ሚዛን ትዩብ "የሙስሊሙ እዉነተኛ ድምፅ"

ሚዛን ትዩብ "የሙስሊሙ እዉነተኛ ድምፅ" ሚዛን ቴሌቪዥን የነባሩ አህለሱና ወልጀማዓ ድምፅ በመሆን ነባሩ አስተምህሮ ትዉፊቱን እሴቱን ተሰዉፉን የአካቢሮቹ የደጋጎቹ ኡለሞች መንገድ ለማስቀጠል የሚተጋ ነዉ

የሳዑዲ ወሓ*ብያ ቀስ እያለ የፓራዳይም ሺፍት እያደረ ነዉኒስፈ ሻዕባን ይቃዐሙ ነበር እንግዲ ታሪካዊ ክሰተት ነዉ ሸይኽ ሱደይስ ኒስፍ ሻዕባን ዱዓ በቪዲዮ አጋርተዋል ሀረመይን ሸሪፈይን በቀጥ...
06/03/2023

የሳዑዲ ወሓ*ብያ ቀስ እያለ የፓራዳይም ሺፍት እያደረ ነዉ
ኒስፈ ሻዕባን ይቃዐሙ ነበር እንግዲ ታሪካዊ ክሰተት ነዉ ሸይኽ ሱደይስ ኒስፍ ሻዕባን ዱዓ በቪዲዮ አጋርተዋል ሀረመይን ሸሪፈይን በቀጥታ ከመግባት ይልቅ ቀኗን ኒስፏን በማሰብ ለረመዷን እንዲያደርሰን ዱዓ አጋርቷል ፡፡ ወሀቢ*ዝ*ም የዲን መሠረት የለዉም ስንል ለማይገባዉ በየ ግዜዉ የሚደረጉ ማሻሻያዎች በቂ ማሣያ ናቸዉ ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም #ተሰዉፍ

ኒስፍ ሻዕባን በታላቁ ኑር መስጂድ በዛሬው ዕለት የሻዕባን ግማሹን አላህ ስራዎቻችን እንዲቀበልና ረመዷንን እንዲያደርሰን በመሻኢኾች ተርቲብ መሠረት ያሲን ቁርዓን በጀመዓ በርካታ ምዕመን ተገኝ...
06/03/2023

ኒስፍ ሻዕባን በታላቁ ኑር መስጂድ

በዛሬው ዕለት የሻዕባን ግማሹን አላህ ስራዎቻችን እንዲቀበልና ረመዷንን እንዲያደርሰን በመሻኢኾች ተርቲብ መሠረት ያሲን ቁርዓን በጀመዓ በርካታ ምዕመን ተገኝቶ በጋራ ተቀርቷል በኡለሞች ደግሞ ለሙስሊሙ ዑማ ለሀገር ዕና ለዓለም የሚደርስ ዱዓ አድርገዋል ፡፡

ማሻአላህ ነበር ....
አላህ በነብዩ በመሻኢኾቹ መጀን ይሁንት መቅቡል ያድርገዉ

የኑር መስጂድ ወጣት ጀመዐ
የዲን ወታደር Ye din wetader
የ ደ/ዘይት ሙስሊም ወጣቶች ማህበር
#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም #ተሰዉፍ

ባለ ብዙ መልኮች ሆ ብሎ በመትመም ለሀገር ነፃነት      በአንድነት ድል ያደረጉበት ቀን   #አደዋ127                       እንኳን አደረሳችሁ !!             #ሚዛን...
01/03/2023

ባለ ብዙ መልኮች ሆ ብሎ በመትመም ለሀገር ነፃነት በአንድነት ድል ያደረጉበት ቀን #አደዋ127

እንኳን አደረሳችሁ !!
#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ

መፈንቅለ መጅሊሱን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኮምቦልቻ ከተማ ለነገ እሁድ በህዝበ ሙስለሊሙ ተጠራ ፡፡መጅሊሱ በተለያዩ አካባቢዎች ህዝባዊ ቅቡልነት በማጣቱ ህዝበ ሙስሊሙ አይወክለኝም እያለ ይ...
18/02/2023

መፈንቅለ መጅሊሱን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኮምቦልቻ ከተማ ለነገ እሁድ በህዝበ ሙስለሊሙ ተጠራ ፡፡

መጅሊሱ በተለያዩ አካባቢዎች ህዝባዊ ቅቡልነት በማጣቱ ህዝበ ሙስሊሙ አይወክለኝም እያለ ይገኛል ፡፡

||   ሸመታና ዘረፋ   ||እዚህ መንደር በሀገር ፍቅር እዉቀት ሸመታ ተጧጡፏል ሌላዉ ድሬደዋ የህዝቡ ኪስ ለማጠብ ለዘረፋ ይሄዳል ፡፡ አህሜ ጀበናዉ ይመቸዉ እጥብ ላስ ነዉስ በፋውንዴሽን ስ...
18/02/2023

|| ሸመታና ዘረፋ ||

እዚህ መንደር በሀገር ፍቅር እዉቀት ሸመታ ተጧጡፏል ሌላዉ ድሬደዋ የህዝቡ ኪስ ለማጠብ ለዘረፋ ይሄዳል ፡፡ አህሜ ጀበናዉ ይመቸዉ እጥብ ላስ ነዉስ በፋውንዴሽን ስም ፡፡

17ቱ የውሀቢያ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አይወክሉንም የዑለሞች ድምፅ - Voice of Ulemas - ዑድ የዲን ወታደር Ye din wetader Yeneta tube የኔታ ቲዩብ የሀይቅ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር/Haik Muslims Youth Associations
#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም

ዜና በዛሬዉ ዕለት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የተወዳጇ እህታችን  Ahmed መፅሐፍ  የተለያዩ አንቂዎች የሀይማኖት አባቶችና የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲሁም የእስልምና ዕና የክርስትነና ተከ...
18/02/2023

ዜና

በዛሬዉ ዕለት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የተወዳጇ እህታችን
Ahmed መፅሐፍ የተለያዩ አንቂዎች የሀይማኖት አባቶችና የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲሁም የእስልምና ዕና የክርስትነና ተከታይ ምዕመን በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም #አሽርቤት

ታላቁ ለሊት ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ ባለ ብዙ ታሪኩ ድንቅ ሌሊት የጌታችን አላህ ድንቅ ተአምራት የታየበት ክስተት በአንድ ሌሊት የተደረገ አስገራሚ ጉዞ በሰውኛ ማይገመቱ ሁነቶች ረሱል ከተኙበት ...
17/02/2023

ታላቁ ለሊት ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ

ባለ ብዙ ታሪኩ ድንቅ ሌሊት የጌታችን አላህ ድንቅ ተአምራት የታየበት ክስተት በአንድ ሌሊት የተደረገ አስገራሚ ጉዞ በሰውኛ ማይገመቱ ሁነቶች ረሱል ከተኙበት ፍራሻቸው እስከ በይተል መቅዲስ ከዛም የከፍታው ወደ ሰማይ የተደረገ ጉዞ በውስጡ የጀነት እና የጀሀነምን ጉብኝት ያካተተ ከአንብያዎች ጋ የተደረገ ምክክር እና ሰላምታ ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም የተላከ መልዕክት።

ዑስማን ኢብን አፋን - ጠሮ መስጅድ ወጣት ማህበር

    #አሁን በኮምቦልቻ ከተማ የፊታችን እሁድ ፀረ መጅሊስ ተቃውሞ ሊደረግ መሆኑን ተሰማ ፡፡      አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏህ ያጀመዐበዉቢቷ ኮምቦልቻ ከተማ ከዳር እስከዳር ያሉት ዑለሞቻ...
17/02/2023

#አሁን

በኮምቦልቻ ከተማ የፊታችን እሁድ ፀረ መጅሊስ ተቃውሞ ሊደረግ መሆኑን ተሰማ ፡፡

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏህ ያጀመዐ

በዉቢቷ ኮምቦልቻ ከተማ ከዳር እስከዳር ያሉት ዑለሞቻችን እና የኮምቦልቻ መጅሊስ ዲናችን ላይ የመጣብንን ፈተና አሳልፈን አንሰጥም በማለት ለመቃወምና የአዲሱ የፖለቲካ መጅሊስ አይወክለንም!!!

በማለት የፊታችንን እሁድ 12/6/2015 ድብልቅልቅ ያለ ሠላማዊ ሠልፍ እንድኖጣ የጠበቀ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

#እና ይሄንን ዜና ለመላው የኮምቦልቻ ሙስሊም እምነት ተከታይ ለሆኑ በሙሉ እንድታስተላልፋልን ሢሉ መሪዎቻችን ትልልቆቹ መሻይኾቻችን በአላህ ስም ጠይቀዋል።

ይሄንን መልእከት ለጓረቤት ለሠፈራቺሁ ሙስሊሞች በሙሉ አስተላልፉልን
#ፆታ እድሜ አይልም እምነት ነው የሚለው


ሼርም አድርጉት አደራ አደራ የዲን ጉዳይ ነው ችላ እንዳትሉት🙏🙏

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም #ትግል1

የአሽር ቤት አብሮት    ነገ  ቅዳሜ          በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት
17/02/2023

የአሽር ቤት አብሮት ነገ ቅዳሜ

በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት

ሚዛን ዜና ወቅታዊ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ጃማ ወረዳ በሙስሊም ማህበረሰቦች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ መዋሉ ተገለፀ ፡፡ በዛሬው ዕለት ጃማ ወረዳ ከሙስሊሞች መካከል በአዲሱ የብልጽግና ...
17/02/2023

ሚዛን ዜና ወቅታዊ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ጃማ ወረዳ በሙስሊም ማህበረሰቦች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ መዋሉ ተገለፀ ፡፡ በዛሬው ዕለት ጃማ ወረዳ ከሙስሊሞች መካከል በአዲሱ የብልጽግና መራሹ መንግሥት የተመሠረተው መጅሊስ ተላላኪ ግለሰቦች ራሳቸውን በመሾም መጂልስነን ብለው መስጊድ አካባቢ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የእስልምና ተከታዩች እኛ አነውቃችሁም በማለት አንቀበላችሁም በማለት የከተማዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ተቃዉሞ በአደባባይ ገለፀ ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድምፅ #ኢስላም #ትግል1

መፈንቅሉ አልሳካ ሲል ተመሳሳይ የተቀመቀመ ፅሁፍ በማዉጣት መቀላቀል እንዲህ ነዉ ተወዛገቡስ ...... ሰዎቹ  ሰፊዉ እስር ቤት ናቸዉ .....ተመሣሣይ ይፃፍላቸዉ ጀምሯል ማን እንደሚፅፋትም ...
16/02/2023

መፈንቅሉ አልሳካ ሲል ተመሳሳይ የተቀመቀመ ፅሁፍ በማዉጣት መቀላቀል እንዲህ ነዉ ተወዛገቡስ ......

ሰዎቹ ሰፊዉ እስር ቤት ናቸዉ .....ተመሣሣይ ይፃፍላቸዉ ጀምሯል ማን እንደሚፅፋትም እንደሚያዘጋጃትም የት እንደሚዘጋጅም ግልፅ ሊሆንላችሁ ይገባልስ ፡፡ ከዑማ ወደ አራት ነጠላነት ተሸጋግረዋል ፡፡

ሰሞነኛ ሰፊ ሀሳብ ስታጋራነን የነበረችዉ የአሸር ቤት መፅሐፍ አስመራቂዋ ጀግኒት Hawlet Ahmed አይናቸዉ ደም የቋጠሩ የታች ሰፈሮች ከህፃናት ሰብሳቢዎች ጋር hack ተደርጎ መጠለፉ አካ...
16/02/2023

ሰሞነኛ ሰፊ ሀሳብ ስታጋራነን የነበረችዉ የአሸር ቤት መፅሐፍ አስመራቂዋ ጀግኒት Hawlet Ahmed አይናቸዉ ደም የቋጠሩ የታች ሰፈሮች ከህፃናት ሰብሳቢዎች ጋር hack ተደርጎ መጠለፉ አካዉንቷ በማስተካከል ላይ መሆኗ ገገልፃለች ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢስላም

ODU Koreen Masgiida fatiih Naqamtee kan kaleessa m. Murtii wabiin gadhiifnan Ajajaan poolisii Angoo isaatiin hidhaa bulc...
15/02/2023

ODU

Koreen Masgiida fatiih Naqamtee kan kaleessa m. Murtii wabiin gadhiifnan Ajajaan poolisii Angoo isaatiin hidhaa bulchu harra gadhiifamaniiru

Meezan Tubee

ሰበር ዜና በነቀምት ከተማ በህገወጥ መንገድ ታፍነዉ ታስረዉ የነበሩት የፈትሕ መስጂድ ኮሚቴ የሀይማኖት አባቶች ከሳምንታት የግፍ ዕስር በሗላ ትላንት ፍርድ ቤቱ በዋስ ለቆ ሲያበቃ ፖሊስ አለቅ...
15/02/2023

ሰበር ዜና

በነቀምት ከተማ በህገወጥ መንገድ ታፍነዉ ታስረዉ የነበሩት የፈትሕ መስጂድ ኮሚቴ የሀይማኖት አባቶች ከሳምንታት የግፍ ዕስር በሗላ ትላንት ፍርድ ቤቱ በዋስ ለቆ ሲያበቃ ፖሊስ አለቅም ካለ በሗላ ዛሬ ረፋድ አካባቢ መለቀቃቸውን ታዉቋል ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢትዮጵያ

አሁን የደረሰን ዜና በዛሬ ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት የነቀምቴ ፈቲሂ መስጊድ ኮሚቴዎች ፍርድቤቱ የዋስ መብታቸው ተጠብቆ ዕያንዳንዱ ተከሳሽ 20,000(ሃያሺ ብር) እንዲለቀቁ የወሰነ ቢሆንም ...
14/02/2023

አሁን የደረሰን ዜና

በዛሬ ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት የነቀምቴ ፈቲሂ መስጊድ ኮሚቴዎች ፍርድቤቱ የዋስ መብታቸው ተጠብቆ ዕያንዳንዱ ተከሳሽ 20,000(ሃያሺ ብር) እንዲለቀቁ የወሰነ ቢሆንም ፖሊስ ሽማግለሌ አባቶችን በማገት አለመፍታቱ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ የመስጂዱ ሙስለሊም ማህበረተሰብ የፍትህ ያለ በማለት ቅሬታዉ እየገለፀ ይገኛል ፡፡

Koree Masgiida fatii Naqamtee hara m.murtii dhiyaachun mirgi wabii jaraa eegamee akka gadi lakkifamanu M.Murtii murtee itti kenne. Poolisinis tokkoon tokkon jaraatif qarshii wabii 20,000(kuma digdama)erga galii taasisaniin booda hidhaa keessa utuu hinbaasin hafee jira.
# # Haqaaf Falmanna # #




#ሚዛን #ኢትዮጵያ

ሰበር ደስ የሚል ዜና በነቀምት ከተማ ከህግ አግባብ ውጭ ለሳምንት ታስረው እስካሁን ፍ/ቤት ሳይቀረቡ የነበሩት የነቀምት ፈቲሂ መስጊድ ኮሚቴዎች 1  መሐመድ አደም ነገዎ2  ማሻአላህ ሰይድ3 ...
14/02/2023

ሰበር ደስ የሚል ዜና

በነቀምት ከተማ ከህግ አግባብ ውጭ ለሳምንት ታስረው እስካሁን ፍ/ቤት ሳይቀረቡ የነበሩት የነቀምት ፈቲሂ መስጊድ ኮሚቴዎች
1 መሐመድ አደም ነገዎ
2 ማሻአላህ ሰይድ
3 አህመድ አደም
4 ዘይኑ መሐመድ
5 ዝናብ ጀማል
6 አቡበከር ሺፋ
7 ኢሣ መሐመድ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዉ የነበረ ሲሆን በዋስ እንዲለቀቁ የነቀምት ከተማ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ማሳለፉ ሰምተናል ፡፡

#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢትዮጵያ

ብልፅግና ሆይ ሽማግሌን ያለወንጀል ማሰር ጀብድ ሳይሆን አሳፋሪ ተግባር ነዉ በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ህገወጥ መጅሊስ አይወክለንም መስጂዶቻችን ሪፎርም በሚል ህገወጥ ታፔላ የመቀራመት ተግ...
13/02/2023

ብልፅግና ሆይ ሽማግሌን ያለወንጀል ማሰር ጀብድ ሳይሆን አሳፋሪ ተግባር ነዉ

በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ህገወጥ መጅሊስ አይወክለንም መስጂዶቻችን ሪፎርም በሚል ህገወጥ ታፔላ የመቀራመት ተግባር ሊቆም ይገባል በሚል ለመብታቸዉ በመታገላቸዉ በመናገራቸው በከተማዋ ከንቲባ ትዕዛዝ ኢ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለዕስር የተዳረጉት ሽማግሌ አባቶች እነ ሸይህ መሀመድ ነገዎ እስካሁን በዕስር ላይ መሆናቸው ታወቀ ፡፡




#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢትዮጵያ

" ዘርና ሃይማኖትን ለፓለቲካ ጥቅም ማዋል ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው " ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክረርስቲያንን በዘር ፖለቲካ ለመሰንጠቅ በተደረገዉ ህገወጥ ተግባር የ...
13/02/2023

" ዘርና ሃይማኖትን ለፓለቲካ ጥቅም ማዋል ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው " ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክረርስቲያንን በዘር ፖለቲካ ለመሰንጠቅ በተደረገዉ ህገወጥ ተግባር የተነሳ በብልፅግና መንግሥት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ከሰሞኑ እየወጡ የነበሩ ሁነቶች ግልፅ ሆነዋል ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ያወጣዉ መግለጫና የአማራ ክልል መንግሥት ያወጣዉ መግለጫ የመንግሥት ዉስጣዊ ሽኩቻ የተጧጧፈ መሆኑ ያመላከተ መሆኑ ለመታዘብ ተችሏል ፡፡በትላንትናው ዕለት ከኦርቶዶክስ ሲነኖዶስ መሪዎች ቆይታ ያደረጉት ፕሬዝደንቷ ሳህለወርቅ ዘዉዴም ከመንግሥት በተቃራኒ ቀይ መስመር ማለፍ ነዉ ሲሉ አስቀምጠዋል ፡፡

እምነቶች ለእኛ አማኞች የመጨረሻ ምሽጎቻችን ናቸው። ብርታት ጽናት ተስፋ ... ይሰጣሉ፡፡ ለጠፋው ሕይወት ሃዘኔን ገልጫለሁ።

ከዚህ በፊት እንዳልኩት ዘርና ሃይማኖትን ለፓለቲካ ጥቅም ማዋል ... ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው። የሰው ልጅ በሕይወቱ፣ በሥራው፣ በማህበራዊ ኑሮው ድንበር ከሌለው እራሱ የእደጋ ምን ነው።

የት ይደርሳሉ ብለን ችላ ያልናቸው ሁኔታዎች ናቸው ማጣፍያውን የሚያሳጥሩት፡፡

የሃይማኖት ጉዳይ የቤተ እምነቶቹ አባቶችና ምዕመናን ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ባሏት ዘመናትን ያስቆጠሩ በህሎቿ ሃይማኖቶቿ ታሪኳ ... እንኮራለን። እንጠብቃቸው፣ ከጥቃት እንከላከላቸው።

ጥንቃቄ፣ ብልሃት፣ ጥበብ፣ የሰከነ አእምሮ፣ እርጋታ፣ አርቆ አስተዋይነት ... የችግሮች መፍቻ ዘዴዎች ናቸው፡፡

የተደረጉትም ሆነ መደረግ ሲገባቸው ያልተደረጉት ሲታዩ የአገር ጽኑ መሠረት የሆኑትና ለድርድር የማይቀርቡ የዜጎች መሠረታዊ መብቶች፣ የሕግ የበላይነት፣ ለሕግ ተገዢነት፣ ተጠያቂነት፣ የሃሳብ ነጻነት፣ መረጃ የማግኘት መብት... የመሳሰሉት ለአደጋ እንዳይጋለጡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ከነበርንበት መከራ ወጥተን ሳናበቃ፣ በአገር በሕዝብ ላይ የደረሱ በርካታ ስብራቶችን ሳንጠግን፣ ሕይወት የሚቀጥፉ ግጭቶችን ሳናስወግድ፣ በርካታ ዜጎቻችን በተፈናቀሉበት፣ በሚሊዮኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ በሚሹበት ተመካክረን ተግባብተን ከመሥራት ሌላ አማራጭ አይታየኝም።

አገሪቱ የሁላችንም ነች። ሁላችንንም ያገባናል። ፈጣሪ ይጠብቀን።

የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ

Yeneta tube የኔታ ቲዩብ Asaye Derbie Ethiopia Insider Ethiopian Media Services EthioTube Ethiopian Human Rights Commission
#ሚዛን #የሙስሊሞችድመምፅ #ኢትዮጵያ

Address

Arat Kilo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚዛን ትዩብ "የሙስሊሙ እዉነተኛ ድምፅ" posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሚዛን ትዩብ "የሙስሊሙ እዉነተኛ ድምፅ":

Share

Category