መረጃ ቲዩብ - Mereja Tube

መረጃ ቲዩብ - Mereja Tube ፈጣን ፣ ታአማኒነት ያላቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን።
ቤተሰባችን ይሁኑ
(2)

19/09/2025

የጭንቅላት ማቀዝቀዣ ! 😂😂

በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ዝውውር 123ቱ ሒሳብ ታገደ!በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ተደረገ።   የፋይናንስ ደህንነት አገል...
19/09/2025

በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ዝውውር 123ቱ ሒሳብ ታገደ!

በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ተደረገ።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው፥ የተጠርጣሪዎቹ የገንዘብ እንቅስቃሴ ታግዶ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በሂደት ላይ ይገኛል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በህጋዊ መንገድ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን እየተጠቀሙ ቢሆንም አንዳንድ አካላት ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ለማትረፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው በክትትል ተረጋግጧል።

በተጨማሪም አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ የክትትል መረጃው ውጤት የሚያመላክት በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ከዚህ በፊት የ138 ግለሰበች ሒሳብ መታገዱ ይታወሳል።

ታግቻለሁ በማለት ከትዳር አጋሩ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀን ዶክተር ተያዘ ! ወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ኮተቤ እየተባለ ከሚጠራው አ...
19/09/2025

ታግቻለሁ በማለት ከትዳር አጋሩ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀን ዶክተር ተያዘ !

ወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ኮተቤ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ዶክተር አበባው በላይነህ የተባለው ይህ ግለሰብ ከሚሰራበት ኮተቤ ጤና ጣቢያ አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች ታግቶ የተወሠደ በማስመሰልና በገዛ ስልኩ አጋቾች እንደጻፉ በማስመሠል ለትዳር አጋሩ "ሦስት ሚሊዮን ብር እንዲያመጡ ይህን ካላደረጉ በህይወት እንደማይገኝ የሚገልጽ የጽሁፍ መልዕክት ይልካል፤ ቤተሠብም በወቅቱ በመደናገጥ ጉዳዩን ለፖሊስ አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተደራጁና የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ጥቆማው ከደረሰው ሠአት ጀምሮ የምርመራ ክፍሉና የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድኑ በመቀናጀት ተገቢውን የክትትል ስራ በመስራት ታግቻለው ያለው ግለሰብ ደብረ ብርሀን ከተማ ከአንድ ሆቴል ውስጥ እንዳለ ይደርሱበታል።

በሆቴሉ ደርሰው ሲያጣሩም ግለሰቡ ለሦስት ቀናት ቆይቶ መሄዱን መረጃ ያገኛሉ። ፖሊስ ለምርመራው እንዲረዳም የባንክ እንቅስቃሴውን እየተከታተለ መሆኑን የተረዳው ተጠርጣሪ ጳግሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሠአት ገደማ አጋቾቹ ብሩ ሊላክላቸው ባለመቻሉ ለቀውኛል በሚል ከሦስት ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቱም ተመልሷል። ፖሊስም ግለሰቡ ወደ ቤተሠቡ መመለሱን በደረሠው መረጃ በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

ፖሊስም ግለሰቡ ላይ ባደረገው ምርመራ የማስፋትና ስራ ታገትኩ ያለው ግለሰብ ምንም ዓይነት የእገታ ወንጀል ያልተፈፀመበት መሆኑን እና ገንዘቡን የጠየቀውም እራሱ መሆኑን፣ ለሦስት ቀናት ሆቴል አልጋ ይዞ እንደቆየም ጭምር በተደረገው ምርመራ ሊደረስበትም ችሏል።

አንዳንድ ግለሰቦች ያልተገባን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ያልተፈጸመባቸውን ወንጀል ተፈጽሞብኛል በማለት በሌሎች ሰዎች ላይ ፍርሀትን ከመንዛትም ባለፈ የሚፈፅሙት ድርጊት ከህግ ተጠያቂነት እንደማያድናቸው ሊገነዘቡ ይገባል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

Via_አዲስ አበባ ፖሊስ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።በዚህም መሰረት፡- 1ኛ...
19/09/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ. እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) - የብሔራዊ ባንክ ገዥ

2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

19/09/2025

"የአለም ሻንፖዬና የመጀመሪያዬ ቢሆንም ፈጣሪ ይረዳኛል ወርቅ እንዳመጣ"

አትሌት ቢኒያም መሃሪ

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በታላቅ ድምቀት ሊካሄድ ነውየኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 - 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።የኦሮሚያ ክል...
19/09/2025

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በታላቅ ድምቀት ሊካሄድ ነው

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 - 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በሰጡት መግለጫ፤ የቱሪዝም ሳምንቱ በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ፀጋዎችን ለማስተዋወቅ ብሎም የቱሪስት ፍሰትን በመሳብ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የቱሪዝም ሳምንት በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ባህላዊ ትውፊቶች እንደሚተዋወቁ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ በሚዘጋጀው የቱሪዝም ሳምንት ላይ ከአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ እንግዶች እንዲታደሙ ጥሪ መደረጉን ተመላክቷል።

በቱሪዝም ሳምንቱ የተለያዩ የውይይቶች መድረኮች፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ሽልማት፣ የቁንጅና ውድድር እና ሌሎች መሰናዶዎች ይካሄዳሉ ተብሏል።

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደና ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ‎በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በማስመጣት ተመራጭ የሆነው ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀ...
19/09/2025

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደና ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

‎በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በማስመጣት ተመራጭ የሆነው ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ።

‎የታማኝነት መገለጫ የሆነው የጋዜጠኝነት ሙያ ባለሙያዎችን የመረጥነው ድርጅቱ ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ ነው ።

‎ኢትዮፒካር ዘመናዊነትን የተላበሱና ለኢትዮጵያ መልካ ምድር ተስማሚ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣትና ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነትን እና ታማኝነትን ማግኘት የቻለ ድርጅት ነው፡፡

‎"ታማኝነት'ን ተቀዳሚ መርሁ ያደረገው ድርጅቱ፤ በቀጥታ ግዢ ከሚያቀርባቸው መኪኖች በተጨማሪ ከተለያዩ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር (አሚጎስ ብድርና ቁጠባ፣ግሎባል ብድርና ቁጠባ )እና ከሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር በውስን ቁጠባ እና መጠነኛ ወለድ ብድር አማራጭን በመጠቀም እስካሁን ለበርካታ መኪና ፈላጊዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን አስረክቧል፡፡

‎በአሁኑ ወቅት ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስመጣቸው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖቹ ከፍተኛ ተፈላጊነትን ያገኘው ኢትዮፒካር ተወዳጆቹን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎች በዛሬው ዕለት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ይሰይማል።

‎በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ብሎም በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢነት ለረጅም አመታት በሙያው የቆዩት ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማ እና ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ የድርጅቱ አምባሳደር ተደርገው ሲሰየሙ የጋዜጠኝነት ሙያ የታማኝነትና የሃቀኝነት ሙያ መሆኑን መነሻ በማድረግ ብሎም ኢትዮፒካርም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን ለማሳየት ነው ::

‎በተጨማሪም ሁለቱ ተወዳጅ ጋዜጠኞች ብራንድ አምባሳደር ሆኖ መመረጥ ድርጅቱ ለጋዜጠኝነት ሙያ እና ባለሙያ ያለውን ክብር ማሳያም ስለመሆኑ በፅኑ ያምናል፡፡

‎ብራንድ አምባሳደር ሆነው የተመረጡት ዮናስ ከበደ እና እፀገነት ይልማ በአምባሳደርነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈላጊዎች ኢትዮፒካር የሚያስመጣቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ ምርጫቸው እንዲያደርጉ የማስቻል ስራን እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡

‎በአዲስ አበባ እና በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ (U.A.E) መቀመጫውን አድርጎ የተመሰረተው ኩባንያው ከኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅቶች ጋር ስምምነት በመግባት ለመኪኖቹ የባትሪ ዋስትና በመስጠት እንዲሁም የተሟላ መለዋወጫ አቅርቦትና አስተማማኝ ጥገና ጋር በማቅረብ ደንበኞቹ ከስጋት ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል፡፡

ለተማሪዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)  እየተሰጠ ነው!በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ መንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በሁ...
19/09/2025

ለተማሪዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እየተሰጠ ነው!

በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ መንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በሁሉም ቅርንጫፎች እየሰጠ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዮች ምዝገባ እና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ፋና፤ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራትን በተመለከተ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ክፍያ የመክፈል በሕግ የተቀመጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ይህንን የወጪ መጋራት ክፍያን ለመሰብሰብ እንዲያመች በአዋጁ መሠረት ለገቢዎች ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት፤ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋማት ወይም ቀጣሪዎችና ባለድርሻ አካላት የወጪ መጋራትን ከመሰብሰብ አንፃር የተሰራው ሥራ ክፍተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ያለውን አሰራር ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያቸውን በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በቀላሉ መፈፈም እንዲችሉ ለማድረግም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ፤ በሁሉም የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች በመገኘት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በቀጣይ ከሌሎች ተቋማት ጋር በሚኖር ቅንጅታዊ አሰራር ደግሞ፤ ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

Via_አሐዱ ሬዲዮ

18/09/2025

ይሄንን ታዳጊ ልጅ አለማድነቅ አይቻልም!

በኢትዬጲያ 867 እጽዋት ዝርያዎች ለመድኃኒትነት ተለዩ👉 400 ያህሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው በሃገራችን ከሚገኙ እጽዋት መካከል ለመድኃኒትነት የሚውሉትን በጥናት በመለየት 867 የ...
18/09/2025

በኢትዬጲያ 867 እጽዋት ዝርያዎች ለመድኃኒትነት ተለዩ

👉 400 ያህሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው

በሃገራችን ከሚገኙ እጽዋት መካከል ለመድኃኒትነት የሚውሉትን በጥናት በመለየት 867 የእጽዋት ዝርያች ወደ ዘረ-መል ባንክ ማስገባቱን የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢኒስቲትዩ ባለሙያና የመድኃኒት እፅዋት ተመራማሪ እና ቴክንሽያን አቶ ቢኒያም ጣሳው "በኢትዮጵያ ከ7 ሺሕ በላይ እጽዋት ለባህላዊ ሕክምና አገልግሎት እየዋሉ ነው ተብሎ ይገመታል" ያሉ ሲሆን፤ እስከ አሁን ፈዋሽነታቸው በጥናት ተረጋግጦ የተመዘገቡት 867 መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህም ምዝገባ እና ጥበቃ ከተደረገላቸው እጽዋት መካከል 400 የሚሆኑት፤ ዝርያቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢኒስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ የባህል ሕክምና አዋቂዎች ማህበር ጋር በመሆን፤ ለመድኃኒትነት የሚውሉ የእጽዋት ዝርያዎችን የመለየት፣ ምዝገባ የማከናወን እንዲሁም ዝርያዎቹን የማብዛት ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ፈዋሽ ናቸው ተብለው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት እጽዋት መካከል፤ ቀበርቾ፣ ኮሰሌ፣ ግራዋ፣ ዝግባ፣ ድንገተኛ፣ ዳማ ከሴ፣ አሪቲ፣ ጤናአደም እና መሰል ሀገር በቀል እጽዋት እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

Via_አሐዱሬዲዬ

Address

4 Kilo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መረጃ ቲዩብ - Mereja Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category