
11/07/2025
የኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ውስጥ ተካተተ
*******
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሌሊት ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።
ይህም ማለት ብርን ወደ ሩብል እንዲሁም ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ዕድልን ይሰጣል።
በዚህም መሰረት ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።
ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።
Ethio-Daily