addisadmassnews.com

addisadmassnews.com Addis Admass is a private company Established in 1992 e.c

05/07/2025

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

ቢያትሪስ ችቤት የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈችበኢዩጂን ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ችቤት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።ችቤት 5 ሺህ ሜትርን ...
05/07/2025

ቢያትሪስ ችቤት የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች

በኢዩጂን ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ችቤት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።

ችቤት 5 ሺህ ሜትርን ከ14 ደቂቃ በታች የገባች የመጀርያዋ ዕንስት አትሌት ሆናለች።

ቢያትሪስ ችቤት በአትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ነው ያሻሻለችው።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደየ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ፣ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል። ድርጅቱ በሚያንቀሳቅሰው የበይነ መረብ...
05/07/2025

የ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

የ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ፣ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል። ድርጅቱ በሚያንቀሳቅሰው የበይነ መረብ አገልግሎት ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ተጠቃሚዎች ሽልማት መበርከቱን ለማወቅ ተችሏል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን ተቋም ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክብሮም ገብረመስቀል ባደረጉት ንግግር፣ ይህ የስፖርት ፌስቲቫል ወጣቶች የስፖርት ዕንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ይኸውም በዚህ የክረምት ወቅት ወጣቶች ከአልባሌ ቦታ እንዲርቁ የሚያግዝ መሆኑን አመልክተዋል።

ፌስቲቫሉ ከሰኔ 28 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚከናወን መሆኑን ያመለከቱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ “ይህ ፌስቲቫል አንድ ጊዜ ተጀምሮ የሚቋረጥ አይደለም” ብለዋል። እንዲሁም ከዳርት እና እግርኳስ ፌዴሬሽኖች በጥምረት በመስራት ፌስቲቫሉን የተሳካ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

አቶ ክብሮም አያይዘውም፣ ፌስቲቫሉ በአዲስ አበባ፣ መቐለ እና አርባምንጭ ከተሞች እንደሚካሄድ የጠቆሙ ሲሆን፣ የክልል ፌዴሬሽኖች የፌስቲቫሉ አንድ አካል በመሆን በዝግጅት ሂደቶች ውስጥ መሳተፋቸውን አስታውቀዋል። በፌስቲቫሉ በሚካሄዱ የስፖርት ውድድሮች አሸናፊ ለሚሆኑ ተሳታፊዎች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉበት ዕድል እንደሚመቻች ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

ከማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በተጨማሪ፣ ሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን አበልጽጎ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ወደ ስራ ባስገባው “ሁሉ ስፖርት” የበይነ መረብ አገልግሎት ተሳታፊ ለሆኑና በአገልግሎቱ ላይ ገንዘብ ተቀማጭ በማድረግ የዕጣ ቁጥሮች ደርሰዋቸው ዕድለኛ ለሆኑ ተጠቃሚዎች የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተዋል። አቶ ለዓለም ገብረኪዳን ከትግራይ፣ መቐለ ከተማ በቀዳሚነት የBYD SEAGULL የኤሌክትሪክ መኪና ተሸላሚ ሲሆን፣ አቶ ይብራህ ፈተዊ ከዓድዋ የኤሌክትሪክ ሳይክል፤ አቶ ጫላ ኦላኒ ከጋምቤላ ስማርት ስልክ፤ አቶ አማኑኤል ኢዮብ ከሃላባ ቁሊቶ ፕሌይ ስቴሽን እና አቶ ምናየው ንጉሴ ከአርባ ምንጭ የስማርት ቴሌቪዥን ተሸልመዋል።

ሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን ከስምንት ዓመታት በፊት ተመስርቶ፣ “ሁሉ ስፖርት” የተሰኘ አገር በቀል የበይነ መረብ አገልግሎት አበልጽጎ ወደ ስራ መግባቱ በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ሲታወስ፣ ከ100 በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የ2014 እና 2016 ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆን ከገቢዎች ሚኒስቴር የዕውቅና ሽልማት እንደተበረከተለት ነው የተገለጸው።

”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል”ን በዓመት ሁለት ጊዜ ለማካሄድ ዕቅድ እንዳለው የገለጸው ተቋሙ፣ በየዓመቱ 5 በመቶውን የተጣራ የድርጅቱን ትርፍ “ትርጉም ላለው” የማሕበረሰብ አቀፍ ተግባራት ፈሰስ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

05/07/2025
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን  በበላይነት አጠናቀቁ  በኢዩጂን በተደረገ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል።አትሌት ቢኒያም መሀሪ ውድድሩን በ...
05/07/2025

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀቁ

በኢዩጂን በተደረገ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል።
አትሌት ቢኒያም መሀሪ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፤ አትሌት በሪሁ አረጋዊ ደግሞ 2ኛ ወጥቷል።
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በ3ኝነት አጠናቋል፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የልብ ሕመምና ካንሰርን ለመቀነስ የታክስ ጭማሪ?! * የዓለም ጤና ድርጅት ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮልና የስኳርመጠጦች ላይ ታክስ እንዲጨምሩ አሳሰበ• በ10 ዓመታት 1 ትሪሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ...
05/07/2025

የልብ ሕመምና ካንሰርን ለመቀነስ የታክስ ጭማሪ?!

* የዓለም ጤና ድርጅት ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮልና የስኳር
መጠጦች ላይ ታክስ እንዲጨምሩ አሳሰበ

• በ10 ዓመታት 1 ትሪሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታልሟል

የዓለም ጤና ድርጅት መንግስታት በሲጋራ፣ በአልኮልና በስኳር የተሞሉ መጠጦች ላይ ታክስ እንዲጨምሩ አሳስቧል። ይህ የታክስ ጭማሪ የ50 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ እንደሚችል ድርጅቱ ገልጿል።

የጤና ድርጅቱ በ2035 በእነዚህ ምርቶች ላይ የሚጣለውን ታክስ በ50 በመቶ ከፍ ለማድረግ ያለመ "3by35" የተሰኘ ንቅናቄ የጀመረ ሲሆን፤ ንቅናቄው ገቢ ከማስገኘት ባሻገር እንደ ልብ ሕመምና ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመቀነስ የሰዎችን ሕይወት ይታደጋል ብሏል።

በአሁኑ ወቅት እነዚህ በሽታዎች 75 በመቶ የሰው ልጅ ሞት ምክንያት እየሆኑ ነው ብሏል፤ ድርጅቱ፡፡

የታክስ ጭማሪው የምርቶቹን ፍጆታ በመቀነስ ለመንግሥታት ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝ የተገለጸ ሲሆን፤ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ከታክስ ጭማሪ 1 ትሪሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታልሟል፡፡ ገንዘቡም ለሀገራት ልማትና ጤና ተደራሽነት ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።

(ቅዳሜገበያ)

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የሱዳን ባለሥልጣናት ኢትዮጵያን ከሰሱየኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው በማለት የሱዳን ባለሥልጣ...
05/07/2025

የሱዳን ባለሥልጣናት ኢትዮጵያን ከሰሱ

የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው በማለት የሱዳን ባለሥልጣናት መክሰሳቸውን ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ የሱዳን ጦር አካባቢውን ከኢትዮጵያ ታጣቂዎች ለማስለቀቅ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የሱዳን ጦር ሠራዊት፣ ሁለቱ አገሮች የሚወዛገቡበትን አልፋሽጋ የተባለ አካባቢ ከአምስት ዓመታት በፊት ከአማራ ክልል አርሶ አደሮችና ታጣቂዎች በማስለቀቅ በኃይል መቆጣጠሩን ዋዜማ በዘገባዋ አስታውሳለች፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

"ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ ተሰጥቷል "ከሀገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ገለጸ፡፡ባለስልጣኑ የተቋማዊ ሪፎርም...
05/07/2025

"ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ ተሰጥቷል "

ከሀገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትና የዴሞክራዊ ተቋማት የጋራ መድረክ ላይ ሪፖርት አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናታን ተስፋዬ እንዳሉት፤ ባለስልጣኑ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የሚዲያ ነፃነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን ሰርቷል።

የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑንም አብራርተዋል።

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ማድረጉንም ነው ያስረዱት፡፡

ከለውጡ በፊት በዘርፉ የሚሰሩ የሙያና ሲቪክ ማህበራት ከ6 የማይበልጡ እንደነበሩ ጠቅሰው፣ ለውጡን ተከትሎ 38 ማህበራትና አደረጃጀቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በትምህርት በማህበረሰብ ሬዲዮ፣ በሃይማኖት፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ ላይ ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃን ቁጥር መጨመሩን ጠቁመዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሃኑ የቋንቋ ተደራሽነትም ከነበረበት 39 አሁን ላይ ወደ 63 ከፍ ማለቱን ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚው አመልክተዋል።

(fmc)

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የሩሲያና ኤርትራ የትብብር ኮሚሽን
05/07/2025

የሩሲያና ኤርትራ የትብብር ኮሚሽን

በደራሲ ንጉስ አየለ የተጻፈው "ኦዛና ምኒልክ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ በተካሄደ መርሐ ግብር  ተመርቋል።መጽሐፉ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመን...
05/07/2025

በደራሲ ንጉስ አየለ የተጻፈው "ኦዛና ምኒልክ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ በተካሄደ መርሐ ግብር ተመርቋል።

መጽሐፉ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመን መንግሥት የነበሩ አዳዲስ ክስተቶችን በመረጃ ላይ በመመርኮዝ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የዓፄ ምኒልክን አስተዳደራዊ፣ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ ያደረጓቸውን ጥረቶች በጥልቀት ይዳስሳል ተብሏል።

በምረቃው ሥነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ደራሲ ንጉስ አየለ፤ መጽሐፉ የአንባቢያንን የታሪክ ግንዛቤ እንደሚያሰፋና በዘመነ ምኒልክ ስለተከናወኑ ዋና ዋና ክስተቶች አዲስ እይታን እንደሚያቀርብ አብራርተዋል፡፡

በ440 ገጾች ተቀንብቦ በ18 ምዕራፎች የቀረበው "ኦዛና ምኒልክ"፣ በ1000 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን፤ በቅርቡ በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮችና አከፋፋዮች እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

ህወኃት ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ለሰጡት ሃሳብ ምን አለ ?ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ትግራይን  በተለይም የተከፋፈሉትን የህወሓት አመራሮች አስመልክቶ ለሰጡት ...
05/07/2025

ህወኃት ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ለሰጡት ሃሳብ ምን አለ ?

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ትግራይን በተለይም የተከፋፈሉትን የህወሓት አመራሮች አስመልክቶ ለሰጡት ሃሳብ ህወኃት ባለ 3 ነጥብ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ምን አለ?

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

አርቲስት ተስፋዬ ሣህሉ  (አባባ ተስፋዬ)በራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ተደርሶ በአሌክዛንደርን ሪቻርድ የተዘጋጀው "አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም" የተሰኘው ቲያትር ላይ አርቲስት ተስፋዬ ሣ...
05/07/2025

አርቲስት ተስፋዬ ሣህሉ (አባባ ተስፋዬ)

በራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ተደርሶ በአሌክዛንደርን ሪቻርድ የተዘጋጀው "አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም" የተሰኘው ቲያትር ላይ አርቲስት ተስፋዬ ሣህሉ በሚተውኑበት ወቅት ፤

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ፤ 1952 ዓ.ም

(ታሪክን_ወደኋላ)

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

https://t.me/AdissAdmas

Address

Kirkos Subcity, Kebele 31 House No. 376
Addis Ababa
1232

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when addisadmassnews.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to addisadmassnews.com:

Share

በአሰፋ ጎሳዬ ላይ ያተኮረ በእዝራ እጅጉ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም

https://youtu.be/ycTXiwjGZfI

https://www.youtube.com/channel/UC4Gc6hka1S4utimVYa6vZHg/feature