Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Miidiyaa M/Lallaba Shaggar  ሸገር  ሀገረ ስብከት ሚዲያ tiktok.com/
(1)

Biyya Lallaba Magaalaa Shaggar irraa kan darbu.
ከሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሚተላለፍ።
This is the Official Shegercitydiocese page you can get all the latest news About EOTC in Afaan Oromoo and Amharic you can follow us.

የብፁዕ አቡነ ሰላማ የሁለተኛ ዓመት የበዓለ ዕረፍት መታሰቢያ የጸሎተ ፍትሐት መርሐ ግብር ተካሄደ። መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተካሄደው የጸሎተ...
28/09/2025

የብፁዕ አቡነ ሰላማ የሁለተኛ ዓመት የበዓለ ዕረፍት መታሰቢያ የጸሎተ ፍትሐት መርሐ ግብር ተካሄደ።

መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተካሄደው የጸሎተ ፍትሐት ሥነ ሥርዐት ላይ በርካታ የብፁዕነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆች ተገኝተዋል።
ብፁዕነታቸው አስተምረው ካሳደጉአቸው መካከል ቀሲስ ዶክተር ዘበነ ለማ አንዱ ናቸው። ቀሲስ ዶክተር ዘበነ በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪጅና የደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት በዚህ የተገኘነው ከብፁዕነታቸው በረከት እንድናገኝ ነው ብለዋል።

በጸሎተ ፍትሐት ሥነ ሥርዐቱ ላይ ከተለያየ ገዳማት አድባራት የመጡ ካህናት፣ ምእመናን፣ ብፁዕነታቸው አስተምረው ለትልቅ ማዕረግ ያበቋቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ተገኝተዋል።
©AAMEDIA

"በመካከላችንም ሆኖ በመስቀሉ አስታረቀን፤ በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛም ወደ ገነት መለሰው”     ቅ/ኤፍሬም     ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ     ክህነት ዋ...
28/09/2025

"በመካከላችንም ሆኖ በመስቀሉ አስታረቀን፤ በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛም ወደ ገነት መለሰው” ቅ/ኤፍሬም
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ።

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በቡራዩ ጽርሐ ጽዮን አቡነ ተ/ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ።

መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ/ም ||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ||

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ቡራዩ ክ/ክተማ የቡራዩ ጽርሐ ጽዮን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ፣ ሐዋርያዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ።

ብፁዕነታቸው አያይዘውም ግንባታው የተጠናቀቀው የጽርሐ ጽዮን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ቤቴልሄም ባርከው አገልግሎት አስጀመሩ፣ እንዲሁም አዲስ ለሚሠራው ለቤተ ክርስቲያኑ የገቢ ምንጭ የሚሆን የገበያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አኖሩ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ኃይል ቆሞስ አባ አፈወርቅ ዮሐንስ፣ መጋቤ ሰላም መምህር ጌትነት በላይ የክ/ከተማው የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ፣ የደብሩ አስተዳዳር መልአከ ዓርያም አባ ወልደ-ሚካኤል፣ሊቃውንት አባቶችና የሰ/ት/ቤት ዘማርያን እንዲሁም ብዙ ምዕመናን ተገኝተዋል።

ሪፖርት
በቤተ ክርስቲያኑ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እንዲሁም ወደፊት የሚከናወኑ ሥራዎች በብፁዕነታቸው ፊት አጭር የሥራ ሪፖርት ቀርቧል።
በተያያዘም የሕንፃ ቤቴልሄም ግንባታ ከተመሠረተ ጀምሮ በእውቀታቸው በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ለረዱና ለተባበሩ ግለሰቦችና ለአቢይ ኮሚቴዎች ከብፁዕ አባታችን የሽልማትና የእወቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶአል።
በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስለ አለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧልና ዕብ 12፥2 በሚል ኃይለ ቃል መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ አፈወርቅ ዮሐንስ ትምህርተ ወንጌል አስተምሯል።

ብፁዕነታቸው ለምዕመናን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ካሉ በኋላ በመካከላችንም ሆኖ በመስቀሉ አስታረቀን፤ በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛም ወደ ገነት መለሰው”
በሚል ኃይለ ቃል ሰፊ ትምህርት ለምዕመናኑ አስተምረዋል፣ በመቀጠልም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መገንባት ብቻ ሳይሆን ሕንፃ ሥላሴንም በመገንባት
የትውልዱን አእምሮ በመስቀል ላይ የተከፈለውን ዋጋ፣ፍቅር በማስተማር፣ ትውልዱ ሃይማኖቱንና ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያውቅና እንዲጠብቅ በማለት አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ቡራኬና ቃል ምዕዳን በመስጠት መርሐ ግብሩ ተጠናቀቀ።

በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡"ወገብረ ሰላመ ማእከሌነ በመስቀሉ ' / ቅዱስ ኤፍሬም /በመስቀሉ በመካከላችን ሰላም አደረገ / መሠረተ/የ2018 ዓ.ም. በዓለ መስቀል...
27/09/2025

በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
"ወገብረ ሰላመ ማእከሌነ በመስቀሉ ' / ቅዱስ ኤፍሬም /
በመስቀሉ በመካከላችን ሰላም አደረገ / መሠረተ/
የ2018 ዓ.ም. በዓለ መስቀል በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ከኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንዐመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የተስጠ የምስጋና መግለጫ
➢ የተወደዳችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣

ምዕመናንና ምዕመናት ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ
➢ የተከበራችሁ በዓለ መስቀሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በከፍተኛ ድካም ዋጋ የከፈላችሁ የፌዴራል ፣

የአዲስ አበባ ከተማና የሁሉም ክልል የፀጥታ ተቋማትና አባላት ፤
➢ የተከበራችሁ ለበዓሉ ድምቀት ከፍተኛ ድጋፍና እገዛ ያደረጋችሁ አካላትና መላው አትዮጵያዊያን በመሉ ፤

ከሁሉ አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያናችን አጠራር አፈ መዓር ፣ አፈ በረከት እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ እንደገለጸልን የጥልን ግድግዳ በደሙ ፈሳሽነት አፍርሶ በመስቀሉ፤

በመካከላችን ሰላምን የሰራልን ወይም የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይድረሰው እያልን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን አደረሳችሁ።

የዘንድሮው በዓለ መስቀል ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሁሉም የቤተ ክርቲያኒቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትበሙሉ ልዩ የበዓል ዝግጅት ኮሚቴ በማዋቀርና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማትና ልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተቀናጅቶ በጋራ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በመደረጉ በዓሉ ሰላማዊ እና
መንፈሳዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ማክበር ተችሏል፡፡

በመሆኑም ለዚህ ትልቅ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ላበረከታችሁ ቅን አገልጋዮችና መላው ሕዝባችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ምዕራፍ 2 ቁጥር 10 ላይ
" በጎ ሥራን ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላም ይሆንላቸዋል " በማለት እንደገለጸው ሁሉ እኛም የሐዋርውን ቃል አብነት በማድረግ በዓሉ መንፈሳዊ እሴቱን በጠበቀና በደመቀ ሁኔታ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አተዋጽኦ ያበረከቱትን አካላት በሙሉ ማመስገንና ማክበር ስላለብን በዚሁ መሠረት ፦

➢ ገና በዓሉ ከመድረሱ አስቀድሞ ልዩ ዝግጅት በማድረግና ለረጅም ቀናት የሌሊት ቁሩ እና የቀን ሀሩሩ ሳይበግራችሁ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ያለምንም እረፍት ለህዝባችሁ ሰላም ተግታችሁ በመስራትከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የፌዴራል ፣ የሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የፀጥታና መስተዳድር አካላት በሙሉ !
➢ መላው ኦርቶዶክሳዊያንና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች
➢ በተለይም እንደ አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ የበዓሉን ዝግጅት ሙሉ ወጭ በመሸፈን እና የጠየቀውን ሌሎች የሥራ ድጋፎችና ትብብሮች በማድረግ ከፍተኛውን ሚና ለተጫወቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና የካቢኔ አባላቶቻቸው በሙሉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም አስቀድሞ ስለ በዓሉ ዝግጅት ከከተማ አስተዳደሩ እና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ጋር በነበረን ውይይት ወቅት በአጽንኦት እንደገለጽነው ሁሉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንዋየ ቅድሳት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ክብረ ነክ የሆነ ሕገ ወጥ ተግባር በሚፈጽሙት ግለሰቦች ላይ ተገቢው የሕግ እርምት እንዲሰጥልን ባቀረብነው ጥያቄ መሠረት በቅርብ ቀን ስዕለ ቅድስት ድንግል ማርያምን በመቅደድ ሕገ ወጥና አስነዋሪ ተግባር የፈጸመችውን ግለሰብ በሕግ ቁጥጥር ስር በማዋል ለተሰጠን ፈጣን ምላሽ ከፍተኛ ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም እንዲህ አይነቱ ሕግን የማስከበር እና ሕገ ወጥ ግለሰቦችን በሕግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳሰብን በድጋሜ በዓለ መስቀሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ በሙሉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ሁሉ _ ሰላሙን ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን አሜን፡፡

አባ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፡፡

መስከረም 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ በኮዬ መስቀል አደባባይ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።በዓሉ ላይም የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ...
27/09/2025

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ በኮዬ መስቀል አደባባይ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
በዓሉ ላይም የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ በዳሳ ቶላ፣መጋቤ አእላፍ ተስፋዬ ቂጤሳ የሸገር ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊን ጨምሮ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳርዎች፣እንዲሁም ብዙ ምዕመናን ተገኝተዋል

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ክ/ከተማ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።በዓሉ ላይም የሸገር ከተማ ሀገረ  ስብከት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ስዩማን ተስፋዬ ላሜቻ፣ መ...
27/09/2025

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ክ/ከተማ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
በዓሉ ላይም የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ስዩማን ተስፋዬ ላሜቻ፣ መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ የሸ/ሀ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ፣የክ/ከተማው ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የሰበታ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳርዎች፣እንዲሁም ብዙ ምዕመናን ተገኝተዋል

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በገላን ክ/ከተማ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።በዓሉ ላይም የክ/ከተማው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ክፍል ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ታ...
27/09/2025

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በገላን ክ/ከተማ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
በዓሉ ላይም የክ/ከተማው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ክፍል ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ታምራት እንድሪስ ጨምሮ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳርዎች፣እንዲሁም ብዙ ምዕመናን ተገኝተዋል

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በበአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ የተከበረው የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ተከትሎ መልእክት አስተላለፈ።መስከረም ፲፰...
26/09/2025

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በበአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ የተከበረው የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ተከትሎ መልእክት አስተላለፈ።

መስከረም ፲፰/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

#ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ በምልዓተ ሕዝብ ከምታከብራቸው በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው የመስቀል ደመራ በዓል ነው።

#የመስቀል ደመራ በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ በዓል ከመሆኑም በላይ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች በአገራችን ተገኝተው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ሲሆን ለአገራችን የቱሪዝም ዘርፍ መጠናከር አይነተኛ ሚና የሚጫወት በዓልም ነው።

#በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት፣ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ የዋለው የመስቀል ደመራ በዓል ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ መዋል የቻለው በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት፣ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ነው።ይህን ላደረገልን አምላካችን እግዚአብሔርም ምስጋና ይገባዋል።
#መላው ሕዝበ ክርስቲያንም ለቀዓሉ በድምቀት ተከብሮ መዋል ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ክብር ምስጋና ይድረሰው እንላለን።

#በሌላ በኩል በዓላችን ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ተቋማት አመራሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት የበዓሉ ማጠቃለያ ድረስ ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ቅድስት ቤተክርስቲያን ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች።
#በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዓሉ በድምቀት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ከስምንት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሙሉ የበዓል ዝግጅቱን ሥራ በስኬት እንዲከናወን፣በአዲስ አበባ ፓሊስና በከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት በኩል የጸጥታ ሥራውን በሚገባ በመምራት በዓላችን በሰላማዊ መንገድ ተከብሮ እንዲውል ስላደረጉልን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምስጋናዋን ስትገልጽ ለቀጣይ ሥራዎቻቸው ስኬት ዘወትር በጸሎቷ የምታስባቸው መሆኗን ትገልጻለች።

#በመጨረሻም በዓላችን በሰላም ተከብሮ እንዲውል ለደከበማችሁ ለፌዴራል ፓሊስ፣ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና ሥራ ፈጻሚዎች ሁሉ የከበረ ምስጋናዋን እያቀረበች ልዑል እግዚአብሔር ለሥራችሁ ስኬትና ውጤታማነትን እንዲሰጣችሁ የዘወትር ጸሎቷ እንደማይለያችሁ እያረጋገጠች በዓሉ የሰላም፣የደስታ፣የመተባበር ፣የስኬትና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቷን ትገልጻለች።

#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
#መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም

Ayyannii Daamaraa Masqalaa Bara 2018 Biyyaa Lallabaa Magaalaa Shaggar ku/Mag/Galaan Haala miidhagaa ta'een Bakka Itti Ga...
26/09/2025

Ayyannii Daamaraa Masqalaa Bara 2018 Biyyaa Lallabaa Magaalaa Shaggar ku/Mag/Galaan Haala miidhagaa ta'een Bakka Itti Gaafatamaa kutaa Lallabaa Wangeelaa Magaalaa Kooyyee Faccee fi Galaan liqa Lissanaat B/saa Taammiraat Indiiriis ;Bulchitoonni Kawaala,Beekttonni Mana Amaantaa,Bulchaan Bulchiinsaa ku/Magaalaa akkasumaas Ortoodooksoonni heddun argamaniitti kabajameera.
የ 2018 ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሸገር ሀ/ስብከት በገላን ክ/ከተማ በደማቅ ሁኔታ የክ/ከተማው የስ/ወንጌል መምሪያ ኃላፊው ሊቀ ልሳናት መ/ር ታምራት እንዲሪስ ሊቃውንተ ቤተ ክ/ን እንዲሁም የክ/ከተማ አስተዳደር እና በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ።
Maddi:- B/sa Aschalew Kebede

"Ayyaanni Masqalaa karaa nagaa fi duudhaa isaa eeggateen akka kabajamuuf xiyyeeffannoon hojjetameera" Dr. Tashoomaa Addu...
26/09/2025

"Ayyaanni Masqalaa karaa nagaa fi duudhaa isaa eeggateen akka kabajamuuf xiyyeeffannoon hojjetameera" Dr. Tashoomaa Addunyaa
---
Magaalaa Shaggar Kutaalee Magaalaa hundatti sirni Daamaraa ibsuu karaa duudhaa amantichaa eegee fi karaa nagaatiin kabajameera.

Sirna Daamaraa ibsuu akka Magaalaa Shaggaritti Kutaa Magaalaa Eekkaa Xaafootti kabajame irratti Sadarkaa Itti Aanaa Pirezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaatti Kantiibaan Magaalaa Shaggar Dr Tashoomaa Addunyaa fi Ittigaafatamaa Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Magaalaa Shaggar Obbo Alamaayyoo Tulluu dabalatee hoggantoonni magaalaa, Kutaa Magaalaa, abbootiin amantaa fi hordoftoonni amantichaa argamuun gaggeeffameera.

Kantibaan Bulchiinsa Magaala Shaggar Dr. Tashoomaa Adunyaa saganticha irratti yaada kennaniin, Ayyaanni Masqalaa fi Sirni Daamaraa ibsuu ayyaanota dirree irratti saboota sab-lammootaa fi uummattoota biyya keenyaatiin tokkummaa fi obbolummaan kabajaman keessaa isa tokkodha jedhan.

Magaala Shaggarittis, Ayyaanni kun karaa nagaa fi duudhaa isaa eegeen Kutaalee Magaalichaa hunda keessatti bifa hawwataa ta'een kabajamee akka xumuramuuf hawaasa akkasumas hordoftoota amantichaa hirmaachisuun xiyyeeffannoon hojjetamaa jiraachuus eeraniiru.

Madda:- Laike Wengel Lammesa Milkessa

መስቀል መልእልተ ኩሉ ነገር ያድህነነ እምጸር መስቀል ከሁሉ በላይ ነው ከጠላት ያድነናል         ቅ/ያሬድ       በሸገር ሀገረ ስብከት ሱሉልታ እና መነ ዓቢቹ ክ/ከተማ ቤተ ክህነት  ...
26/09/2025

መስቀል መልእልተ ኩሉ ነገር ያድህነነ እምጸር መስቀል ከሁሉ በላይ ነው ከጠላት ያድነናል
ቅ/ያሬድ
በሸገር ሀገረ ስብከት ሱሉልታ እና መነ ዓቢቹ ክ/ከተማ ቤተ ክህነት በመነ ዐቢቹ ክፍለ ከተማ ስር በሚገኘው ቱፋ ሙና ደ/ሰ/ቅ/ጊዮርጊስ አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል ብዙ ምእመናን በተገኙበት ልዩ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ ዋለ።

የደመራ በዓል አከባበር በፎቶ መስከረም 16 /2018 ዓ/ምሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ
26/09/2025

የደመራ በዓል አከባበር በፎቶ
መስከረም 16 /2018 ዓ/ም
ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

26/09/2025

ቀጥታ ሥርጭት ከመስቀል አደባባይ Tamsaasa kallattii Addababayii Masqaala irraa

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share