02/12/2020
በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ
የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቀሌ ላይ መከላከያ የማያወቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።
የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ ፈርጥጧልም ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል
የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
በመሆኑም እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢዜአ