Beautiful Areka Ethiopia

Beautiful Areka Ethiopia Areka Boditi Gasuba Bale Hawasa Bixana Didaye Xabala Gara Gununo Bomibe warka Achura woyibo Badesa

  በማድረግ ሁላችንም እንተባበር  !!🤲   #ተማሪ   በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ሠፈረ ሰላም ቀበሌ ነዋሪና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነዉ።ላለፉት ወራት በተለያዩ ሆስፒታሎች በልብ ሕመም ምክንያት...
04/01/2025

በማድረግ ሁላችንም እንተባበር

!!🤲



#ተማሪ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ሠፈረ ሰላም ቀበሌ ነዋሪና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነዉ።

ላለፉት ወራት በተለያዩ ሆስፒታሎች በልብ ሕመም ምክንያት የሕክምና አገልግሎት እያገኘ ቆይቶ አሁን ሕመሙ ከአቅም በላይ እየተባባሰ በመሄዱ እና አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ታዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል በአፋጣኝ የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንዲደረግለት አዟል።

ይህንን የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማድረግ ብቻ 885,000 (ስምንት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ) ብር እንደሚያስፈልግም አረጋግጠዋል።

እናም እናንተደጋግ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፦ የተማሪው ወላጅ ቤተሰቦች ምስኪን ደሃ አርሶአደሮች በመሆናቸው ለተማሪው ሕክምና የተጠየቀውን ገንዘብ መክፈል ስለማይችሉ የወጣቱን ሕይወት ለመታደግ ሁላችሁም ልባችሁ በፈቀደዉ ልክ እጃቹን እንዲትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።

ምስጋና ሳኦል ላቤና
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000479180702

04/01/2025
የህብረ ብሔራዊነት ግንባር ቀደም ተምሳሌት በሆነው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግባችን እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ለያዝናቸው እቅዶች ስኬት ተጨማሪ አቅም ...
04/01/2025

የህብረ ብሔራዊነት ግንባር ቀደም ተምሳሌት በሆነው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግባችን እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ለያዝናቸው እቅዶች ስኬት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ውጤታማ የአመራር ምክክር መድረኮች በተከታታይ አካሄደናል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላላ አመራር እና የ12ቱ ዞኖች ማለትም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጌዴኦ፣ የጎፋ፣ የኮንሶ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የአሪ፣ የባስኬቶ፣ የኮሬ፣ የቡርጂ፣ የጋርዱላ እንዲሁም የአሌ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በመድረኮቹ ተሳትፈዋል።

በአጠቃላይ ለ4 ቀናት ያካሄድናቸው የምክክር መድረኮች የክልሉን አመራር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እና አቅም ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም በክልሉ የተጀመሩ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የሕዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መግባባት እና መነሳሳት የፈጠሩ ሆነው ተጠናቀዋል።

በቆይታችን በአከባቢው እየተሰሩ ያሉና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ፣ የሥራ እድል በመፍጠር እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ህብረተሰቡን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ እያደረጉ ያሉትን የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ጎብኚተናል።

እጅግ ታታሪ ሕዝብ መኖሪያ በሆነችው እና ከፍተኛ የማደግ ተስፋ ባላት በወላይታ ሶዶ ከተማ በነበረን ስኬታማ ጊዜ ከክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ ጀምሮ የክልሉ መንግስት፣ የዎላይታ ዞንና የዎላይታ ሶዶ ከተማ አመራሮች እና ሕዝብ ላደረጋችሁልን አቀባበልና ትብብር ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከገቢ የሚገኘውን ገንዘብ አሰራርን ጥሶ ከመዝረፍ ባሻገር ከ45 በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ መቅጠሩ ተነገረ።የክልሉ ገቢ ቢሮ 88% በላይ ሰራተኞች የአ...
04/01/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከገቢ የሚገኘውን ገንዘብ አሰራርን ጥሶ ከመዝረፍ ባሻገር ከ45 በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ መቅጠሩ ተነገረ።

የክልሉ ገቢ ቢሮ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ሰዎች ብቻ እንዲሰሩ በመደረጉ በተለያዩ ዞኖች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ መሆኑንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ በተለይም በዎላይታ ዞን፣ በጌዴኦ የሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ግብር ከፋይ የሆኑ ባለሀብቶች ላይ ያለአግባብ ጫና በመፍጠር ፋብሪካዎች እንዲዘጉ፣ ባለሀብቶች እንዲታሰሩ እና እንዲሸማቀቁ መደረጉም ተገልጿል።

በክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች ከግብር ከፋይ የተሰበሰበ ከፍተኛ ገንዘብ የተለያዩ ህገወጥ ዘዴዎችን በመጠቀም በክልሉ ርዕሰ መስተደድር አማካይነት ወጪ ተደርጎ እንዲወጣ ተደርጎ በኢፍትሃዊነት ለራሳቸው ለሚሉት ጥቅምና ፍላጎት መጠቀሚያነት እያዋሉ ስለመሆኑም የደረሰን ተጨባጭ የስነድ መረጃ ያመለክታል።

በተለይም የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የስነምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆነና የልጇን ባል ሾፌር በማድረግ ጭምር ከማህበረሰቡ እሴት ውጪ ባህሪ የሚያሳዩ እንዲሁም የሌሎች ብሄሮች ሰራተኛ አለአግባብ እንዲባረሩ በውድድርም እንዳይገቡ በማድረግ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ብቻ እንዲሆኑ በማድረግ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ግብር ከፋዮች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ እንደምትገኝ አንድ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተል አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግረዋል።

ከ 45 በላይ ስራተኞች የቢሮው የሰው ሀብት አመራሮችና ሰራተኞች ሳያውቁ በህገወጥ መንገድ በራሷ ፊርማ ብቻ ቅጥር መፈፀሟንም መረጃው አመላክቷል።

ለማሳያነት ከክልሉ ገቢዮች ቢሮ አመራርን ጨምረው አጠቃላይ 77 ሰራተኞች 88% ጋሞ፣ 6 የዎላይታ ተወላጆች (2 ሾፈሮች እና 4 ተራ ስራተኞች) እንዲሁም የተቀሩ ሰራተኞች 3% የማይሞሉ ከሌሎች ብሄሮች እንደሆኑ ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ይጠቁማል።

ፌደሬሽን ምክርቤት ባፀደቀው ህግ መሠረት በክልሉ በአንድ አከባቢ የሚገኝ የፈደራል ተቋም ለክልሉ በማሳወቅ ለፌደራል ገቢዎች ከከፈለ በኃላ በፐርሰንት ወደ ተቋሙ ያለበት ዞን የሚላክ "የጋራ ገቢ ህግ" መሠረት መላክ የነበረበትን በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ከግማሽ በታች እንዲሆን ማድረጓንና አለግባብ ገንዘቡ በህገወጥ አሰራር ወጪ እየተደረገ ስለመሆኑም ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አመራር መረጃ ከሆነ በህጉ መሠረት፦ ከጋራ ገቢ ከፌደራል ለሚመለከታቸው ዞኖች ለክልሉ የተላከውን በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ገንዘብ አለአግባብ ለአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ፣ ለአደባባይ ግንባታ፣ ለተለያዩ መስተንግዶ፣ ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሆነና ኦዲት እንዳይደረግ በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና መከልከሉንና እስካሁን ኦዲት ተደርጎ አለማወቁን አስረድተዋል።

በክልሉ ዎላይታ ዞን ከክልል ማዕከል ውጪ ባለው ዕቅድ 60% በመቶ በላይ ይይዛል፣ በ2016 በጀት አመት ዞኑ በክልሉ ከፍተኛ ገቢ ሰብስቧል፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 6.1 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በ6 ወር አፈፃፀም ብቻ ከ 3.9 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ በአፈፃፀም ከክልሉ ከፍተኛ አፈጻጸም አሳይቷል፣ በተቃራኒው በዘንድሮ በጀት ዓመት ጋሞ ዞን 5 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በስድስት ወር አፈፃፀም 1 ቢሊዮን ብቻ መሰብሰብ መቻሉን ከሪፖርቱ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

የመንግስት ስራተኞች ደመወዛቸውን በአግባቡ መክፈል እየተቸገሩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች የሚከፍሉትን ግብር ሰብስበው ለሰፈራቸው ልማትና ለግ

የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሟላት ነገን የሚሰሩ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ያግዛል፦ አቶ ተስፋዬ ይገዙወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 26/2017 በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ አንጋፋው የጋሌ ...
04/01/2025

የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሟላት ነገን የሚሰሩ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ያግዛል፦ አቶ ተስፋዬ ይገዙ

ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 26/2017 በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ አንጋፋው የጋሌ ሐሙስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ነገን የሚሰሩ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገር ደረጃ የብዙዎች እንባን ያበሰ ሰው ተኮር ተግባራት በመከናወን በበጎ ስራ የሚታወቁ ናቸው ብለዋል።

ይህንን አርዓያነት ተከትለን በየአካባቢያችን የሚገኙ አቅም ደካሞች በማገዝና ለትውልድ የሚጠቀሙ ልማቶች መስራት መቻልን አለብን ብለዋል።

እርስበርስ የመተጋገዝና የመደጋገፍ ባህላችን ማጎልበት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተስፋዬ ይህንን ካደረገን ሀገራችን ብሎም አካባቢያችን መለወጥ እንችላለን ብለዋል።

መምህራን ለተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ያሳሰቡት ሚኒስቴር ዴኤታው ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲማሩ አሳስበዋል።

ሁሉም ሰው ከራሱ የሚጠበቅበትን ስራ መሰራት ከቻለ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ እንደሚቻልም ጠቅሰዋል።

ትምህርት ቤቱን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱት አካላትን ምስጋና አቅርበዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ትምህርት በሀገራችን ለሁሉም ነገር መሠረት እንደሆነ ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት በመሻሻል ተወዳዳሪ እና ምርታማ ዜጋን ለመፍጠር የበኩላቸውን አሻራ እያበረከቱ ያሉ አካላትን ትውልድ ያመሰግናል ብለዋል።

በዞኑ በቼንትሮ አዩቲ ፔር ለኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትምህርት፣ በጤና፣ ድጋፍ የሚሹ አቅመ ደካሞች ባሻገር በሁሉም ዘርፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልማቶች መሰራቱንም ገልጸዋል።

በቼንትሮ አዩቲ ፔር ለኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት እያደረገ ያለው ሁለ አቀፍ ድጋፍ በዞኑ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ያሉን ፀጋዎችን አሟጠን ከተጠቀምን፣ ተጋግዘንና ተደጋግፈን ከሰራን በትምህርት ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።

የቼንትሮ አዩቲ ፔር ለ -ኢትዮጵያ ግብረ ስናይ ድርጅት አስተባባሪ ሮበሮቶ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

"ንጹሀን ወገኖቻችንን ያስገ'ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ" - የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን "በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል...
04/01/2025

"ንጹሀን ወገኖቻችንን ያስገ'ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ" - የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን

"በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል አመራሮች መድረክ ተጀምሯል። በቀድሞዉ የደኢህዴን አዳራሽ ዉስጥ። ርዕሱ ደግሞ የክልሉ የ6 ወራት የድርጅት እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸምና ወቅታዊ ጉዳዮችን መገምገም ይላል። የተጀመረው ደግሞ ቦና ወረዳ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነዉ" ስሉ አንድ የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ወደ ሰነዱ ይዘት ሳይገባ አስቀድሞ "ወቅታዊ ሁኔታዎች" ላይ የጋራ አቋም መያዝ አለብን በማለት በሁለት ሀሳቦች ላይ አስቀድሞ ዉይይት ተደርጎ እንደነበር አስረድተዋል።

"ባለፈው ሳምንት ቦና ወረዳ በተፈጠረውና ከ71 ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ በተመለከተ "ክልሉ ዝምታ መርጧል፣ ክልላዊ ሀዘን ማወጅ አለበት ተብሎ የሚናፈሰዉ ነገር ዉጪና ሀገር ዉስጥ የሚገኙ ጥገኞች የሚያናፍሱት ወሬና የፖለቲካ ቁማር ስለሆነ አስፈላጊ ምላሽ መስጠት አለብን፣ ፕሬዝዳንቱ ጭምር ሄዶ አስቀብ አጽናንቷል፣ የድጋፍ አካዉንት ተከፍቶ ድጋፍ እየተደረገ ነዉ" የሚል ሀሳብም መነሳቱን አክለዋል።

በመድረኩ በሎካ አባያ ከዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ጉዳይ ክልሉ ለምን መግለጫ አልሰጠም? የተፈጠረዉ ነገር ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ሰዉ መኖሩ ተገቢ ቢሆንም ከአቶ አብርሃም ጋር አያይዞ የዉስጥ ባንዳ ከዎላይታ ጠላቶች ጋር በማበር ጓዱን ከስልጣን መነቅነቅ ስለ ጀመሩ አመራሮች በአንድ አቋም መታገል አለባችሁ" በሚል አንድ አመራር አስተያየት መስጠቱን ተናግረዋል።

አክለውም "ይህ ነገር ሰፍቶ እስከ ፓርቲው ዋና ቢሮ ከደረሰ ጓዳችንን ልናጣው እንችላለን የሚል ሀሳብ በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ አንዳንድ አመራሮች "የዎላይታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ነዉ እየታገሉ ያሉት፣ ለኢንቬስትመንት የተሰጡ መሬቶችን በዞኑ በኩል እንደተሰጠ ጭምር በቂ መረጃ እያቀረቡ ነዉና በእኛ በኩል ምን አለ" የሚሉና ከአብርሃም፣ ከአባቱና ዘመድ አዝማዱ ጋር ተያይዞ በሎካ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታሮችን በጸጥታ ሀይል ጭምር በመታገዝ እየተወረረ ነዉ የሚል ወሬ በህዝቡ ዉስጥ እየሰፋ ነዉና ሀሳቡን የመመከት ስራ መስራት አለብን" በሚል አመራሩ የድጋፍ አስተያየት መስጠቱንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም እኚህ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጪ አመራር፦ "አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይህንን የሚፈጽሙት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን (ይርጋለም ዞን) የሰላም፣ ጸጥታና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ባስቀመጠው በወንድሙ አማካኝነት በወታደር ጭምር ታግዞ ነዉ የሚል ወቀሳ በተጨባጭ የቀረበ ስሆን፣ ይህንን ችግር ሌላ ጊዜ በራሳችን መድረክ እናየዋለን አሁን ግን ለጠላታችን መጠቀሚያ ሳንሆን ከጓዱ ጋር መቆም አለብን፣ ሁሉም አመራር በአጠቃላይ ከአብርሃም ጎን እንደሆነ በማሳወቅ በዎላይታ በኩል የሚመጣዉን ጫና በተደራጀ መልኩ በፌስቡክ ዘመቻ፣ በሚዲያ ሰራዊት እንምራ በሚል ማሳሰቢያ ተዘግቶ ወደ ሰነዱ ንባብ እንደተገባ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት።

በአቶ አብርሃም ጉዳይ ላይ በሚነሳው አጀንዳ ላይ በመድረክ ከአብርሃም ጋር የነበሩት የክልሉ ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ አንድም አስተያየት ያልሰጡ ሲሆን ስለ ቦና የትራፊክ አደጋ በተመለከተ በመፍትሔውና ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰብን በዘላቂነት ማጋዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ በስፋት እንደተናገሩም የመረጃ ምንጫችን ጠቁመዋል።

የመድረኩን መረ

ከዲቻ ዉጪ ወደ ዉጪ 🐝👊  🔥 🇧🇪 Beautiful Wolaita🇩🇪 Colors, Ethiopia 🇪🇹𝚅𝚒𝚜𝚒𝚝   Wolaita    🇧🇪🇧🇪    ❣️❣️𝙑𝙄𝙎𝙄𝙏 𝙀𝙏𝙃𝙄𝙊𝙋𝙄𝘼 𝙳𝚒𝚜𝚌𝚘𝚟𝚎𝚛 𝚃𝚑𝚎 ...
03/01/2025

ከዲቻ ዉጪ ወደ ዉጪ 🐝👊

🔥 🇧🇪
Beautiful Wolaita🇩🇪 Colors, Ethiopia 🇪🇹
𝚅𝚒𝚜𝚒𝚝 Wolaita 🇧🇪🇧🇪 ❣️❣️
𝙑𝙄𝙎𝙄𝙏 𝙀𝙏𝙃𝙄𝙊𝙋𝙄𝘼
𝙳𝚒𝚜𝚌𝚘𝚟𝚎𝚛 𝚃𝚑𝚎 𝙱𝚎𝚊𝚞𝚝𝚒𝚏𝚞𝚕 𝚗𝚊𝚝𝚞𝚛𝚎 𝚊𝚗𝚍 𝚌𝚞𝚕𝚝𝚞𝚛𝚎.
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙪𝙣𝙛𝙤𝙧𝙜𝙚𝙩𝙩𝙖𝙗𝙡𝙚 𝙢𝙤??𝙚𝙣𝙩𝙨.. 𝙬𝙞𝙩?? 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙛𝙧𝙞𝙚𝙣𝙙𝙨.
𝕐𝕠𝕦 𝕨𝕚𝕝𝕝 𝕖𝕟𝕛𝕠𝕪 𝕥𝕙𝕖 𝕨𝕒𝕣𝕞 𝕨𝕖𝕝𝕔𝕠𝕞𝕚𝕟𝕘 𝕠𝕗 Wolaita 𝕤𝕠𝕔𝕚𝕖𝕥𝕪.

Tamrineshi Dicha

አስቸኳይ መልዕክት!የደቡብ ክልል መንግስትን ግምገማ ለሚመራ አካል ከጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት  "በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ያለው ብልፅግና ሀገር አቀፍ ፓርቲውን በሚመሩ ክቡ...
03/01/2025

አስቸኳይ መልዕክት!

የደቡብ ክልል መንግስትን ግምገማ ለሚመራ አካል ከጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት

"በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ያለው ብልፅግና ሀገር አቀፍ ፓርቲውን በሚመሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድና ምክትላቸው አቶ አደም ፋራህ በሚያስቀምጡት አቅጣጫ ሳይሆን በብልፅግና ፓርቲ ሽፋን አድርገው ዞኑን የእነርሱ የግል ንብረት ለማድረግ ሌት-ተቀን በሚዳክሩ ጥቂት የፖለቲካ ተሿሚዎችና ከንግድ ማህበረሰብ ውስጥ ከወጡ ጥቂት ክራይ ሰብሳቢ ግለሰቦች በኩል አቅጣጫ እየተቀመጠ እንደሆነ ከውስጥ ሆነን ማየት ከጀመርን ሰነባብተናል።

አዎን አሁን ዞኑን እየመራ ያለው በዶ/ር ዝናቡ ወልዴ የሚመራ ካቢኔ እንደሆነ አልጠፋኝም። ሆኖም ዶ/ር ዝናቡ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህም ቢሆን ዶ/ሩ ያላቸውን ነፃነት ተጠቅመው ዞኑንና ህዝቡን በፈለጉት ልክ በነፃነት እየመሩ እንዳልሆነ ብዙ ምልክቶችን በቅርበት ማየት በመቻሌ ነው።

በሆነ ጫናና ቁጥጥር ውስጥ ዞኑን እየመሩ እንደሆነ ግንዛቤው ስላለኝ ነው። ሆኖም ዶ/ር ዝናቡ በዚህ ጫናና ቁጥጥር ውስጥ ሆነው የሚያደርጉትን ጥበብ የተላበሰ አመራር እያደነቅሁ ቢሆንም ይህንን የታወቀ ጫና ከሚመሩት ህዝባቸው ጋር ተቋቁመውና ተጋፍጠው የማለፍ አቅም እያላቸው ጫናውን ለማስታመም መፈለጋቸው ለዞናችን ፖለቲካ ዛሬም ፈውስን እንዳላጎናፀፈ ይሰማኛል።

ዛሬም ይህንን ያፈጠጠውን ተግባር ከላይ ያለው የፓርቲያችን ቤት መፍትሔ ያበጅለታል ብለን በትዕግሥት ብንጠብቅም እዚያው ነው። ብልፅግና ፓርቲያችን ከተመሰረተ አምስተኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ወቅት ላለፉት አምስት ዓመታት ከላይ ያለው የበላይ አካል በዝምታ ያያቸው ጉዳዮች ዛሬ ከመስመር ወጥተው ለዞኑ መጥፎ ድባብ ሰጥተዋል።

አሁንም አልመሸምና ህዝባችን ብልፅግናችን ላይ ያለው እምነት እንዳይሸረሽር አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ከመጠየቅ ጋር በዞናችን የነበረውን የአስተዳደርና የፖለቲካ ሥልጣን መዋቅር ችግር ከትዝብቴ ተነስቼ ማስቀመጥን ወደድኩ። ማን ያውቃል ዞን ያልቻለውን ክልል፣ ክልል አውቆ ያልፈታውን ችግር የፌዴራል ጆሮ ሰምቶ ትኩረት በመስጠት የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ዘመን ቢመጣ በምል ግምት!

የፖለቲካ ዓይን ቀጥተኛውን ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚካሄደውንና የሚያርፈውን ጫና በጥንቃቄ ያያል። ከዚህ በመነሳት ያለፊት አምስት የብልፅግና ዓመታት ዞኑ በተፈለገው ልክ እንዳያድግ እንቅፋት ሆነው ከቆዩ ጉዳዮች አንዱ በአመራር ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች ለአንዳንድ ኃይሎች ጥገኛ እንዲሆን አሳልፎ መስጠት ነበር።

እነኚህ ኃይሎች በንግድ ሽፋን ህገ ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ስለሆኑ ጥገኛ ባለሥልጣናትን በገንዘባቸው ይዘውራሉ። በገንዘባቸው ለእነርሱ የሚመቸውን ወደ ሥልጣን ያስወጣሉ። እንቅፋት የሚሆኑ ካሉም በአስቸኳይ ከሥልጣን እንዲባረሩ ያስደርጋሉ።

ይህ የተለመደ የዞናችን የፖለቲካ ጫወታ ነበር ነውም። አምስተኛውን የፓርቲያችንን ምስረታ በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ላለፉት አምስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ከላይ በተቀመጠው ምክንያት ለዞኑ መቀጨጭ በበርካታዎቹ ውስጥ እንደ ሰበብ በዋናነት ስሙ የሚነሳውን ሰው ለማንሳት ዛሬ እንደፍራለን።

በመንግስት ደረጃ ዞኑን እንዲመራ የተቀመጡ ዶ/ር ዝናቡ እንደሆኑ በበርካታው የዞን ህዝብ ይታወቃል። እንዲሁም ፓርቲውን እንዲመሩ አቶ አበባየሁ ኢሳያስን። ዞኑን በሥራ አስፈፃሚነት ተያይዘው እንዲመሩ የተቀመጡት ደግሞ በድምሩ አምስት እንዳሉን ለሁላችንም ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ የዞኑ ፖለቲካ የሚዘወረው በአምስቱ ህጋዊያን ብቻ ሳይሆን ከፓርቲው ጀርባ ሆኖ ለስድ

የባስኬት ብሔር የምስጋና በዓል የሆነው "ሾልኣ-ካሻ" ላይ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ እንድታደም የቀረበለትን ጥሪ ተቀበሉወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 25/2017 የባስኬት ብሔር ዓመታዊ የምስጋና በዓ...
03/01/2025

የባስኬት ብሔር የምስጋና በዓል የሆነው "ሾልኣ-ካሻ" ላይ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ እንድታደም የቀረበለትን ጥሪ ተቀበሉ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 25/2017 የባስኬት ብሔር ዓመታዊ የምስጋና በዓል የሆነው "ሾልኣ-ካሻ" ላይ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ እንድታደም የቀረበለትን ጥሪ ተቀብለዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም ከባስኬቶ ዞን አስተዳደር የቀረበለትን ጥሪን ተቀብለው በዕለቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ለባስኬት ህዝቦች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ2017 ዓ.ም የባስኬት ብሔር የምስጋና በዓል "ሾልኣ ካሻ" በአደባባይ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወርኃ ጥር የመጀመሪያዎቹ ቀናት በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ በድምቀት ይከበራል።

በቦዲቲ አስተዳደር በአንድ የግል ባለሀብት በአቶ ዮሐንስ ማላቆ እየተሰራ የሚገኝ የኮሪደር ልማት ስራ የምሽት ገጽታ በፎቶ 📸ቦቦዲቲ ከተማ አስተዳደር/Boditi Town Adiminstration
01/01/2025

በቦዲቲ አስተዳደር በአንድ የግል ባለሀብት በአቶ ዮሐንስ ማላቆ እየተሰራ የሚገኝ የኮሪደር ልማት ስራ የምሽት ገጽታ በፎቶ 📸ቦቦዲቲ ከተማ አስተዳደር/Boditi Town Adiminstration

የዎላይታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ ልቦናዊ፤ ስነ ምህዳራዊ መጎሳቆል ከመቼ ይጀምራል? ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት በተለይም የአጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር ? ...
01/01/2025

የዎላይታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ ልቦናዊ፤ ስነ ምህዳራዊ መጎሳቆል ከመቼ ይጀምራል? ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት በተለይም የአጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር ? - ከፈረንሳዊ አይን ምስክርነት

(ክፍል ሁለት)

ይህ ጸኁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ #ቫንደራሂም /J.G Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደ ነው፡፡

ጹሑፉ ጉምቱ የዎላይታ ባህል አዋቂና ምሁር ለነበሩት ለክቡር ዶክተር ዘብድዎስ ጫማ በነጻ የተሰጠ ስጦታ አንደነበር በትርጉሙ ላይ ተብራርቷል፡፡

ጸሃፊው ስለ ዎላይታ እንደጻፈው ከወረራው በፊት ዎላይታ በፖለቲካው መስክ በራሱ ንጉስ ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ግዛት ነበር። ዎላይታ በኢኮኖሚው በለምነቱና በልምላሜ የሚታወቅ በመሆኑ ዎላይታዎች በምግብ ራሳቸውን ችለው ይተዳደሩ ነበር፡፡

በባህል ደግሞ ዎላይታዎች ድንቅ ባህልና ቅርስ አንዲሁም የራሳቸው የእምነት ተቋማት ነበራቸው፡፡ ዎላይታዎች እጅግ በጣም በጀግንት የአቢሲኒያ ወታደሮች ስለተቋቋሙ ንጉሳቸውን ጦና በቀላሉ ለመያዝ አልተቻለም፡፡ በስነ ልቦና ዎላይታዎች ደስተኞች፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ጀግና ተዋጊዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ ጠቢባን… እንደነበሩ እንመለከታለን፡፡

በክፍል አንድ ዎላይታ ከምኒክ ወረራ በፊት ምን ትመስል እንደነበር ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደት ምን እንደሚመስልና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል በተመለከተ ተቀንጭቦ ቀርቧል፡፡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ "በታሪክ ጥንቅር ዝግጅት" ላይ፦ ትርጉሙ ከዚህ በታች ቀርቧል መልካም ንባብ!

የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደትና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል ድፍን ሶስት ወራት ለዘመቻው ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ የጉዞ ቀን ህዳር መጀመሪያ አካባቢ መሆኑ ገልጽ እየሆነ መጣ፡፡ አዲስ አበባ ካለወትሮ በበለጠ ሽር ጉድ በዛ፡፡ ከንጉሱ ጋር እንዲሄዱ የተጠሩት ጀኔራሎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ፡፡ በጣም የተጠበቀውና ከሁሉም የላቀ እና ከራሱ ሰዎች ጋር 10000 (አስር ሺህ) ሰራዊት እንዲመራ የተመረጠ ራስ ሚካኤል ነው፡፡

ራስ ሚካኤል የጦር መሪ፣ የወሎ ኦሮሞች አገር ገዢ፣ የንጉስ ምኒልክ አማች፣ ደግሞም ሙስሊም፣ ታላቅ የባሪያ ውጪ ላኪ ነጋዴ፣ የሰበአዊ ፍጡርን በተከታታይ በኮንቮይ ወደ ቀይ ባህር ጠረፍ ከወሰደ በኋላ በእንግሊዝ ወይም በቱርክ መርከቦች አማካይነት ወደ የመን የሚልክ ነው፡፡ እሱ መጨረሻ ላይ ህዳር 1 ደረሰ፡፡

በሁለተኛው ቀን ማለቂያ የሌለው ጉዞ በሰልፍ ተጀመረ፡፡ ሴቶች በእግራቸው መጠጥ በገምቦ በጀርባቸው አዝለው፣ ማር ወይም ቅቤ ተሸክመው ከብቶችንና በጎችን እየነዱ ወደ መጀመሪያው ካምፕ አመሩ፡፡ በንግስት ጣይቱና በታላላቅ የቤተመነግስት አማካሪዎች ግፊት ህዳር 15 ቀን ጉዞ ተጀመረ…

ንጉሱ በሚያልፍባቸው በራሱ ግዛት የሚኖሩ አገረ-ገዢዎች ሁሉ ለንጉሱና ለሰራዊቱ ግብር እንዲያዘጋጁ አስቀድሞ ተነግሯቸዋል፡፡በኢትዮጵያ መንገዶች የሚሰሩት በሰው ጉልበት ነው፡፡ ይሄውም በደሃ ገበሬዎች ጉልበት (እጅ) ነው፡፡ እንጨቶችን ይቖርጣሉ፤ ግንዶችን ይነቅላሉ፣ ያቃጥላሉ፣ ወንዞችን ይሞላሉ፣ አፈር ይደለድላሉ፡፡ በጠላቱ (በወላሞ) አገር ግን ይህ ሁሉ የተከናወነው በራሱ በንጉሱ ወታደሮች ሲሆን በንጉሱ ጥብቅ ቁጥጥር ነበር፡፡

ይህን እስኪከወን ድረስ ለብዙ ሰአታት የጉዞአችን መስተጓጎል ግድ ነበር፡፡ እያንዳንዱ የስራ ድርሻውን ይወጣ ነበር፡፡ ይሄውም ድንጋይ ማንከባለል፣ የተቆረጡ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beautiful Areka Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share