Universal Information Ethio times

Universal Information Ethio times Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Universal Information Ethio times, Media/News Company, Addis Ababa.

25/02/2025
25/02/2025

ፍኖተ ፅድቅ

Ten Unknown Facts About  1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germa...
11/10/2024

Ten Unknown Facts About
1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germany, initially producing aircraft engines. The company transitioned to motorcycle production in the 1920s and eventually to automobiles in the 1930s.
2. Iconic Logo: The BMW logo, often referred to as the "roundel," consists of a black ring intersecting with four quadrants of blue and white. It represents the company's origins in aviation, with the blue and white symbolizing a spinning propeller against a clear blue sky.
3. Innovation in Technology: BMW is renowned for its innovations in automotive technology. It introduced the world's first electric car, the BMW i3, in 2013, and has been a leader in developing advanced driving assistance systems (ADAS) and hybrid powertrains.
4. Performance and Motorsport Heritage: BMW has a strong heritage in motorsport, particularly in touring car and Formula 1 racing. The brand's M division produces high-performance variants of their regular models, known for their precision engineering and exhilarating driving dynamics.
5. Global Presence: BMW is a global automotive Company
6. Luxury and Design: BMW is synonymous with luxury and distinctive design, crafting vehicles that blend elegance with cutting-edge technology and comfort.
7. Sustainable Practices: BMW has committed to sustainability, incorporating eco-friendly materials and manufacturing processes into its vehicles, as well as advancing electric vehicle technology with models like the BMW i4 and iX.
8. Global Manufacturing: BMW operates numerous production facilities worldwide, including in Germany, the United States, China, and other countries, ensuring a global reach and localized production.
9. Brand Portfolio: In addition to its renowned BMW brand, the company also owns MINI and Rolls-Royce, catering to a diverse range of automotive tastes and luxury segments.
10. Cultural Impact: BMW's vehicles often become cultural icons, featured in fi

በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች የተከናወነው የመስቀል ደመራ መዝሙር የመጨረሻው ጥናትና ልምምድ *********በ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ከሚቀርቡ ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች አንዱ ለበዓሉ የሚስማ...
25/09/2024

በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች የተከናወነው የመስቀል ደመራ መዝሙር የመጨረሻው ጥናትና ልምምድ
*********

በ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ከሚቀርቡ ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች አንዱ ለበዓሉ የሚስማማ መዝሙር ነው።

ይህ መዝሙር የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ጊዜ ወስደው የሚዘጋጁበት ነው።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ለ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሲያደርገው የነበረውን የመዝሙር ጥናት ያጠናቀቀውም ዛሬ ነው።

በዛሬው ዕለትም ነገ በሚከናወነው የመስቀል ደመራ የሚቀርብ መዝሙር የመጨረሻ ጥናትና ልምምድ ተከናውኗል።

ዕለቱን የሚያወድሱ እና ሌሎች የምስጋና መዝሙራትን ጨምሮ የማዕከሉ ዘማሪያን ከ80 በላይ መዝሙራትን ሲያጠኑ ቆይተዋል።

የመዝሙር ጥናቱ በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በወላይትኛ፣ በጉራግኛ እና በክስታንኛ ተከናውኗል።

ማዕከሉ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል በደመቀ እና ኃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ለማሳለፍ እንደተዘጋጀም ተገልጿል።

በአሰግድ ሲሳይ

Ten Unknown Facts About  1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germa...
15/09/2024

Ten Unknown Facts About

1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germany, initially producing aircraft engines. The company transitioned to motorcycle production in the 1920s and eventually to automobiles in the 1930s.

2. Iconic Logo: The BMW logo, often referred to as the "roundel," consists of a black ring intersecting with four quadrants of blue and white. It represents the company's origins in aviation, with the blue and white symbolizing a spinning propeller against a clear blue sky.

3. Innovation in Technology: BMW is renowned for its innovations in automotive technology. It introduced the world's first electric car, the BMW i3, in 2013, and has been a leader in developing advanced driving assistance systems (ADAS) and hybrid powertrains.

4. Performance and Motorsport Heritage: BMW has a strong heritage in motorsport, particularly in touring car and Formula 1 racing. The brand's M division produces high-performance variants of their regular models, known for their precision engineering and exhilarating driving dynamics.

5. Global Presence: BMW is a global automotive Company

6. Luxury and Design: BMW is synonymous with luxury and distinctive design, crafting vehicles that blend elegance with cutting-edge technology and comfort.

7. Sustainable Practices: BMW has committed to sustainability, incorporating eco-friendly materials and manufacturing processes into its vehicles, as well as advancing electric vehicle technology with models like the BMW i4 and iX.

8. Global Manufacturing: BMW operates numerous production facilities worldwide, including in Germany, the United States, China, and other countries, ensuring a global reach and localized production.

9. Brand Portfolio: In addition to its renowned BMW brand, the company also owns MINI and Rolls-Royce, catering to a diverse range of automotive tastes and luxury segments.

10. Cultural Impact: BMW's vehicles often become cultural icons, featured in fi

በቄሌም ወለጋ በደረሰ የመሬት ናዳ የሦስት ልጃገረዶች ሕይወት አለፈበኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ የሦስት ልጃገረዶች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ደግ...
10/09/2024

በቄሌም ወለጋ በደረሰ የመሬት ናዳ የሦስት ልጃገረዶች ሕይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ የሦስት ልጃገረዶች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ደግሞ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል፡፡

በዚሁ በወረዳው ሶስት ቀበሌያት ጳጉሜ 01 ቀን 2016 ዓ.ም. ዓርብ ሌሊቱን ቤተሰቡ በእንቅልፍ ላይ እያለ በጣለ ከባድ ዝናብ በተለይ ከዞኑ ከተማ ደምቢዶሎ በስተምዕራብ 135 ኪ.ሜ. ግድም ርቀት ላይ በሚገኝ በአንድ አባወራ መኖሪያ ቤት ላይ አፈር ተደርምሶ የቤቱ አባወራ እና እማወራ በህይወት ሲተርፉ የሦስቱን ሴቶች ልጆቻቸውን አስከሬን እንኳ ማውጣት የተቻለው ቅዳሜ ጳጉሜን 02 ቀን 2016 ዓ.ም. በማግስቱ መሆኑን ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

የቄለም ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑራ መሃመድ እንደተናገሩት አደጋው በተከሰተባቸው ሦስት ቀበሌያትየቤት እንስሳትና 20 ሄክታር በሰብል የተሸፈነ መሬት ላይ ጉዳት ደርሶበታል። አደጋው ከተከሰተ በኋላ ከዞን እስከ ወረዳ በተሰጠው ትኩረት ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳያልፍ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ኃላፊው በአደጋው የተፈናቀሉትና በንብረታቸው ላይ አደጋ የደረሰውን ወገኖች ለማቋቋም እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።ዘንድሮ ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 36,409 ተማሪዎች ወይም 5.4 በመቶው ማለፋቸውን የት/ሚኒስቴር ዛሬ በሰ...
10/09/2024

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ዘንድሮ ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 36,409 ተማሪዎች ወይም 5.4 በመቶው ማለፋቸውን የት/ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
ዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ፈተናዉን ከሰጡ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተማሪ አለማሳለፋቸዉን ሚንስትሩ አክለው ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ሐረሪ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከአስፈተኗቸው ተማሪዎች ውስጥ የተሻለ ቁጥር ማሳለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር ዘንድሮ የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ማሳለፍ መቻሉ በሚንስትሩ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡
ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ከለሊት 6 ሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

የሉዓላዊነት ዘንጎች ከጦርነት እስከ ዲፕሎማሲ**********ሉዓላዊነት ምንድን ነው? ሉዓላዊነት ማለት ያለ ምንም ውጫዊ ጣልቃ ገብነት ራስን ለማስተዳደር የሚያስችል የአንድ ሀገር የሥልጣን የ...
08/09/2024

የሉዓላዊነት ዘንጎች ከጦርነት እስከ ዲፕሎማሲ
**********

ሉዓላዊነት ምንድን ነው? ሉዓላዊነት ማለት ያለ ምንም ውጫዊ ጣልቃ ገብነት ራስን ለማስተዳደር የሚያስችል የአንድ ሀገር የሥልጣን የበላይነት ነው። በዓለም አቀፍ መርህ መሰረትም ነጻነት እና የራስ አገዛዝ የሚያረጋግጥ የሀገራት መብት ነው።

የተሟላ ሉዓላዊነት የከፍተኛ ሥልጣን ባለቤትነት፣ የግዛት አንድነት፣ ፖለቲካዊ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡

የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ታሪክ ጥንታዊ ሲሆን ሃገሪቱ በየትኛውም ዘመን ሊተናኮሏት የመጡትን የውጭ ኃይሎች የታገሰችበት ወቅት አልነበረም፡፡

በሀገር ውስጥ እንኳን ሽኩቻ ቢኖር በልጆቿ ክንድ ወራሪዎችን ስትከላከል ኖራለች፡፡

የግብፅ ኃይሎችን ተደጋጋሚ ትንኮሳ መክተው ወራሪዎቹን የበረሃ ሲሳይ ያደረጉት አፋሮች፣ ከመሃዲስት ጋር ሲፋለሙ የተሰውት አጼ ዮሐንስ፣ ዶጋሊ ላይ የጣሊያንን ወራሪ ከአፈር የደባለቁት እነ ራስ አሉላ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ቀንዲሎች ነበሩ፡፡

ባህር ተሻግሮ የመጣውን የጣሊያን ወራሪ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መሪነት በዓድዋ ድል ያደረገችው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ቀጥላለች፡፡

የዓድዋ ድል አፍሪካን እንዳሻቸው ሲገዙ ለኖሩት የአውሮፓ ኃይሎች የሽንፈት በርን የከፈተ፣ በነሱ ቅኝ ግዛት ሲሰቃዩ ለኖሩት አፍሪካውያን ደግሞ የነጻነት ሻማ የለኮሰ ነበር፡፡
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7764

የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታሪካዊው ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡            ...
08/09/2024

የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታሪካዊው ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡
---------------------------------------------
ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም ሐ.ብ.ሚ ( አዳማ - ኢትዮጵያ )
(ሙሉ መልዕክት ከሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media )
የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በታሪካዊው ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ፡ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፡ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት የማኅበራት ማደራጃና ቅርሳቅርስ መምሪያ ኃላፊ ፡ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የአቡነ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ፡ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፡ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች ፡ ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች ፡ የአድባራት ና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፡ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን ፡የመንፈሳዊ ማኅበራት ወጣቶች ፡ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡

በዕለቱም በደብሩ ሊቃውንትና በደብሩ ከሣቴ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን ያሬዳዊ ወረብ የቀረበ ሲሆን ክቡር መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ወልደ ሩፋኤል የደብሩ አስተዳዳሪ አጠቃላይ ዓመታዊ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱም በደብሩ በሚገኘው ታሪካዊ የአብነት ጉባኤ ቤት የተሠሩ ሥራዎች ፡ በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት የተሠሩትን በደብሩ ስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ በጎ ታሪካዊ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት ደብሩ ተራራማ ከመሆኑ የተነሳ በምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውን ገደላማ ተራራን የግዙፍ መግቢያ በርና የደረጃ ሥራዎችን ኃላፊነት በመውሰድ የፒራሚዲ ሪዞርት ባለቤት አቶ ዳንኤል አስፋው 4,500,000 ( አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር ) ወጭ በማድረግ ተሠርቶ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መመረቁ ተገልጿል፡፡ ከፍተኛ ወጭ የወጣበት የመንገድ ሥራ በሙያና በገንዘብ ያገዙ የአቱ ሆቴል ባለቤት አቶ ኢዩኤል ከፍተኛ አበርክቶ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡ አጠቃላይ በክቡር መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ወልደ ሩፋኤል የሚመራው ሰባካ ጉባኤ ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸምና ሰላማዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በመቀጠልም በደብሩ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ዳንኤል ንጉሡ አቅራቢነት በልዩ ልዩ ልማታዊ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አበርክቶ ላላቸው የምስክር ወረቀትና የሽልማት መርሐግብር ተከናውኗል ፡፡

በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ " ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ "
(2ኛ ነገ 6:16) በሚል መነሻ ኃይለ ቃል ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከተት ሊቀ ጳጳስ የዕለቱን ታሪክ ከምዕመናን ሕይወት ጋር በማዛመድ አባታዊ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

የታንዛኒያ ሽንኩርት ሊበላ ነው 😁  የሀገሬ ሰዎች ምን ተሰማችሁ?  🤔 እንደው ልዩነቱን እናጣጥም ይሆን ? በሀገር መሬት የበቀለና ከውጪ ሀገር የተላከን ሽንኩርት የዋጋውስ ልዩነት ምን ያህል...
06/09/2024

የታንዛኒያ ሽንኩርት ሊበላ ነው 😁 የሀገሬ ሰዎች ምን ተሰማችሁ? 🤔

እንደው ልዩነቱን እናጣጥም ይሆን ? በሀገር መሬት የበቀለና ከውጪ ሀገር የተላከን ሽንኩርት የዋጋውስ ልዩነት ምን ያህል ይሆን ?

በአሁን ሰአት በተለያዩ አካባቢዎች ከ 90 - 120 ድረስ በኪሎ እየተሸጠ ይገኛል ።

የአቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ እና የዋጋ ውድነትን ለማስተካከል በሚል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሽንኩርት ከታንዛኒያ ማስገባቱ ተሰምቷል።

እያጣጣማችሁ ልዩነቱን አሳውቁን !

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Universal Information Ethio times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share