
23/09/2025
“ ባርሴሎና እና ሜሲን አመሰግናለሁ “ ዴምቤሌ
የባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ኡስማን ዴምቤሌ ከሽልማቱ በኋላ የቀድሞ ክለቡን ባርሴሎና ማመስገን እንደሚፈልግ ገልጿል።
“ ባርሴሎና ማመስገን እፈልጋለሁ “ ያለው ዴምቤሌ “
እንዲሁም ሊዮኔል ሜሲን ማመስገን እፈልጋለሁ ከእሱ ብዙ ተምሬያለሁ “ ሲል ተናግሯል።
የተበረከተለት ሽልማት በቡድን ስራ የመጣ መሆኑን የገለፀው ዴምቤሌ “ የቡድን አጋሮቼን በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ “ ብሏል።
“ የትውልድ መንደሬን ከልብ አመሰግናለሁ ወደዛ የመሄድ አጋጣሚ ሳገኝ የአካባቢው ሰው እዚህ እንድደርስ ረድቶኛል “ ዴምበሌ