Enderase MEDIA

Enderase MEDIA This is official Page Of Enderase Media

Be discovered daily with latest news and informations about Ethiopia
from...
Related PageBe discovered daily with latest news and informations about Ethiopia
from...
Related Pagess

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ እንዲሉ...8ኛው ሺህ ማለት አሁን ነው!ኦጂ የተባለ ናይጄሪያዊ ወጣት እናት ልጅን ማስረገዙ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡😯🤔ኦጂ መጀመሪያ የፍቅር ግኙነት የነበረው ከልጅቷ...
16/09/2025

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ እንዲሉ...8ኛው ሺህ ማለት አሁን ነው!

ኦጂ የተባለ ናይጄሪያዊ ወጣት እናት ልጅን ማስረገዙ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡😯🤔

ኦጂ መጀመሪያ የፍቅር ግኙነት የነበረው ከልጅቷ ጋር ቢሆንም ልጅቷ ለእናቷ ኦጂ በደንብ እንደሚንከባከባት እና ጥሩ የፍቅር ጊዜ እያሳለፈች እንደሆነ ትነግራታለች፡፡

በዚህ ጊዜ እናት የልጇ ጓደኛ ላይ ፍላጎት ያድርባታል ፣ በመጨረሻም እናቷም ለኦጂ ጥያቄ ታቀርብና ልጇም ትስማማ እና እናት እና ልጅ በኦጂ ፍቅር ጭልጥ ይላሉ፡፡ ከዛም በተመሳሳይ ሁኔታ ያረግዛሉ፡፡

እናት ወንድ ልጅ ልጅ ደሞ ሴት ልጅ እንደሚወልዱ በሃኪም ተረጋገጠ፡፡ ኦጂንም ሰርፕራይዝ አደረጉት፡፡ አሁን እናት እና ልጅ በቅርቡ የልጅ እናት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

የወንዶች ጉዳይ....👏 ሊመለስ ነው
18/08/2025

የወንዶች ጉዳይ....👏 ሊመለስ ነው

ከመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ሊፈፀሙ የሚችሉ ሕገ-ወጥ ተግባራት ቁጥጥርን ይመለከታል፡-መንግስት የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማ...
18/08/2025

ከመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ሊፈፀሙ የሚችሉ ሕገ-ወጥ ተግባራት ቁጥጥርን ይመለከታል፡-

መንግስት የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ለማድረግ ያስተላለፈው ውሳኔ የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያግዝ በጎ ተግባርና አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

የደሞዝ ማሻሻያው ከሀገራችን ጠቅላላ ህዝብ ቁጥር ከ2% የማይበልጠውን የመንግስት ሠራተኛ የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል መንግስት ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከዚህ በፊት ካለው ልምድ ለመገንዘብ እንደሚቻለው አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብ ሕግና ስርዓትን ጠብቆ የሚሠራ መሆኑ የሚያስመሰግን ቢሆንም የተወሰኑ በአፍቅሮተ-ነዋይ የታወሩ ነጋዴዎች ለሠራተኛው ኑሮ ማሻሻያ የሚደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት መሯሯጥ ተስተውለዋል።

እንደዚህ አይነት ኢ-ሞራላዊ ያልተገባ ጥቅም ማግኛ ሩጫ ከንግድ ሥነ-ምግባርና ሞራል አኳያ ሲታይ አሳፋሪ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአዋጅ ቁጥር 980/2008 እና 813 /2006 እንዲሁም በወንጀል ሕግ 1996 ተላልፎ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመድረግ በማንኛውም የንግድ እቃ እና አገልግሎት ግብይት ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ወይም ሰው ሰራሽ እጥረት ለመፍጠር ምርት የሚሰውሩ እና አላግባብ የሚያከማቹ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኝ የንግድ መዋቅር ከሚመለከታቸው የፍትህ እና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ የገበያ ማረጋጋት፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በማጠናከር በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ የግብይት ሂደቱ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል እንዲደረግ እናስታውቃለን፡፡

የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

Daballii mindaa hojjettoota mootummaa waliin walqabatee hojiiwwan seeraan ala raawwatamuu to’achuu ilaallata: - .

Mootummaan fulbaana 2018 irraa eegalee haala jireenya hojjettootaa fooyyessuuf murteesse hojii gaarii fi tarkaanfii gaarii haala jireenya hojjettootaa fooyyessuuf gargaaru ta’uu ni hubanna. Daballii miindaa kun haala jireenyaa hojjettoota mootummaa, kanneen ummata biyya keenyaa keessaa %2 hin caalle fooyyessuuf, tajaajila mootummaan hawaasaaf kennu bu’a qabeessa taasisuuf akka ta’e ni beekama.

Muuxannoo kanaan duraa irraa akka hubatamutti hawaasni daldalaa harki caalaan seeraa fi sirnaan socho’uun isaa kan galateeffamu ta’us, daldaltoonni of jaalattoonni tokko tokko daballii mindaa sababa godhachuun haala jireenya hojjettootaa fooyyessuuf faayidaa hin malle akka barbaacha ariifachaa akka jiraan hubatameera.

Gochi akkasii gocha haamilee cabsu fiigichi faayidaa argachuuf taasifamu naamusa fi haamilee dal

ሰበር ዜና................................................ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቀው የደመወዝ ማሻሻያ፦ *********************...
18/08/2025

ሰበር ዜና................................................
ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቀው የደመወዝ ማሻሻያ፦
*****************************

ከመስከረም 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ በዚሁ ማሻሻያ መሠረት፦

1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ
ይደረጋል፡፡
2. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።
3. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም
ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡
4. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000
እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ  የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈፀመ   | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ለደንበኞቹ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማቅረብ የሀገሪቱን...
16/08/2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈፀመ

| የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ለደንበኞቹ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማቅረብ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞቻችን ማመልከቻዎችን ሁሉንም በማጽደቅ የ420.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች ፈቅዷል።

የዛሬው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከተፈቀደው ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ በባንካችን ለ1,140 ደንበኞች 541.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ተፈቅዷል።

ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ ነው።

ባንካችን ከጁላይ 1 ቀን 2025 ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ 1.034 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ፈፅሟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውድ ደንበኞቻችን ፍላጎት እና ከአገራችን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ጋር በማጣጣም ለውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመደበኛነት ምላሽ መስጠቱን ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

🛑 19 ሚሊዮን ብር ለፎቶ ማጠቢያ ማሽን በኢትዮጵያአዎ19,000,000 ለፎቶ ማጠቢያ ማሽን በኢትዮጵያ 👉አንድ አመት ለሚጠጋ ጊዜ “ወገኔ ሳይበላ አልበላም” በሚል መርሃ ግብር  ቀን በቀን ሳ...
16/08/2025

🛑 19 ሚሊዮን ብር ለፎቶ ማጠቢያ ማሽን በኢትዮጵያ
አዎ19,000,000 ለፎቶ ማጠቢያ ማሽን በኢትዮጵያ

👉አንድ አመት ለሚጠጋ ጊዜ “ወገኔ ሳይበላ አልበላም” በሚል መርሃ ግብር ቀን በቀን ሳያቋርጥ 100 ሰው እየመገበ የሚገኝው እንዲሁም ከ 90 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረው የ25 አመቱ ወጣት ስራ ፈጣሪ ወጣት ጳውሎስ ጎይቶም ከ2 አመት በፊት ስራ የጀመረው በኢትዬጵያ የመጀመርያው ሙሉ የሠርግ ጥቅል አገልግሎት አቅራቢ የሆነው

👉PAUL ፎቶ ቬሎ እና ሜካፕ በ 19,000,000 ብር ውጭ
- Noritus Lps-24 pro
- Frontier lp-7700
- 14 in one album making.
የተሰኙ የዘመኑ የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆኑ ሶስት ማሽኖች ያስገባን ሲሆን ይህም ለደንበኞቻችን በ አለማችን የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆኑ የፎቶ ጥራት እና የላቀ ፍጥነት ይዞ በአዲስ መልክ ስራ ጀምረዋል።

🛑በሀገራችን እንደ ወጣት ስራ ፈጣሪ ጳውሎስ ጎይቶም ያሉ ኢትዬጵያ ውስጥ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ያሳዩ እና ወገኖቻቸውን የሚረዱ ብሎም ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የቻሉ ጀግና ወጣቶችን ፈጣሪ ያብዛልን።

አዳዲስ ጉዳዮችን ይዞ ከ82 ቀናት በኋላ ዛሬ የሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ****************የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሦስት ወር የቀረበ ጊዜ ረፍት ካደረገ በኋላ ዛሬ ከአዳዲስ...
15/08/2025

አዳዲስ ጉዳዮችን ይዞ ከ82 ቀናት በኋላ ዛሬ የሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
****************

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሦስት ወር የቀረበ ጊዜ ረፍት ካደረገ በኋላ ዛሬ ከአዳዲስ ተጫዋቾች ጋር ብቻ ሳይሆን ከአዳዲስ ጉዳዮች ጋር ይመለሳል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአንፊልድ ሊቨርፑል ከ ቦርንማውዝ የሚያደርጉት ጨዋተ ደግሞ የሊጉ መክፈቻ ሆኗል፡፡

ክለቦች በአዲሱ የውድድር ዘመን ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ በርካታ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ከማድረግ ጀምሮ ረብጣ ገንዘብ አውጥተው ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

ክለቦች ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች አንጻር ለዋንጫ የሚደረገው ፉክክር ከቀደሙት አመታት እጅግ ጠንካራ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ የሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑል እስከ አሁን ከ280 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ወጭ አድርጎ ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

አርሰናል ለዓመታት ጥያቄ ሲነሳበት የነበረውን የፊት መስመር ችግር ለመፍታት ቪክቶር ጊዮኬሬሽን ጨምሮ ከአማካይ እስከ ተከላካይ አስፈርሟል፡፡

ባለፈው ዓመት አስቸጋሪ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው ማንችስተር ሲቲ ከጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ጀምሮ ራሱን በሚገባ አጠናክሯል፡፡

ረብጣ ገንዘብ አውጥቶ ከዋክብትን በመሰብሰብ የሚታወቀው ቼልሲ በዚህኛው የዝውውር መስኮት የለቀቃቸው ተጫዋቾች እንዳሉ ሆነው 8 ተጫዋቾች ወደ ምዕራብ ለንደን ወስዷል፡፡

በሊጉ 15ኛ ደረጃን ይዞ የጨረሰው ማንችስተር ዩናይትድ በተለይ የፊት መስመሩን ለማጠናከር ቤንጃሚን ሸሽኮ፣ ብሪያን ምቤሞ እና ማቲያስ ኩንሀን አስፈርሟል፡፡

ከሻምፒዮን ሽፑ ያደጉት እንደ ሰንደርላንድ አይነት ቡድኖች በሊጉ ለመቆየት እስከ 10 የሚደርሱ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ለዋንጫ ብቻ ሳይሆን በሊጉ ለመቆየት የሚደረገው ፉክክርም ቀላል እንደማይሆን ይገመታል፡፡

ባለፉት 25 ዓመታት በናይክ ኳስ ሲጫዎት የቆየው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በአዲሱ የውድድር አመት በፑማ ኳስ የሚጫዎት ሲሆን የግብ ጠባቂዎች የ8 ሰከንድ ህግ፣ ሰሚ አውቶሜትድ ኦፍሳይድ ቴክኖሎጂ፣ በጨዋታ መሀል ተቀይረው የሚወጡ ተጫዋቾችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እና ዋና ዳኞች የቫርን ውሳኔ በግልጽ መሳወቅ 380 ጨዋታዎች በሚደረጉበት ሊግ አዲስ የሚተገበሩ ህጎች ናቸው፡፡

ዛሬ በሚጀመርው መርሐ ግብር የሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሜዳው ቦርንማውዝን ያስተናግዳል፡፡ ክለቡን በተረከቡበት ዓመት የሊጉን ዋንጫ ያሳኩት አሰልጣኝ አርን ስሎት በተከታታይ ስኬታማ ለመሆን ዛሬ አጀማመራቸውን ማሳመር ይጠበቅባቸዋል፡፡

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ሦስት ወሳኝ ተካለካዮቹን ያጣው ቦርንማውዝ ከሊቨርፑል ካደረጋቸው ያለፉት 12 ጨዋታዎች በ11ዱ ተሸንፏል፡፡

የመርሲሳይዱ ክለብ በቅርቡ በመኪና አደጋ ህይወቱን ላጣው ተጫዋቹ ዲየጎ ዦታ እና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫ መታሰቢያ በማድረግ ረጅሙን ጉዞ የሚጀምርም ይሆናል፡፡

የአንድ አመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያለውን ሕፃን አግተው፤ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉየአንድ ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያለውን ሕፃን አግተው፤ 2 ሚሊዮን ብር የጠ...
14/08/2025

የአንድ አመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያለውን ሕፃን አግተው፤ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያለውን ሕፃን አግተው፤ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ወንጀሉ የተፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ኀብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ ሰላሳ 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡40 ሰዓት ገደማ፤ “ፋኑኤል ብርሃነ” የተባለ የ1 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለውን ሕፃን ከመኖሪያ ቤቱ በስውር መውሰዳቸውን ፖሊስ ገልጿል። ሕጻኑን ከወሰዱ በኋላ ወደ ወላጅ አባቱ ስልክ በመደወል፤ ሕጻኑን እንዳገቱት ገልጸው 2 ሚሊዮን ብር በአካውንት ገቢ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ተብሏል። ይህን ማሳሰቢያ የሰሙት ወላጅ አባት ስለ ሁኔታው በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ በወቅቱ ማስታወቃቸው ተነግሯል።

የሕፃኑ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ የቄራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ እና የክትትል ክፍል ካህሳይ ተክላይ የተባለውን እና ከሕፃኑ ወላጅ አባት ጋር ዝምድና ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደቻለ ፖሊስ ገልጿል።

የወንጀሉ አቀነባባሪ ነው ተብሎ ተጠርጥሮ በተያዘው ካህሳይ ተክላይ ላይ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ሥራ፤ በሕፃኑ እገታ ከሚገኝ ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ ለመሆን በመስማማት ወንጀሉን የተባበሩ ተጨማሪ ሦስት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ተይዘዋል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ፊሊሞን ገ/ማርያም፣ ተክሊት ህሉፍ እና ምሕረት ዕድሉ እንደሚባሉ ፖሊስ አስታውቋል። ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግስቱ ነው። በዕለቱ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ማራኪ በተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ ክፍል በመከራየት ሕጻኑን ይዘው ተሸሽገው እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ በማህበራዊ ገጹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል። በአጠቃላይ በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሁሉም ግለሰቦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ተብሏል።

Enderase mediaየኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንትይህን መረጃ የርሳቸው ዘመድ ያደረሰኝ ሲሆን እኔም አቶ ናስር ሀሰን...
14/08/2025

Enderase media
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት

ይህን መረጃ የርሳቸው ዘመድ ያደረሰኝ ሲሆን እኔም አቶ ናስር ሀሰንን በስልክ አግኝቼ አውርቻቼዋለሁ። በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ነው ። ከሳምንት በኋላም እንደምንገናኝ ተቀጣጥረናል። እስከዛው ድረስ የባንኩ አርማ ሲሰራ የነበረውን ሂደት በተመለከተ ያላቸውን ትዝታ እንዲህ በማለት አካፍለውኛል


የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርማ (ሎጎ) ሙያዬና ሥራዬ ባይሆንም ማንም ሳይጠይቀኝና ሳያዘኝ በራሴ ተነሣሽነት አንዲት ሣንቲም ሳይከፈለኝ ዲዛይን አድርጌና ክሊሼውን እንግሊዝ ሀገር በነፃ አሰርቼ ለወቅቱ የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ለአቶ አለሙ አበራ አቅርቤ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎ ላለፋት 50 ዓመታት አገልግሏል።

በመሆኑም አርማው በቼኮች በቁጠባ ሒሣብ ደብተሮችና በበንኩ የፅህፈት መሣሪያዎች ላይ እንዲታተም አስደረግኩ ።

በወቅቱ የባንኩ የሒሣብና የኢንቬስትሜንት (መዋዕለ ንዋይ) መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ነበርኩ ።

በወቅቱ ለዚህ ሥራዬ የቃል ምስጋና እንኳን አላገኘሁም ነበር። አሁን ያን ወርቃማና ሽክርክር አርማ ለመተካት ግማሽ ቢሊዮን ብር ከማስወጣቱም በላይ በየሕንፃዎቹ ላይ ያሉትን አርማዎች አፍርሶ አዲሱን መተካት ፣ ያሉትን የጽህፈት መሣሪያዎች የቼክና የቁጠባ ደብተሮች ፣ የኮምፒዩተር ሶፍትዌሮችና ወዘተ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ የትየሌሌ ነው።

በዚያ ላይ አዲሱን አርማ በመላ ዓለም ላሉ ባንኮች የፋይናንስ ድርጅቶች ለባንኩ ደምበኞች ሀ ብሎ ለማስተዋወቅ ሚሊዮኖች ያስወጣልና ትርፍና ኪሣራው በሚገባ ታስቦበታል ወይ ያሰኛል ? በማለት ይገልጻሉ አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞው የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት

አቶ ናሥር ሐሰን በትጋት በታማኝነት፣በቅንነት ከነበረባቸው ሃላፊነት በተጨማሪ ያሳዩት ትጋት የሚያስደንቅ እና የሚያስተምር ነው ።
በቀጣይ በአካል አግኝቻቸው ታሪካቸውን ያካፍሉናል ብየ እገምታለሁ ። መረጃውን ላደርስከኝ፣ከርሳቸው ጋር ላገናኘኸኝ አዲስ ምስጋናየ ይድረስህ

(አብዱረሂም አህመድ ) #ሼር

ለቅርጫ ብለው ከገዙት ሰንጋ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞችበአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በሚባለው አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ለበዓሉ ቅርጫ ይሆነናል ብለው ገዝተው ካረዱት ሰንጋ ውስ...
18/04/2023

ለቅርጫ ብለው ከገዙት ሰንጋ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞች

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በሚባለው አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ለበዓሉ ቅርጫ ይሆነናል ብለው ገዝተው ካረዱት ሰንጋ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።

ቀድመው ከብቱን ለመግዛት 40,000 ብር ያወጡ ሲሆን የተገኘውን ወርቅ ደግሞ 53,000 ብር መሸጥ ችለዋል። ይህም 13 ሺብር ትርፍ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

ቅርጫውን ሲያስተባብሩ የነበሩት አቶ በቀለ ቀነኒ የተባሉ ግለሰብ ወርቁን በመሸጥ ባገኙት ገንዘብ ሌላ ስንጋ ለመግዛት ቀጠሮ መያዛቸውን ተናግረዋል።
Via OBN
ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ይህንን የቴሌግራም ቻናል

የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰሜናዊት ኮኮብ መቐለ ከተማ
17/04/2023

የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰሜናዊት ኮኮብ መቐለ ከተማ

Address

Gsmbiya
Addis Ababa

Telephone

0967456789

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Enderase MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Enderase MEDIA:

Share