Maos Media

Maos Media Follow us🙏

ከአየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር...
03/12/2025

ከአየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ እና ይዲድያ ነጻነት ላይ በነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽ ጆን ዳንኤል ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስተቱን ቲክቶክ በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።

ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ዕለት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ተከሶሾቹ የተከሱበት የህግ አንቀፅ ቀላል እስራትን የሚያስከትል በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከአራት ወር፤ 2ኛ፣ 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በስምንት ወር እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ በ10 ወር እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

በመሆኑም ተከሳሾቹ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ተሰልቶ ተከሳሾቹ እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

Via FBC

🥴
02/12/2025

🥴

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 23/ 2018 በተጨማሪም አንዱ በህክምና ላይ ያሉት ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆ...
02/12/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 23/ 2018

በተጨማሪም አንዱ በህክምና ላይ ያሉት ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።

Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
December 2/ 2025



ለ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የ10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት አበር...
02/12/2025

ለ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የ10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አስመልክቶ ለቡድኑ የእራት ግብዣ አከናውኗል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ቡድኑ የመንግሥት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ ውጤት ነው፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳካ ጊዜ እንደሚያሳልፍም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን በ3ኛነት በማጠናቀቅ ከ22 ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወቃል፡፡

ክልላዊ የፀሬ ሙስና ቀን አከባበር ማጠቃለያ ዋዜማ ምሽት...!!በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ፣ በሀገር ደረጃ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ እንዲሁም በክልላችን ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ ‘’ትዉልድን በስነ-ምግባ...
02/12/2025

ክልላዊ የፀሬ ሙስና ቀን አከባበር ማጠቃለያ ዋዜማ ምሽት...!!

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ፣ በሀገር ደረጃ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ እንዲሁም በክልላችን ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ ‘’ትዉልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል ከህዳር 18-23/2018 ዓ/ም በክልል ተቋማት፣በልማት ተቋማት፣ በዞኖች፣በከተማ አስተዳደሮች፣በወረዳዎችና በትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር የቆየዉ የጸረ-ሙስና ቀን በዛሬው ቀን ዋዜማዉ በክልሉ በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

የፀሬ ሙስና ቀን በተከበረበት ወቅት የክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ፣ የስነምግባርና ፀሬ ሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች እንዲሁም የከተማዉ ነዋሪ በተሳተፈበት የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡

በየደረጃዉ በተለያዩ ኩነቶች ሲካሄድ የቆየዉ በዓል በዛሬው ቀን የክልሉ ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ጋር በመቀናጀት በሚያዘጋጁት ደማቅ ፕሮግራም በነገው ዕለት በቀን 24/03/2018 ዓ/ም የሚጠቃለል ይሆናል፡፡

‎ኢትዮጵያ ከ22 አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች 🇪🇹🇪🇹‎‎⏱️ ተጠናቀቀ‎🇪🇹 ኢትዮጵያ 3 - 0 ኬኒያ 🇰🇪‎⚽️65' ዳዊት ካሳዉ‎⚽️79' ቢኒያም አብርሃ⚽️90+3' ብሩክ ...
02/12/2025

‎ኢትዮጵያ ከ22 አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች 🇪🇹🇪🇹

‎⏱️ ተጠናቀቀ
‎🇪🇹 ኢትዮጵያ 3 - 0 ኬኒያ 🇰🇪
‎⚽️65' ዳዊት ካሳዉ
‎⚽️79' ቢኒያም አብርሃ
⚽️90+3' ብሩክ አይላቸዉ

💚💛❤️ እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያዊያን 💚💛❤️

𝐒𝐢𝐝𝐚𝐦𝐚 𝐁𝐮𝐧𝐧𝐚 𝐅𝐚𝐧𝐬 @ 𝐀𝐝𝐝𝐢𝐬 𝐀𝐛𝐚𝐛𝐚
02/12/2025

𝐒𝐢𝐝𝐚𝐦𝐚 𝐁𝐮𝐧𝐧𝐚 𝐅𝐚𝐧𝐬 @ 𝐀𝐝𝐝𝐢𝐬 𝐀𝐛𝐚𝐛𝐚

𝐆𝐨𝐚𝐭 🤓
02/12/2025

𝐆𝐨𝐚𝐭 🤓

02/12/2025

 #መልዕክተኛዉ
02/12/2025

#መልዕክተኛዉ

Address

Addis Ababa

Website

media

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maos Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share