Ethio Daily Feta

Ethio Daily Feta The aim of this page to Entertain people.

03/05/2024

በአዲስ አበባ ቅርጫ ተከልክሏል የሚባለው ሃሰት ነው አልተከለከለም!

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።

የመኖሪያ ቤት እጥረትና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀከግዜ ወደግዜ እየናረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ...
03/05/2024

የመኖሪያ ቤት እጥረትና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

ከግዜ ወደግዜ እየናረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅድቆዋል ምክር ቤቱ ያፅደቀው አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርን እና አስተዳደር ይመለከታል

ይህ አዋጅ ቀደም ብሎ በቃል እና በእምነት በተከራይ እና አከራይ መካከል ይደረግ የነበረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 4 መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በፅሁፍ ማድረግን ግዴታ ከማድረጉም ባሻገር ውሉ በተቆጣጣሪው አካል ተረጋግጦ እንዲመዘገብ ያዛል ግዴታቸውን ያልተወጡ አከራይና ተከራይ ላይ የቤት ክራዪን የሦስት ወር ገንዘብ ቅጣት አዋጁ አስቀምጧል። ከዚህ ቀደም ተከራይ የሶስት እና የስድስት ወር ቅድሚያ ክፍያ ለአከራይ መስጠት ግዴታው የነበረ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ ግን ተከራይ የሚጠበበት የሁለት ወር ኪራይ ቅድመ ክፍያ ብቻ ነው ።

ክፍያውም በባንክ ወይም በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ መፈፀም ይኖርበታል ይህ አስገዳጅ ህግ አዲስ የሚፈስም የኪራይ ውል ብቻ ሳይሆን እድሳትንምያካትታል ፣ በአዲሱ አዋጅ አንድ የምኖሪያ ቤት ክራይ ውል የቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው ። በዚህ ግዜ ውስጥ አከራይ ተቆጣጣሪው ከሚያወጣው የክራይ ጣሪያ ውጭ ምንም እይነት የቤት ክራይ ጭማሪ ማድረግ አይችልም።

አዲሱ አዋጅ እስካሁን የቤት ክራይ ዋጋን በተመለከተ ፍላጭ ቆራጭ ናቸው የሚባሉትን የመኖሪያ ቤት አከራዩች እንዳሻቸው ዋጋ ከመጨመር ያግዳቸዋል ። አቅምን ያማከል የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግር ሳቢያ የሚፈጥዕረውን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ተብሎዋል ። DW ያናገራቸው የአዲስ አበባ የቤት ክራይ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እንዲህ ይናገራሉ አዲስ ቤት ለኪራይ የሚያቀርቡ አከራዮችን የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በአዋጁ መሰረት ከሚወጡ የኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች ለአራት አመት ነፃ ይኾናሉ የሚል የማበረታቻ ሲኖረው በሌል በኩል ባለቤቶች ቀደም ብሎ ሲከራይ የነበረን ቤት ከስድስት ወር በላይ ሳይከራይ እንዲቆይ ቢያደርጉ ቤቱ ቢከራይ ያስገኝ የነበረውን የቤት ኪራይ ግብር ገቢ ታስቦ በማግረግ እንዲከፍሉ ይደረጋል ይላል ።

የህግ ባለሙያው አቶ ካፒታል ክብሪ ለ DW እንደተናገሩት አዋጁ በ ግለሰቦች ለፍተው ባፈሩት ሀብት ላይ የሚኖራቸውን መብት ለመገደቡ አሻሚ አይደለም ይላሉ

ትክክለኛው መፍትሄ ኢኮኖሚያዊ ላይ መስራት ነው ። እንደውም በጣም ጥብቅ የሆነ ህግ በውጣቁጥር የበለጠ አልሚዎችን በመጉዳት ችግሩን ከድጡ ወደማጡ ሊወስደው ይችላል ይላሉ።

ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት ባለባቸው ከተሞች የመኖሪያ ቤትን አላግባብ ከህግ ውጭ አገልግሎት ሳይሰጡ ከአንድ አመት በላይ ለሚያቆዪ ባለንብረቶች ከኪራይ ግብር በተጨመሪ የቤቱን ንብረት ግምት ተምን 25 ክርመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ እንዲያወጡ አዋጁ ለየከተሞች መብት ሰጥቶዋል።

ዘገባው የዶይቼ ቬለ ነው።

የዛሬን አያድርገዉና አብሮ መስራት ባህላችን ነበረ🤣🤣
03/05/2024

የዛሬን አያድርገዉና አብሮ መስራት ባህላችን ነበረ🤣🤣

Address

Addis Ababa

Telephone

+251922670068

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Daily Feta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Daily Feta:

Share