23/10/2024
እለት እለት ስዎች ሳይገለገሉባቸው አይውሉም ተብለው ከሚታሰቡ ቁሶች አንዱ መስታወት ነው ።
ከፊትለፊቱ የተቀመጠለት ማንኛውንም ነገር ምስል ደግሞ ያሳያል እኛም የምናውቀው ገፃች በዚያው ውስጥ ዘወትር እንፈልገዋለን እክል ካለው ለማስተካከል እና ለማረም እንታትራለን ውብየሆነው የእኛ ውበትነው የምንለው እስኪመጣ እረፍት የለም።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደገኛወዳጆች ከመስታወት በላይ ያሳዩናል ከፍ ሲልም በእጆቻቸው እክሉን ያሳድዱልናል።ሌሎች ደግሞ አሉ ያዩትን ትንሽ ነቅ ህዝብ መሀል የሚለፍፉ ።
በውሀ ከሚጠራው እድፍ በላይ ስለሃጢአት ነቅ እናውጋ።
በዚህ አጭር ወግ ውስጥ እራሳችንን እንፈልግ እና ፊልሙ ሲያበቃ ራሳችንን ይህን መጠይቅ እንጠይቅ ።
አንተ የትኛው ነህ?
እንደግዑዙ መስታወት የሰዎችን እክል በዝምታ ለግለሰቡ የምታሳየው ?
ወይስ
እንደ መልካም ባልንጀራ ያየኸውን በወዳጅ ልብ በእጆችህ የምትሰድ?
ወይስ
"ሰዎች ሁሉ ይሔን ሰው እዩት ቆሻሻ አለበት" የምትል?