመም።
«አዎ! ሐዲሡ ዶዒፍ ነው!» ሲለው፤ እንኳን ኣደም ኢስሐቅ ራሱ ምድር ተሰንጥቃ ብትውጠው የሚመኝ ይመስላል አደነጋገጡ!
«እስኪ ዶዒፍ እንደት እንደሆነ ሰነዱን ንገረኝ? ማንኛው ዘጋቢ ላይ?» ሲለው፤ ሙዓዝ አነበበለት። ጭራሽ ቡኻሪ ደካማ ያሉት ሰው እንዳለበት ነገረው። ምን ይባላል⁉️ ኢንተሃል አምር!

ከዚያ ወዲህ አደም አደብ ይዞ በሩን ዘግቶ እያጨበጨበ ነው። ለወደፊቱ ካላበደ በቀር ሙዓዝ ባለበት የሚሄድ አይመስለኝም።

ዑመር በአንድ መንገድ ሲሄድ ሸይጧን በሌላ መንገድ እንደሚሄደው ሁሉ፤ ሙዓዝ በአንድ መንገድ ሲሄድ ኣደም አቅጣጫ የሚቀይስ ይመስለኛል።
ኢስሐቅም «ምነው እጄን በቆረጠው!» እንደሚል እሙን ነው። ምክንያቱም ለዘብተኛ የሆነ ሰው አግኝቼ ነጥብ አስቆጥራለሁ ብሎ አስቦ፤ በተቃራበኒው በራሱ ላይ ጎል ሲያስቆጥር አስቡት!

አሁን ላይ አቅም ባነሰውና ክፉኛ በተጎዳው አደም ቦታ ሌላ ይሻላል የሚለውን ሰው ማምጣት ሲገባው፤ ውርደቱን ለመደበቅ ወደ ሌላ ተንጠራራ።
ሲጀመር ሰው መቀየር ያለበት የተሸናፊ ወገን እንጂ አሸናፊ አይደለም።

በል! አሁንም ኢስሐቅ ከኢብኑ ሙነወር ጋር ተወያይ፤ እነ ሰመሃር ደግሞ ከአቡል ቡኻሪይ ጋር ይወያዩ።

ባይሆን ከአሁን በኋላ ሙዓዝ የሚባል ስም ስትሰሙ እንዳትበረግጉ። የሶሐብዩ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ስም ሊሆን ይችላልና!

via Murad Tadesse

The “Aisha” Conspiracy and Fano’s Hate Propaganda: A Reflection of Rwanda’s Manufactured Threat(ወላሂ አማራ አልሆንም‼)The 1994 ...
05/10/2025

The “Aisha” Conspiracy and Fano’s Hate Propaganda: A Reflection of Rwanda’s Manufactured Threat
(ወላሂ አማራ አልሆንም‼)

The 1994 Rwandan genocide demonstrated that mass violence is rarely spontaneous; it is politically engineered through fear, propaganda, and the deliberate creation of an enemy. Rwanda’s Hutu extremists spread a narrative of a “Tutsi threat,” mobilizing ordinary citizens under the illusion of self-defense. Media outlets like RTLM amplified lies and hatred, transforming rumor into justification for extermination.

A strikingly similar pattern is emerging in Ethiopia. The Amhara nationalist militia known as Fano, widely perceived as the military wing of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church, has used religion and ethnicity to consolidate power and legitimacy. Facing declining public support and internal division, Fano appears to be manufacturing a sense of existential threat—particularly among Muslim Amharas, who historically have been skeptical of the militia’s Christian identity.

To bridge this divide, propagandists circulated the story of “Aisha,” an alleged Muslim Amhara girl who was said to have been persecuted by Oromo militants and who supposedly renounced her Amhara identity by declaring, “Wollahi, I will never be an Amhara.”(ወላሂ አማራ አልሆንም‼) The tale quickly spread across social media and local networks, presented as proof that “Amharas are under attack.”

However, mounting evidence suggests that the Aisha narrative was fabricated—a strategic propaganda device designed to manipulate emotion and faith, portraying the Fano movement as the only defender of Amhara identity and dignity. Through this fabricated case, Fano sought to convince Muslim Amharas that their survival depended on aligning with a movement rooted in Orthodox Tewahdo militancy.

Just as Rwandan elites turned fear of the Tutsi into a mobilizing myth, Fano’s use of the “Aisha” story represents a calculated effort to weaponize identity and religion. It creates an artificial sense of persecution, fosters hatred toward perceived enemies, and converts ordinary citizens into instruments of a political project.

Both cases reveal a dangerous formula:

1. Invent an existential threat.
2. Use propaganda and religion to unify followers.
3. Portray violence as self-defense.
4. @ fear to suppress dissent and consolidate control.

The Rwandan genocide stands as a warning that hate-based mobilization built on fabricated conspiracies can spiral into mass atrocity. Exposing and countering such manipulative propaganda—like the Aisha fabrication—is essential to prevent Ethiopia from descending further into communal polarization and violence.

©️ Abebe Hagos

"ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው" አለ❗️የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?...
05/10/2025

"ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው" አለ❗️

የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?

‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡

በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወቅከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡

ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ
እኔም ለምን አልኩት
እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡

ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡
ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም፡፡

#አደይ
#ሼርርርር

"የፋኖ ትግል የሚጀምረው ከነ አደም መስሎኝ""የእስልምና መንግስት መስሎኝ ችግር አመጣ ያልነው"ለአንድ አላማ ግን በብዙ አቅጣጫ የተሰለፈ የጥፋት ጎራበአማራ ክልል እየሆነ ያለው ጥፋት እየከፋ...
05/10/2025

"የፋኖ ትግል የሚጀምረው ከነ አደም መስሎኝ"

"የእስልምና መንግስት መስሎኝ ችግር አመጣ ያልነው"

ለአንድ አላማ ግን በብዙ አቅጣጫ የተሰለፈ የጥፋት ጎራ

በአማራ ክልል እየሆነ ያለው ጥፋት እየከፋ ነው:: በተለይ ፅንፈኛ ቡድኑ ለአንድ አላማ ብዙ ጎራዎችን አሰማርቶ እየፈፀመ ያለውን እልቂት እና ጥፋት ምክንያታዊ ለማድረግ በስፋት እየለፋ ነው:: እንደ ማሳያ ይሆን ዘንድ በደቡብ ወሎ ሰሞኑን እየሆነ ያለውን ማየት በቂ ነው::

አንዱ ጎራ "እኛ ሙስሊሙን ልናጠቃ ይቅርና በሙስሊም ስም "ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ብለን የዘመቻ ስም ሰይመን እየተዋጋን ያለን ሀይሎች ነን በማለት ሙስሊሙን ለማታለል እና ለማጃጃል ዲፕሎማሲያዊ ፉተታ ሲያካሂድ ሌላኛው ጎራ ደግሞ ብሎ በኩራት ትግሉ የሚጀምረው ከሙስሊሙ ጋር እንደሆነና የችግሩ ዋና መንስኤና ነፍጥ አንግበው ፍጅ*ት የጀመሩት የሙስሊም መንግስት በመምጣቱ መሆኑን በማንሳት እንቅጩን በኩራት በመናገር አስመሳዩን ጎራ በተግባራችን አትፈሩበት እያለ ሲገስፅ እያየን ነው::

የሙስሊም መንግስት የተባለው እንግዲህ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የአባት ስም የሙስሊም መሆኑን ልብ ይበሉ::

ይህን መርዛማ እቅዳቸውን ወደ ተግባር በማውረድም የመካነሰላሙ የመስጂድ ጥቃት ተፈፅሟል:: ይህን ነውር ፈፅመውም ከጎናቸው ያሰለፉትን ጥቂት ሙስሊም እንዳይባንንባቸው በተለያየ ጎራ ሆነው ለማድበስበስ ምክንያት እየደረደሩ እያስተባበሉ ይገኛሉ:: ከነዚህም መካከል

ጎራ አንድ :- ጥቃቱን የፈፀመው መንግስት ነው በማለት ለማድበስበስ ሲሞክሩ

ጎራ ሁለት;- የተገደሉት የሀይማኖት አባቶች ሳይሆኑ በመስጂዱ የተደበቁ የሚሊሻ ኃላፊዎች ናቸው በማለት ነውራቸውን በኩራት ምክንያታዊ ለማድረግ እየሞገቱ ነው::

ጎራ ሶስት:- የገደሏቸው የሀይማኖት አባቶች እንደሆኑ ለመካድ አላስችል ያላቸው እነዚህ ደግሞ ኢማሞቹ የመንግስት አፈቀላጤዎች ስለነበሩ ነው የተወገዱት ብለው ቀጣይ ተረኞች ጋር እስኪደርሱ እየፎከሩ ነው::

ጎራ አራት:- ወለጋ ላይ ብዙ ሙስሊም ሲጠቃ ዝም ብላቹ አሁን የምን ማካበድ ነው በማለት ጥቃቱን የማቃለል ቅስቀሳ እየፈፀመ ነው::

ጎራ አምስት :- በኩራት የተፈፀመውን ግድያ በማፅደቅ የትግላቸው መነሻ ሙስሊሙን ማፅዳት መሆኑን በግልፅ እየሰበከ ነው::

ይህ ጎራ ዛሬ ሳይሆን ላለፉት አመታት በአደባባይ የእስላም መንግስት ከመጣ ጀምሮ ነው ሀገራችን የረከሰችው፣ ኢትዮጵያ ከገባችበት ውጥንቅጥ ለመውጣት ያላት አማራጭ አንድ ብቻ ነው:: ይህም ወደ ድሮው የአፄው ዘመን ተመልሰን ክርስቲያናዊ መንግስት ስንመሰረት ብቻ ነው በማለት ትላልቅ መስቀል ደረታቸው ላይ አንጠልጥለው በአደባባይ ሲሰብኩ እና የሚታገሉበትን አላማ ሲያብራሩ እርራሳቸው ባሰራጩት ቪዲዮ ላይ ከተመለከትን ቆይተናል::

ጠላታቸው እስልምና እና ሙስሊሞች መሆናቸውን በአደባባይ ሰብከዋል:: አሁን እቅዳቸውም ወደ ተግባር በማውረድ በኩራት ሙስሊሙን ማጥቃት ተያይዘውታል::

ይህ መርዘኛ አስተሳሰብ የሁሉም ክርስቲያኖች አስተሳሰብ ባይሆንም በብዙ መዋቅሮች ውስጥ ሰርፆ በመግባት አላማውን ለማሳካት ከንቱ ሙከራ እያደረገ ይገኛል::

ይህን እኩይ አላማ በድህነት በድንቁርና እና በመሀይምነት የአለም ቁንጮ የሆነውን፣ ቀን እየቆጠረ አመት ሙሉ ስራን እየተፀየፈ ሀገሪቷን ለድህነት እና ለችጋር ለዘመናት ተጠፍንጋ እንድትቀመጥ ያደረገን እሳቤ አዝሎ የሚውልን የእውቀት ፀበኛን ኃይል አሰልፎ ያሳካል ብሎ ማሰብ ዘበት ቢሆንም የሚያደርሰው ጥፋት እና ውድመት ግን ከባድ ስለሚሆን ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቁ ይበጃል እና ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከር ፣ጥበብ እና ማስተዋል በተሞላበት መንገድ ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን እራሱን ከነዚህ ደብተራዎች ጥቃት ለመከላከል በሚገባቸው ቋንቋ (በግዕዝም)ቢሆን ለማነጋገር ሊዘጋጅ ይገባዋል::

በመካነ ሰላም የተገደሉትን ኢማሞች እና ሙስሊሞች አላህ በሸሂድነት ይቀበላቸው::

በክልሉ ያለውን ሙስሊም ማህበረሰብ ከዚህ ፅንፈኛ ቡድን ሴራ አላህ ይጠብቅልን!

© አቡ ዳውድ ኡስማን

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂ...
04/10/2025

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ ፦
1 የመስጂድ ዋና ኢማምና የወረዳው መጅሊስ ም/ሰብሳቢ
2 የመስጂድ አመራሮች
3 የመስጂድ ኻዲሞችን አሰቃቂ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ መግደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አረጋግጦልናል።

እነሱም ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው ።

ጠቅላይ ምክርቤቱ የእምነት ተቋማት የተከበሩ ቦታዎች በመሆናቸው ሊጠበቁ እንጅ እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባር የሚፈፀምባቸው መሆን የለባቸውምና ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል።

መላው የሃይማኖት ተቋማትም በእምነት ቦታዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎች እና በእምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ መሰል የጅምላ ግድያ
ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል።

ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በሀይማኖት ተቋማት ላይ የተቃጣ አደጋ ለመከላከል መረጃ በመለዋወጥ የሃይማኖት ተቋማትንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ምክርቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ብዝሃ ሀይማኖት ባለባት ሀገራችን በተለያየ እምነት ውስጥ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት ያቆዩተን ሰላማዊ እና መልካም መስተጋብር ሆን ተብሎ ለመናድና ማባሪያ ያጣ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚፈልጉ አካላት የፈፀሙት መሆኑን ጠቅላይ ምክርቤቱ ይገነዘባል።

በመጨረሻም ሁሉም ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ይህ ጉዳይ አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር ብሎም እንዳያጠፋ ድርጊቱን እንድታወግዙ እንዲሁም በፅኑ እንድትቃወሙ እየጠየቅን መንግስትም ይህንን ተግባር በእምነት ቦታዎችና አባቶች ላይ የፈፀሙት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።

መስከረም 24፣2018 ዓ.ል
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page:

Share