31/07/2026
ጋና የህገ መንግስት ማሻሻያ አደረገች። የሀገሪቱን ፕረዘዳንት የሥልጣን ዘመን አራዘመች
****************
የጋና መንግስት አጠቃላይ የሕገ-መንግስት ማሻሻያ አጀንዳ አካል አድርጎ የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን ከባለ አራት ዓመት ወደ አምስት ዓመት ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተቀብሏል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ዶሚኒክ አዪኔ ውሳኔውን ያረጋገጡ ሲሆን፥ ሁለቱም ተቋማት በተመሳሳይ የምርጫ ዑደት ውስጥ እንዲቀጥሉ የፓርላማው የስልጣን ዘመንም ወደ አምስት ዓመት እንደሚራዘም ገልጸዋል።
የማሻሻያ ፓኬጁ የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎችን ዝቅተኛ የዕድሜ ገደብ ወደ 35 ዓመት ዝቅ ለማድረግ የቀረበውን ሃሳብም አካቷል።