Ethio News -ኢትዮ መረጃ

Ethio News -ኢትዮ መረጃ We are here to provide you true and fair informations....

Iran said it hit Mossad building with missile+++++++++++++++++++++  | Iran has announced that it has hit the Mossad buil...
17/06/2025

Iran said it hit Mossad building with missile
+++++++++++++++++++++

| Iran has announced that it has hit the Mossad building in Herzliya with a missile.

Iran military reports that the military information and Mossad building north of Tel Aviv has been hit with missiles.

The Russian Sputnik News Service and Almayadin TV reported that there was a real missile attack this morning.

It is said that the attack between the two sides indicates that the military deterioration is increasing.

According to the sources, the missile directly targeted the building.
There is no officially confirmed death of material and human in Israel.

As the commander of Iran's land force told the Iranian government media, the attacks on Israel's strategic locations will be intensified using advanced weapons in the coming hours.

Herzliya is the main center of Israel's spying activities; the action taken on the center is feared that the two countries will be in a serious conflict.

In the Arabic language.
++++++++++++++++

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#እስራኤል #ኢራን #ሞሳድ

አዲስ የተሾሙት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ በእስራኤል ተገደለ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ እና ከአገዛዙ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑትን አሊ ሻድ...
17/06/2025

አዲስ የተሾሙት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ በእስራኤል ተገደለ።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ እና ከአገዛዙ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑትን አሊ ሻድማኒ መገደሉን አስታውቋል።

ዋና አዛዡ የተገደሉት በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ መሆኑም ተዘግቧል።

🚨 ፕሬዝደንት ትራምፕ:-     "ማንኛውም በቴህራን የሚገኝ ሰው ከተማዋን ለቆ ይውጣ"
17/06/2025

🚨 ፕሬዝደንት ትራምፕ:-

"ማንኛውም በቴህራን የሚገኝ ሰው ከተማዋን ለቆ ይውጣ"

ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ሰላም ማምጣታቸውን ተናገሩ! 🇪🇹🇪🇬የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያ...
17/06/2025

ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ሰላም ማምጣታቸውን ተናገሩ! 🇪🇹🇪🇬

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት የነበራቸውን ውጥረት በማብረድ “ሰላም” እንዳመጡ ገለፁ።

ይህንን ያሉት ሰኔ 8/2017 ዓ.ም (June 15, 2025) በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው።

ትራምፕ፣ በእስራኤል እና ኢራን ግጭት ዙሪያ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራቱ ወደ ስምምነት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም በህንድና ፓኪስታን መካከል የነበረውን ግጭትም “ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ንግድን” በመጠቀም መፍታት እንደቻሉ አስታውሰዋል።

በተጨማሪም፣ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው በሰርቢያና ኮሶቮ መካከል “ለአስር ዓመታት” የዘለቀውንና ወደ ጦርነት ሊያመራ የነበረውን ግጭት ማስቆማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

🔴🙏ተዓምር ነው 🙏🔴  | የሳውዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ አል-ዋልድ ቢን ካሊድ ከ20 አመታት በላይ ኮማ ውስጥ ከቆየ በኋላ በመጨረሻ መንቃታቸው ተነግሯል። እ.ኤ.አ. በ 2005 ከባድ የመ...
17/06/2025

🔴🙏ተዓምር ነው 🙏🔴

| የሳውዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ አል-ዋልድ ቢን ካሊድ ከ20 አመታት በላይ ኮማ ውስጥ ከቆየ በኋላ በመጨረሻ መንቃታቸው ተነግሯል።

እ.ኤ.አ. በ 2005 ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሞት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርጎ ነበር ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለ 20 ዓመታት ኮማ ውስጥ ነበር በዚህ ዓመት ሚያዝያ 18 ቀን 36 ዓመቱን ሞልቶ ነበር።

ዶክተሮቹ ከህይወቱ እንዲቋረጥ ምክረ ሃሳብ ሰጥተው ነበር ነገር ግን ቤተሰቡ እምቢ ብለው እንደሚያገግም ተስፋ አድርገው ሳይቀበሉት ቆይተዋል

ገንዘብ አንዳንድ ጊዜ ህይወትን ሊገዛ ይችላል እንበል?

የኔታ ትዩብ

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የ  #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸውየ  #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራ...
13/09/2024

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው

የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴም ከተከሳሾቹ መካከል ነው።

ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት ፣ አትሌት ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው።

በከሳሾቹ ጠበቆች በኩል ክሱ የቀረበለት የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራድ ምድብ ችሎት ኮሚቴው፤ ግንቦት 5 እና ሰኔ 4፤ 2016 ዓ.ም. ያካሄዳቸው ጠቅላላ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች እንዲታገዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ አያሌው ቢታኔ “ከፓሪስ ኦሊምፒክ ጋር በተያያዘ [ተከሳሾቹ] ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል ብለን እንጠረጥራለን። የወንጀል ተጠያቂነቱ እንዳለ ሆኖ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም ኦሊምፒክ ኮሚቴውን [በዝብዘዋል]” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጠበቃው አክለው “ደብዳቤ ስለተጻፈ ብቻ የማይመለከተው ሰው [ወደ ፓሪስ] ይሄድ ነበር” ብለዋል።

የአቶ ታዬ የዋስትና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይቀበለው ቀረየቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት...
04/09/2024

የአቶ ታዬ የዋስትና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይቀበለው ቀረ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ በችሎቱ ውድቅ ተደረገ።
አቶ ታዬ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ይግባኝ የጠየቁት ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም. በነበረ ችሎት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገ በኋላ ነው።
የቀድሞ ሚኒስትር ዲኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባሉ ፀረ ሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚሉ ወንጀሎች ተከሰው ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል።

ዐቃቤ ሕግ አቶ ታዬ ደንደአ መገናኛ ብዙኃን እና ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሁከት የሚያስነሱ እና “ፀረ ሰላም የሆኑ የኦነግ-ሸኔ እና ፋኖ ኃይሎችን” ዓላማዎች የሚያሳኩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር እንዲሁም ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የሚሉ ሦስት ክሶች መስርቶባቸው እንደነበረ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ አቶ ታዬ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያጋሯቸው ጽሑፎች የሰላም ጥሪ እንጂ ሁከት ቀስቃሽ አለመሆናቸውን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው የተገኘው ጦር መሳሪያ መንግሥት ለደኅንነታቸው ሲባል ያስታጠቃቸው መሆኑን በመናገር ከዚህ ቀደም ተከራክረዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አቶ ታዬ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ሁከት የሚያስነሱ መሆን አለመሆናቸውን እንዲሁም የሕዝብ ሞራል እና የግለሰቦች መብትን የሚጣረሱ መሆን አለመሆናቸውን መመርመሩን ገልጿል።

በዚህ መሠረት አመጽ መቀስቀስ እና ፀረ ሰላም ኃይሎችን መደገፍ በሚል የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው አቶ ታዬ ነጻ ተብለው በሦስተኛው ክስ ግን እራሳቸውን እንዲከላከሉ ተወስኗል።
ይህን ተከትሎ አቶ ታዬ በዕለቱ (ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም.) ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች መካከል በሁለቱ ነጻ መባላቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር።

ይሁን እንጂ የአቶ ታዬ እንዲከላከሉ የታዘዙበት ክስ እስከ 20 ዓመት የሚያስቀጣ ነው በማለት የዋስትና ጥያቄያቸውን ዐቃቤ ሕግ ተቃውሞ ተከራክሯል። ችሎቱም የዐቃቤ ህግን መከራከሪያ በመቀበል የአቶ ታዬ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ታዬ ይግባኝ ሲሉ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም በጠበቆቻቸው ላይ ማስፈራራት እየደረሰ በመሆኑ ብቻቸውን ችሎት ፊት ቀርበው የነበሩት አቶ ታዬ፤ በዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 29/2016 ዓ.ም. በነበረው ችሎትም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ያለ ጠበቃ ነበር የተገኙት።

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ውሎው አቶ ታዬ የተከሰሱበት ሦስተኛው ክስ ከ8-25 ዓመታት በእስር እንደሚያስቀጣ እንዲሁም ተከሳሹ በሚፈለጉበት ጊዜ ፍርድ ቤት ላይቀርቡ ይችላሉ በሚል የታችኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን አጽንቷል።

አቶ ታዬ በቀረበባቸው ሦስተኛው ክስ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ለጥቅምት 8/2017 ዓ.ም. ለተዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።(BBC)

ዛሬ  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲግራት ከተማ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል ደማቅ የሚባል  ነው። በከተማው ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
04/09/2024

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲግራት ከተማ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል ደማቅ የሚባል ነው።

በከተማው ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቻይና ተወያይተዋል።ለይፋ...
04/09/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቻይና ተወያይተዋል።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቻይና ሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ላካሄዱት ጠቃሚ ውይይት ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንደስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል ብለዋል።

አያይዘውም በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ሲሉ ነው የገለጹት።

በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና እንደ ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንደስትሪንም ለማሳደግ እምቅ አቅም አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በጽናት እንሰራለን ብለዋል።

የግፍ ጎርፍ ራስን  ይወስዳል! የግፍ እሳት ራስንም ያቃጥላል!  ከአዘነ ጋር የሚያዝኑት፣ እናት የሌላቸውን ሕጻናት አጥብተው የሚያሳድጉት፣ የጎረቤት ልጅ እንደ ራስ ልጅ የሚቀጡት፣  ሕግና ሥ...
03/09/2024

የግፍ ጎርፍ ራስን ይወስዳል! የግፍ እሳት ራስንም ያቃጥላል!

ከአዘነ ጋር የሚያዝኑት፣ እናት የሌላቸውን ሕጻናት አጥብተው የሚያሳድጉት፣ የጎረቤት ልጅ እንደ ራስ ልጅ የሚቀጡት፣ ሕግና ሥርዓት የሚያስተምሩት፣ ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ እያሉ የሚናገሩት የት ገቡ? ለሕጻናት የሚያዝኑ እንጀቶች፣ ለሕጻናት የሚንሰፈሰፉ ሆዶች፣ ለሕጻናት የሚራሩ ልቦች ምን አስቆረጣቸው ? ምንስ አስጨከናቸው?

የት እየሄድን ነው? በሕጻናት ላይ መጨከን እንደምን ያለ ጭካኔ ነው? ሕጻናትን መግደለስ እንደምን ያለ አገዳደል ነው? እንባቸው አያሳዝንምን ? ዋይታቸው አያንሰፈስፍምን? ለቅሷቸው አንጀት አይበላምን? ኮልታፋ አንደበታቸው የጨካኝን ልብ አያራራምን? ፍቅራቸው ጥላታቻን አያርቅምን? የልጅነት ወዛቸው ከክፋት አይመልስምን? ያልጠናው ገላቸው ልብ አይነካምን? ስለ ምን ተጨከነባቸው? ስለ ምንስ ተቆረጠባቸው?

ዓይን እንዳይበዛቸው ሸፍኗቸው፣ በሰው ፊት አትግለጧቸው፣ በምሽት ከቤት አታውጧቸው እየተባሉ ጥንቃቄ የሚበዛላቸውን፣ አብዝቶ የሚሳሳላቸውን ሕጻናትን ለመግደል እንደምን ተቻላችሁ? እንደምንስ ኾነላችሁ? ጭካኔውንስ ከየት አገኛችሁት ? ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አስተምረዋልን? ኢትዮጵያን እንኳን ለሰው ልጅ ለአዕዋፋት ልጆች የሚያዝኑ፣ እናት የሞተችባትን የፍየል ግልገል ወተት አጠጥተው የሚያሳድጉ አይደሉምን? ከየት መጣችሁ? ማንስ ይሄን የጭካኔ ሀሳብ በልባችሁ ጻፈላችሁ? የአጨካከንም ልክ አለው፣ የአገዳደልም ወግ አለው እኮ።

በማሕጸኗ የተሸከመች፣ አምጣ የወለደች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ እየተራበች ያጎረሰች፣ እየተጠማች ያጠጣች፣ እየታረዘች ያለበሰች፣ እንቅልፍ አጥታ ለልጇ የኖረች እናት አታሳዝንምን? ለልጆቹ ሲል በችግር የሚኖር፣ ሀዘኑን በልጆቹ ደስታ የሚረሳ፣ ለእነርሱ ሲል ዓለሙን የተወ አባትስ አያሳስብምን? አምላክ ለዘር እንዲያበቃቸው የተማጸኑ ወላጆች አያሳዝኑምን?

እንደዚህ መክፋትስ ለማን ይበጃል? የዘሩትን ማጨድ፣ በሰፈሩት ቁና መሠፈር አይመጣምን? በራስ እንዲኾን ያልፈለጉትን በሰዎች ላይ ማድረግስ የተገባ ነውን ? ከሚደሰቱት ጋር ተደሰቱ፣ ከሚያዝኑትም ጋር እዘኑ እየተባለ በሚሰበክባት ሀገር፣ ደግነት እንደ ምንጭ ውኃ ሲፈስስባት በኖረች ምድር እንደዚህ ማድረግ ጤነኝነት ነውን ? የግፍ ጎርፍ እኮ ራስንም ይወስዳል። የግፍ እሳት እኮ ራስንም ያቃጥላል። ለሰው የተቆፈረ መቃብር እኮ ለራስም ይኾናል። በግፍ የፈሰሰ ደም እኮ በምድርም በሰማይም ይጮሃል። ለምህረት የተጠበቀው ሰማይ እኮ ለማዕት የታዘዘ መከራ ያወርዳል።

የሕጻን ሄቨን ለቅሶ እና ሀዘን ሳይጠፋ፣ የፈሰሱ እንባዎች ሳይታበሱ፣ ያጠላው የድንጋጤ ድባብ ሳይገፈፍ ሌላ አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሟል። ለወትሮው ከሀዘን ማግስት ሀዘን የሚያስረሳ ተድላና ደስታ ይሰማ ነበር። ዛሬ ግን ሌላ መከራ፣ ሌላ ሀዘን፣ ሌላ እምባ፣ ሌላ አንጀት የሚቆርጥ መርዶ ተሰምቷል።

ኖላዊት ዘገዬ የተባለች ሕጻን በጎንደር በአጋቾቿ ተገድላ ኑ ሬሳችሁን አንሱ የሚል መርዶ መጥቷል። ከጡት ያልተለየች ሕጻን በአጋቾች ተወስዳ፣ በረሃብ እና በናፍቆት አልቅሳ በመጨረሻም በጨካኝ እጆች ላትመለስ አልፋለች። የወላጆቿን አንጀት ቆርጣ ያለ በደሏ አሸልባለች። ከዘሀኑም የከፋው ሀዘን ደግሞ ሕጻን ኖላዊት ከእገታ እንድትላቀቅ ብር ተጠይቆባት ነበር። ወላጆችም ልጃቸውን ለማስለቀቅ ብሩን ከፍለው ነበር። ዳሩ ግን ልጃቸውን አላገኟትም። በሕይወት አልተመሰለችም። ሬሳቸው ተላከላቸው እንጂ።

ብሩን ተቀብለው ሕጻኗን የገደሏት። ከበደልም የከፋው በደል ተፈጽሟል። ሕጻን እያስለቀሳችሁ ከዚያም ጨክናችሁ ገድላችሁ በተቀበላችሁት ገንዘብ ሊታጌጡበት ነውን? ወይንስ ልጅ ልታሰደጉበት ነው? ግፍ አይደርሳበችሁምን?

የዚያች ታሪካዊት እና ቀደምት ከተማ ጎንደር ነዋሪዎች፣ ደጋጎቹ አዝነዋል። ከማንነታቸው፣ ባሕላቸው እና ከልካቸው የወጣ ክፉ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋልና አንብተዋል። እነርሱ የሚያውቁት ታላቅን ማክበር፣ ታናሽን እየወደዱ ማሳደግ እንጂ እንዲህ አይደለምና። በቀያቸው ተደርጎ የማይታወቅ ነገር ተደርጎባቸዋልና። እነርሱ የሚያውቁት ያዘነን ማጽናናት ነውና እያዘኑ ነው።

እሺ ሕዝብ እትብቱ ከተቀበረበት፣ ተወልዶ ካደገበት፣ አግብቶ ወግ ማዕረግ ካየበት፣ ምድር ርቆ የት ይሂድላችሁ ? ምን ያድርግላችሁ ? ስለ ምን መከራውን ታበዙበታላችሁ ? ስለምንስ ሰቃዩን ታጸኑበታላችሁ? ለምን በሰላም እንዲኖር አትተዉትም? ለምን በቆዬው በባሕሉና እሴቱ እንዲኖር አትፈቅዱለትም? መከራው በዛ እኮ። ሰቃዩ በረታበት እኮ። መሳቀቅ ይበቃዋል። የጥይት ድምጽ ሰልችቶታል። እያነሱ መቅበር መሮታል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ግፍና በደል እንደቦይ ውኃ እየፈሰሰ ነው። በየቀኑ ንጹሐን ይታገታሉ፣ ለፍቶ አዳሪዎች ይታፈናሉ። በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ይጠየቃሉ። መክፈል የሚችሉ ጥሪታቸውን ሰጥተው ይለቀቃሉ። መክፈል የማይችሉ ደግሞ በአጋቾች አፈሙዝ ተበልተው የወገን ጸጸት ኾነው ይቀራሉ። ሕጻን ኖላዊትም የኾነችው እንዲሁ ነው።

ግፍና እንግልቱ ሊገልጹት፣ ሊናገሩት፣ ሊጽፉትና ሊተርኩት ከሚችሉት በላይ ኾኗል። በሕጻን ሄቨን እንዲያቆም የታሰበው ግድያ በሕጻን ኖላዊት ቀጥሏል። እኒያ መልካም እሴቶች ካልተመለሱ፣ ነውር የሚፈጽሙት፣ ግፍን የሚያደርጉት ካልተወገዙ፣ ከሰው ካልተለዩ ነገም ላለመቀጠሉ ዋስትና የለም።

ግን የት እየሄድን ነው? መድረሻችንስ የት ነው? ግባችንስ ምንድን ነው? ስንት ሕጻናት ሲሞቱ ነው የሚቆጨን ? ስንት ንጹሐን ሲያልቁ ነው የሚያንገበግበን ? መቼ ነው በቃ የምንለው ? ዛሬ ከንፈር መጥጠው ቢያሳልፉት ነገ በየቤቱ ይደርሳል። ዛሬ እንደዋዛ ዝም ቢሉት አንዳንድ እያለ ሁሉንም ይወስዳል። ሁሉም ከመወሰዱ፣ ግፈኞች በንጹሐን ላይ ከመሰልጠናቸው አስቀድሞ በአንድነት፣ በኅብረት እና በቁርጠኝነት በቃን ብሎ መነሳት፣ በጋራም ሰላምን መጠበቅ ግድ ይላል። ያ ካልኾነ ግን ከንፈር መምጠጡ ይቀጥላል። ሞቱም እንደዚያው ይኾናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠየኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡አየር መ...
03/09/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር ነው፡፡

ስለሆነም ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ ሲያደርግ የነበረውን በረራ እንደሚያቋርጥ አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ወደ አስመራ ለመጓዝ ቀድመው ትኬት ለቆረጡ መንገደኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌሎች አየር መንገዶች የሚጓጓዙበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች አመልክቷል፡፡

አሊያም እንደአማራጭ በደንበኞቹ ፍላጎት ለትኬት የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉውን ተመላሽ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው፡፡

ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ በደንበኞች ላይ ለሚፈጠረው መጉላላት አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ የግብርና መስኮች ላይ በትብብ...
03/09/2024

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ የግብርና መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አሕመድ እና የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ሊቀመንበር ቢል ጌትስ ናቸው በጋራ የፈረሙት፡፡

ኃላፊዎቹ በተለይም በወተትና ወተት ተዋፅኦ፣ በዶሮ እርባታና በምርጥ ዘር ምርምር ላይ በማተኮር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሚድሮክ ኢንቨስትምንት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912230944

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News -ኢትዮ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share