28/10/2024
ብሔራዊ አገራዊ ክብርን ማስከበር እና የሀገር ሉዐላዊነትን መጠበቅና ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የውዴታ ግዴታ እንደሆነ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም (አሶሳ) ለ 2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የሀገር መከላከያ ምልመላ እየተካሄደ ነው። ምልመላውን በተሳካ ሁኔታ በማከናወን ክልሉ የተሰጠውን ኮታ መሸፈን እንዲችል ትዕዛዝ ተላልፏል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የ2017 በጀት አመት የመጀመርያ ዙር ምልመላ ጀምሯል፣ በዲሲፕሊን፣ በታማኝነት እና በጠንካራ ደረጃ የክልሉ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች ይህንን ሂደት እንዲደግፉና እንዲቆጣጠሩ ስምሪት ተሰጥቷል።
የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ በዞኖችና ወረዳዎች የሚሰማሩ አመራርና ባለሙያዎችን ለምልመላው ስኬታማነት የማስተባበር ጥረቶችን እንዲመሩ መመሪያ ሰጥተው በሥርዓት የተሞላ አካሄድ ማከናወን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ክቡር አቶ ቢንያም መንገሻ እንዳሉት ብሔራዊ አገራዊ ክብርን ማስከበር እና የሀገር ሉዐላዊነትን መጠበቅና ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የውዴታ ግዴታ እንደሆነ ገልፀው አሁን ላይ የሚደረገው ምልመላ የኮታ ጉዳይ ሳይሆን የኢትዮጵያን የአንድነት፣ የዲሲፕሊን እና የማይናወጥ የሀገር ፍቅር እሴቶችን የሚያንፀባርቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ለማፍራት ያለንን አገራዊ ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳያል። በጋራ፣ የወደፊት ሰላምና ደህንነትን እንገነባለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መረጃው የክልሉ ሠላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ነው።