Capital city of Africa

Capital city of Africa ✊🏾 United we stand, divided we fall. Showcasing the vibrant spirit, diverse cultures, and collective strength of a United Africa. 🌍❤️ Join the movement!

27/06/2026

I HATE POLITICS 😡

11/05/2026
08/05/2026


በፌደራል ፖሊስ እና በባለሀብቷ በረከት ወርቁ መካከል ያለው ውጥረት አይሏል!የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የኢኮኖሚ ጉዳት አድርሰዋል ያላቸውን አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማ...
08/05/2026

በፌደራል ፖሊስ እና በባለሀብቷ በረከት ወርቁ መካከል ያለው ውጥረት አይሏል!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የኢኮኖሚ ጉዳት አድርሰዋል ያላቸውን አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የህዝብ ትብብር መጠየቁን አስታውቋል።

ፖሊስ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በረከት ወርቁ አደራ፣ ጌታቸው አምሻ ያየሁ፣ ይልቃል የኔሰው ዘለቀ እና አቡሽ አየለ ገነት የተባሉ ግለሰቦች በፈጸሙት ወንጀል ምክንያት በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁሟል።

እነዚህ ግለሰቦች ያሉበትን ስፍራ ወይም ማንኛውንም መረጃ ያላቸው ዜጎች በ011-111-9475 ደውለው ጥቆማ እንዲሰጡ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላለፈ ሲሆን፣ የጠቆሚዎች ምስጢራዊነትም ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ እንደሚሆን አረጋግጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዝርዝሩ ውስጥ ስሟ የተጠቀሰው ባለሀብት በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ) በወንጀል መፈለጓን ተከትሎ ከባድ ውንጀላዎችን የሰነዘረችበት ምላሽ ሰጥታለች።

ባለሀብቷ ከእርሻ ስራዋ ወጥታ ወደ ወርቅ ማዕድን ዘርፍ መግባቷን እንደምትቆጭ ገልጻ፣ ስምንት ሚሊዮን ብር ሀገር አሳጣሽ መባሏን በማጣጣል "እናንተ ራሳችሁ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወስዳችሁብኛል" ስትል ስማቸውን ያልጠቀሰቻቸውን አካላት ወንጅላለች።

በተጨማሪም የተፈቀደላትን ነዳጅ እንዳልወሰደችና ሌሎች አካላት ሸጠው እንደበሉት በመጥቀስ፣ ድርጊቱ እሷን ከመንገድ ለማስወገድ የተጠነሰሰ ሴራ እንደሆነ ገልጻለች።

ባለሀብቷ አብሮት ስሙ የተጠቀሰው አቡሽ አየለ 28 የሚደርሱ የወርቅ ማውጫዎች ያሉትና ለብሔራዊ ባንክ በኩንታል ወርቅ የሚያስገባ መሆኑን በመጥቀስ፣ በወርቅና ነዳጅ ዘርፍ ያሉ ጥቂት ቡድኖች ሌሎች ተወዳዳሪዎች እንዲወገዱ እያደረጉ ነው ስትል ተናግራለች።

"መጨረሻውን አብረን እናያለን" በሚል መልእክት ምላሽዋን የደመደመችው በረከት ወርቁ፣ ከዚህ ድርጊት ጀርባ ያሉ ግለሰቦች እጃቸውን እንዲሰበስቡ አሳስባለች።

በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በፖሊስ የክትትል ሂደት እና በባለሀብቷ የመከላከል ምላሽ መካከል ሆኖ ከፍተኛ ህዝባዊ ትኩረትን ስቧል።

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

08/05/2026

يتاثر الوحل يتاثر الوحل



#🇪🇹

08/05/2026

አማርኛ አማርኛ የሚለው ግለሰብ ንግግሩ ከንግድ ሥነ-ምግባር (Professionalism) አንጻር ሲታይ ክፍተት አለበት።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Capital city of Africa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Capital city of Africa:

Shortcuts

Share