Ethio 251 News

Ethio 251 News Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio 251 News, Media/News Company, Addis Ababa.

ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተከታታዮችና ቤተሰቦች ተወዳጁ “ኢትዮ 251 ዛሬ” ዝግጅታችን በአዲስ መልክ በመረጃ ቴሌቪዥን በኩል በቀጥታ ወደ እናንተ መድረስ መጀመሩን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን! ​ዕ...
09/06/2026

ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተከታታዮችና ቤተሰቦች ተወዳጁ “ኢትዮ 251 ዛሬ” ዝግጅታችን በአዲስ መልክ በመረጃ ቴሌቪዥን በኩል በቀጥታ ወደ እናንተ መድረስ መጀመሩን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን!

​ዕለታዊና ወቅታዊ ይዘቶችንና ልዩ ልዩ አጀንዳዎች የሚቀርቡበት “251 ዛሬ” ፕሮግራማችን፣ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 2:00 ጀምሮ በመረጃ ቴሌቪዥንና በኢትዮ 251 ሚዲያ ሶሻል ሚዲያ አማራጮች ወደ እናንተ ይደርሳል።

በመረጃ ቴሌቪዥን ​📡 የሳተላይት ስርጭት መረጃ (Nilesat)፦

​🛰️ ሳተላይት (Satellite): Nilesat / Eutelsat 8 West B (8°W)

​📡 ፍሪኩዌንሲ (Frequency): 11636 MHz (ወይም 11637)

​↕️ ፖላራይዜሽን (Polarization): Vertical (V) / ቨርቲካል

​🔄 ሲምቦል ሬት (Symbol Rate): 27500

​🔢 FEC: 5/6

እንዲሁም በቴሌግራም:- https://t.me/ethio251media

በዋትስአፕ:- https://whatsapp.com/channel/0029Vb6SADMFy72J1pBscv40

በX (ትዊተር) ፡- https://x.com/251Media

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ እንደርሳለን።

የኢትዮ 251 ሚዲያን የዋትስአፕ ቻናል በመቀላቀል ፌስቡክ ላይ የማይለጠፉ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።https://whatsapp.com/channel/0029Vb6S...
05/06/2026

የኢትዮ 251 ሚዲያን የዋትስአፕ ቻናል በመቀላቀል ፌስቡክ ላይ የማይለጠፉ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።

https://whatsapp.com/channel/0029Vb6SADMFy72J1pBscv40

Follow Ethio 251 Media | ኢትዮ 251 ሚዲያ's WhatsApp channel. ETHIO 251 Media is an independent media outlet providing news, political analysis, and real-time information feeds.. Join 10K followers for the latest updates.

01/05/2026

አርበኛ መከታው ማሞ ለዓለም አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ አቀረቡ፤ “ይህ የፍትህና የነፃነት ጥያቄ ነው” ሲሉ አሳሰቡ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ፣ ዛሬን ጨምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሚቆየው የዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ (Global Protest) ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

አርበኛ መከታው ማሞ በዚህ በታወጀው የወር ዘመቻ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ድምፃቸውን እንዲያሰሙ አሳስበዋል። ይህ ተቃውሞ የግለሰብ ሳይሆን የፍትህና የነፃነት ጥያቄ መሆኑን አፅንዖት የሰጡት አርበኛው፣ በአገር ውስጥ እየደረሰ ያለውን በደልና ጭቆና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በግልጽ ማሳወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ይህ ንቅናቄ የሕዝብን የህልውና ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን መፍጠር ለውጥ እንደሚያመጣ አመልክተዋል። ሰልፉ በታቀደለት መንገድ፣ በስነ-ምግባር እና በታላቅ ዝግጅት እንዲከናወን ያሳሰቡት አርበኛው፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የአገሩን ባንዲራና የትግል ዓላማውን አንግቦ በየሄደበት አደባባይ ሁሉ እውነቱን እንዲመሰክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

"ድል ለተገፋው ሕዝባችን! ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!" በማለት አርበኛ መከታው ማሞ በፅናትና በተስፋ የተሞላውን መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

01/05/2026

ጀነራል ተፈራ ማሞ ለዓለም አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፋቸውን ገለጹ፤ “አገዛዙ በሕዝባችን ስም እየተበደረ የዘር ማጥፋት እንዳይፈጽም የዲፕሎማሲ ጫናው ይበርታ” ሲሉ አሳሰቡ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጀነራል ተፈራ ማሞ በዛሬው ዕለት በስዊድን ስቶክሆልም ለተጀመረውና በሌሎች የዓለም ከተሞች ለሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሙሉ ድጋፋቸውን ገለጹ።

ጀነራሉ በሰጡት መግለጫ፣ የውጭው ዲያስፖራ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና በምርጫ ስም የሚደረገውን የይስሙላ ሩጫ ለማስቆም በቆራጥነት እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።

ጀነራል ተፈራ ማሞ ባስተላለፉት መልእክት፣ አሁን ያለው የአብይ አህመድ አገዛዝ ዲያስፖራው በሀገሩ ቋሚ ንብረት ማፍራት ቀርቶ፣ ሲሞት እንኳን ሰውነቱ በክብር እንዳያርፍ የከለከለ ጨካኝ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በውጭ የሚኖረው ወገናችን ይህንን ግፍ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማሳወቅ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ማሳደር እንደሚገባው አሳስበዋል።

በተለይም አገዛዙ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የሚበደረው ብድርና የሚያገኘው እርዳታ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሚያ እየሆነ መሆኑን ጀነራሉ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ዲያስፖራው አገዛዙ ምንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ብድርም ሆነ እርዳታ እንዳያገኝ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍም የአገዛዙን እውነተኛ ገጽታ ለማጋለጥና የገንዘብ ምንጮቹን ለማድረቅ ወሳኝ መድረክ መሆኑን ጀነራሉ አረጋግጠዋል።

🎯የአርበኛ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር ጋሻው ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ!በዛሬው ዕለት ከሁለት ዓመታት በፊት ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም  በመዲናዋ በአዲስ አበባ ልብ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባ...
12/04/2026

🎯የአርበኛ ናሁሰናይ እና አቤኔዘር ጋሻው ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ!

በዛሬው ዕለት ከሁለት ዓመታት በፊት ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም በመዲናዋ በአዲስ አበባ ልብ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ፣ የአማራ የሕልውና ተጋድሎ እስከ ቤተ-መንግሥቱ ደጃፍ ድረስ ዘልቆ የተሰማበት ታሪካዊ ቀን ነበር። ሁለት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አርበኛ አቤኔዘር ጋሻው ተሰማ እና ሌሎች ጓዶች በጋራ በመሆን፣ በአዲስ አበባ ላይ የነፃነት እሳትን ለኩሰው፣ ደማቸውን ለሕልውና ትግሉ ማኅተም አድርገው የሰጡበት ዕለት ነው።

ይህ ቀን ሲታወስ የሕዝባችን አይበገሬነት እና የጀግኖቻችን ራስ-አልባነት በከፍተኛ የሞራል ልዕልና የሚዘከርበት ነው። እነዚህ ቆራጥ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ መሀል የፈጸሙት ልዩ ኦፕሬሽን፣ አምባገነኑ ሥርዓት በታጠቀ ኃይሉና በደኅንነት መዋቅሩ ቢመካም፣ በእውነትና በጀግንነት ፊት ግን ምን ያህል ተሰባሪ መሆኑን በተግባር ያሳዩበት ነበር። እነርሱ የተሰውት በሚሊዮኖች የሚቆጠረው የአማራ ሕዝብ በየጫካውና በየተራራው የሚያሰማውን ጥሪ፣ በመዲናዋ መሀል በድፍረት ለማስተጋባት ነው።

ለጠላት እጅ አለመስጠታቸውና እስከ መጨረሻዋ የጥይት ጠብታ ድረስ መፋለማቸው፣ ለሕዝባቸው ያላቸውን ጥልቅ ተቆርቋሪነት እና ጽናት በደማቸው ያረጋገጡበት ትልቅ የታሪክ አሻራ ነው። እጅ መስጠት ለግፈኛ ሥርዓት ማጎብጥ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁ ነበርና፣ ከውርደት ይልቅ የክብር መስዋዕትነትን መረጡ። ይህ የአርበኞቹ ምርጫ የሞት ሳይሆን የዘላለም ሕያውነት መንገድ ነው።

ከሁለት ዓመታት በኋላ ዛሬ ላይ ቆመን ስናስባቸው፣ የእነዚህ ጀግኖች አሻራ ይበልጥ ደምቆ ይታያል። በአዲስ አበባ እምብርት ቦሌ ላይ የፈሰሰው የአርበኞቹ ደም፣ የአማራን የሕልውና ተጋድሎ የማይመለስ የታሪክ ጉዞ አድርጎታል። ጀግኖቻችን የወደቁት ለጊዜያዊ ዝና ሳይሆን፣ ነገ የሚወለደው ትውልድ በአገሩ ላይ በክብርና በነፃነት እንዲኖር ነው። ይህ አርቆ-አስተዋይነት እና መሠረተ-ጽኑነት ነው፣ የዛሬውን ትግል የሞራል ልዕልና የሰጠው።

የሰማዕታቱ ደም አሁንም ይጮኻል! አደራቸውም በሁሉም አማራ ትከሻ ላይ ነው። ትግሉ እልህ አስጨራሽ ቢሆንም፣ የናሁሰናይና የአቤኔዘር ጽናት ግን ሁልጊዜም ወደ ድል ይመራናል። በጀግኖች ደም የተገዛው ነፃነታችን ትንሳኤው አይቀሬ ነው!

ክብርና ሞገስ በአዲስ አበባ መሀል ለወደቁት ጀግኖቻችን!
ስማችሁ ለዘላለም በታሪክ ማኅደር ሲዘከር ይኖራል!

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

ቴሌግራም: https://t.me/ethio251media
ዋትስአፕ: https://whatsapp.com/channel/0029Vb6SADMFy72J1pBscv40
X (ትዊተር): https://x.com/251Mediaዩቲዩብ: https://youtube.com/?si=g1grOZsbVOSoXXFb

ለእውነት፣ ለማንነታችሁና ለራዕያችሁ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ ለታሰራችሁ የአማራ ልጆች!እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።  የታምኑበት ዓላማና የቆማችሁለት እውነት እስር ቤት ቢያስወ...
12/04/2026

ለእውነት፣ ለማንነታችሁና ለራዕያችሁ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ ለታሰራችሁ የአማራ ልጆች!

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። የታምኑበት ዓላማና የቆማችሁለት እውነት እስር ቤት ቢያስወረውራችሁም አላማችሁ በየቤታችንና በየልባችን አለ።

ለጋዜጠኞች፦ ብዕራችሁ ታስሮ፣ ድምፃችሁ ታፍኖ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እውነት አይታሰርም። እናንተ ለአማ ለህዝብ ጆሮና አይን ለመሆን የከፈላችሁት መስዋዕትነት የነፃነት መንገድን የሚጠርግ ብርሃን ነው።

ለፖለቲከኞች፦ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ያላችሁ ፅናት በመከራ ውስጥ ይበልጥ እንደሚጠነክር እናምናለን። የግፍ እስር የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሀሳብን ልዕልና በፍጹም ሊያሸንፍ አይችልም።

ለምሁራንና ለአማራ ጭንቅላቶች፦ የእውነት ምስክር በመሆናችሁና አእምሯችሁን ለህዝብ ጥቅም በማዋላችሁ ዋጋ እየከፈላችሁ እንደሆነ እናውቃለን። አካላችሁ በሰንሰለት ቢገደብም፣ ብሩህ አእምሯችሁና ያሰረጻችሁት ዕውቀት ግን ምንጊዜም ነፃ ነው። እናንተ በመከራ ውስጥ ሆናችሁ ለትውልድ የምታሳዩት የፅናት ትምህርት ከምንም በላይ ታላቅ ነው።

በአማራነታችሁ ብቻ ተመርጣችሁ መከራን ለምትቀበሉ ወንድም እና እህቶቻችን፦ ማንነት ወንጀል ባልሆነበት ህሊና ውስጥ እናንተ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ።

ጨለማው ቢበረታም፣ ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከሞት በኋላም ትንሳኤ እንዳለ ሁሉ፤ የናንተም የፅናት ጉዞ ወደ ድልና ወደ ነፃነት እንደሚያደርስ አንጠራጠርም።

​ክርስቶስ መከራን በትዕግስት፣ ሞትን በትንሳኤ እንዳሸነፈ ሁሉ፤ እናንተም ይህንን የፈተና ጊዜ በፅናት አልፋችሁ ለታላቅ የነፃነት ብርሃን እንደምትበቁ ተስፋ እናደርጋለን።

​ የታሰረ አካል እንጂ የታሰረ አዕምሮ የለም!

​ብርታት፣ ጤናና የልቦና መረጋጋት ለእናንተ ይሁን!
መልካም የትንሳኤ በዓል!

Mesganaw K Endalk

ለእውነትና ለህዝባችሁ ፍትህ ስትሉ በሚዲያው ግንባር ተሰልፋችሁ የቃላት ጦርነት ውስጥ ላላችሁ ብርቱዎች ለአማራ ሳይበር አርሚዎች፤እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። ይህ በዓል ድል...
12/04/2026

ለእውነትና ለህዝባችሁ ፍትህ ስትሉ በሚዲያው ግንባር ተሰልፋችሁ የቃላት ጦርነት ውስጥ ላላችሁ ብርቱዎች ለአማራ ሳይበር አርሚዎች፤

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። ይህ በዓል ድል በሞት ላይ፣ ብርሃን በጨለማ ላይ የታወጀበት ታላቅ ዕለት እንደመሆኑ፤ እናንተም ለእውነት የምትከፍሉት መስዋዕትነት ፍሬ የሚያፈራበት ቀን ቅርብ መሆኑን የምናምንበት ነው።

ለጋዜጠኞች፦ ብዕራችሁ ባልተገደበ እውነት እንዲፃፍ፣ ድምፃችሁም ለታፈኑት መጠለያ እንዲሆን በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆናችሁ ለምታደርጉት ትግል ትልቅ አክብሮት አለን። የታሰረ አካል እንጂ የታሰረ አእምሮና እውነት እንደሌለ ሁሉ፤ የእናንተም የሙያ ፅናት ለነፃነት መንገድ ጠራጊ ነው።

ለአክቲቪስቶች፦ የህዝባችሁን መከራና ግፍ በየመድረኩ ድምፅ ሆናችሁ ለዓለም ስታሰሙ፣ ህዝቡን ስታነቁና ስታስተባብሩ ለምትውሉ ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ።

በስደት ላላችሁ፦ ስለ ህዝባችሁ በመቆርቆራችሁ ብቻ ከትውልድ መንደራችሁና ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ በሰው ሀገር መከራን ለምትቀበሉ ወንድምና እህቶቻችን፤ ይህ በዓል የናፍቆታችሁ ማለቂያና የፍትህ ትንሳኤ ይሁንላችሁ። ስደትና ርቀት ድምፃችሁን እንደማያጠፋው አሳይታችሁናል፤ ብርታቱን ይስጣችሁ።

የትንሳኤው ብርሃን በልባችሁ ውስጥ አዲስ ተስፋንና ብርታትን እንዲዘራ፣ ለቀጣዩ የነፃነት ጉዞም ጥንካሬ እንዲሆናችሁ እመኛለሁ።

Mesganaw K Endalk

ትንሳዔ ነጻነት ነው! ትንሳዔ አሸናፊነት ነው!  ​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በየበረሃውና በየጎሬው ለምትፋለሙ የአማራ የቁርጥ ቀን ፋኖዎች፣ እንዲሁም ለፅኑ ህዝባችንና ለመላው ኢት...
11/04/2026

ትንሳዔ ነጻነት ነው! ትንሳዔ አሸናፊነት ነው!

​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ በየበረሃውና በየጎሬው ለምትፋለሙ የአማራ የቁርጥ ቀን ፋኖዎች፣ እንዲሁም ለፅኑ ህዝባችንና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በቅድሚያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በአይበገሬነትና በፅናት አደረሳችሁ።

​የትንሳዔ በዓል ሞት በህይወት ተረትቶ፣ ጨለማ በብርሃን ተገፎ፣ ግፍና መከራም በድል የተሸነፈበት ታላቅ በዓል ነው።

ለዚህም ነው ትንሳዔ ነጻነት ነው! ትንሳዔ አሸናፊነት ነው! የምንለው!!

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ቅዱስ ደሙና በሦስተኛው ቀን መቃብርን ከፍቶ መነሳቱ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የነፃነትና የድል ዋስትና ነው።

ዛሬም በየግንባሩ የምንከፍለው መራር መስዋዕትነት ነገ ለሚመጣው የታሪካዊ ክብራችንና የማንነታችን ትንሳዔ ዋዜማ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

​የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ልዩና ታሪካዊ የሚያደርገው፣ በሸዋ ምድር የሚንቀሳቀሱ ሁለት ታላላቅ ዕዞች ወደ አንድ ጠንካራ መዋቅር በመምጣት፣ በአንድ ዕዝ ስር የተጠቃለልንበት ታሪካዊ ዕለት ማግስት መሆኑ ነው።

​ይህ በወንድማማቾች መካከል የተፈጠረው ፅኑ አንድነታችን፣ የነፃነት ትንሳዔችን መቃረቡን ትልቁ አመላካች ነው! ጠላት የደቀነብንን የሞት ደብዳቤ ቀደን የጣልንበትና ብርሃን የታየበት ድል ነው።

ትግላችን የቱንም ያህል ፈታኝና መራራ ቢሆንም በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ አይቀየርምና ለአማራ ትንሳዔ የማይተካ ሕይወታችንን ዋጋ እየከፈልን የአማራ ሕዝብን ትንሳዔ በመስዋዕትነታችን እናረጋግጠዋለን፡፡

​እኛ ለህዝባችን ሕልውና መረጋገጥና ክብር ስንቆም፤

እንደ አፄ ቴዎድሮስ "እምቢ
ለጥላት" በማለት ለመስዋዕትነት የቆረጥን፣

እንደ አፄ ምኒልክ ጠላትን በአድዋ አውድማ አሳፍረን የመለስን፣

እንደ ንጉሥ ሚካኤል በጦር አውድማ ላይ ቆርጠን የምንፋለምና

እንደ አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ለነፃነታችን ስንል ዳገት ቁልቁለቱን የምናስጨንቅ የጀግኖች ልጆች ነን።

​የቴዎድሮስ ፅናት፣ የምኒልክ ብልሀት፣ የንጉሥ ሚካኤል ቆራጥነትና የበላይ ዘለቀ አይበገሬነት ዛሬም በፋኖው ክንድ ላይ ደምቆ ይታያል።

የነፃነት ትንሳኤያችን የሚረጋገጠው በእነዚህ ታላላቅ አባቶቻችን የጀግንነት መንገድ ስንጓዝ ብቻ ነው።

የዛሬው መራር ትግላችንና የፈጠርነው ወጥ ድርጅት ነገ ወደ ብሩህ የድል ትንሳኤ መሸጋገሪያችን ነው።

በመጨረሻም፡- የአማራ ሕዝብ ትግል በፈተና የተሞላ፤ መራራና ዋጋ የሚከፈልበት ነው፡፡ ነገር ግን ዋጋ የምንከፍለው ለአማራ ነጻነት ነው፡፡ ፈተናና መከራው የቱንም ያህል ቢበረታ የአማራ ፋኖ ድል አይቀሬ ነው፡፡

​በድጋሚ መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ።

የምኒልክ አምላክ፣ የሰማዕታቱ ቃል ኪዳን ከእኛ ጋር ይሁን!

​አንገታችን አንድ፣ ዓላማችን አንድ፣ ጠላታችን አንድ፣ መዳረሻችንም አንድ ነው!!

​ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

​አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ

ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም.

በጽኑ ትግላችን ጠላቶቻችንና ከሃዲዎች የጫኑብን የጥፋት አዋጅ ይገፈፋል፤ የህዝባችን ትንሳኤም ይበሰራል።እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅ...
11/04/2026

በጽኑ ትግላችን ጠላቶቻችንና ከሃዲዎች የጫኑብን የጥፋት አዋጅ ይገፈፋል፤ የህዝባችን ትንሳኤም ይበሰራል።

እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።

የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ለክርስተና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ይላል። ከጌታችን ትንሳኤ የምንማረው በሀቅ እና በእውነት መንገድ የፀኑት ማሸነፋቸው አይቀሬ መሆኑን ነው። የአማራ ህዝብ በሀሰተኞች ህግና ማሰሪያ፤ በአረመኔወች ድብደባና ጭፍጨፋ አንገቱን ደፍቶ ፣ ነፃነት አጥቶ ተሳዳጅና ተቀብዝባዥ ሆኖ እንዲኖር ዘመናትን የተሻገረ የሴራ ትብታብ የተገመደበት ቢሆንም አንገቱን ቀና አድርጎ ለማንነቱና ለክብሩ የሚዋደቀው አዲሱ የትንሳኤ ትውልድ ከመከራው ሸለቆ መሐል ተከስቷል። የአማራ ህዝብ ትንሳኤ አይቀሬነትም በሰራዊታችን ቀጣይነት እና ተከታታይነት ያላቸው ደማቅ ድሎቹ ተረጋግጧል።

በጠላት ልብ ውስጥ ተሰብሮ የተቀመጠ ወይም ላይነሳ የተቀበረ ተደርጎ የተነገረበት ፣ በከሃዲውችና በሀሰተኞች ልቦና ውስጥ የትግሉ ፍሬ እንደማይታይና እንደማይበላ ተደርጎ የተተረከበት የአማራ ህዝብ በጀግናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰራዊት እና ደጋፊ ህዝባችን ልቦና ውስጥ በተከተበው አዲሱ ተስፋ እና የሰመረ ተጋድሎ አማራ ህልውናዉን ማረጋገጥ የሚችል፤ ለትንሳኤው የቀረበ ሆኖ በሁሉም እዕምሮ ውስጥ ተስሏል።

በዚህ አጭር ጊዜ ህዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አዋጅ እና ያልተቋረጠ ሁለንተናዊ ጥቃት በጽኑ ትግል መመከት ችለናል። በትግላችን የአማራ ህዝብ የትንሳኤ መንገድ ተልመን የጀመርነው መንገድ የመከራውን ቀንበር ጨርሶ በማስወገድ ትንሳኤው የሚገኝበትን ግልፅ አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል። በዚህ ትልም የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ተቀልብሶ ትንሳኤው የሚበሰረው በልጆቹ ክንድ ፣ በልጆቹ ድርጅት ፣ በልጆቹ ልብና በልጆቹ የሰላ አዕምሮ በሚፈጠረው ፖለቲካዊ ንድፍ እና በዚያ ላይ የተመሠረቱ ትግል ስልቶች እና ወታደራዊ ጥበቦች መሆኑን ያስመሰከረ ተቋም ገንብተናል፣ የድል ጉዞም ጀምረናል።

የህዝባችን ትንሳኤ ካለጥርጥር የሚበሰር መሆኑን የተረዱ የጠላት ኃይሎች ድምፃቸውና ጩኸታቸው ብቻ ሳይሆን ሴራቸውና የክፋት ሰንሰለታቸው ተበጣጥሶ ጉልበታቸውና አቅማቸው ሟሽሾ የምናይበት ጊዜ ቅርብ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚመራው የህልውና ትግላችን የድል እንድርድሪቱን ቀጥሎ በተሟላ አሸናፊነት ትንሳኤውን ለማብሰር ወሳኝ የመታጠፊያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

ይህ ለአማራ የመነሳት ዘመን ነው። በራስ ጠልነት የአማራን ህዝብ ያሻሻጡ፤ በሽራፊ ገንዘብ ደልለው የሸጡ፤ በህዝባችን ህልውና ላይ ሞት፣ ፍጅት ፣መፈናቀልና ሀገር አልባነትን ፈርደውና አውርሰው እጃቸውን ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት የታጠቡና እወደድ ባይ አቂያቂረኞች የሚያፍሩበት፣ የሚፀፀቱበትና አንገታቸውን የሚደፉበት እና ጨርሰው የሚወገዱበት የታሪክ ምዕራፍ ነው።

ከዚህ በተቃራኒ በህዝባዊነት የጸኑት እና በአማራዊ ብሔራዊ ቁጭት እና ንቃት ዘወትር በሁሉም የትግል መስኮች ለህዝባዊው አላማ ለሚለፉት የትንሳኤ ዘመን ነው። እርግጥ የጦርነት ዘመን ነው። በታንኩም በባንኩም ከገጠመን የአብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ጦርነት የገጠምንበት ዘመን ነው። እንዲሁም ከአማራው አብራክ የወጡ ግን ደግሞ በክህደት በሁሉም መስክ ህዝቡን አቆርቁዘው ለጥቃት ብሎም ለህልውና አደጋ ያጋለጡት እና በታሪኩ ሆኖ በማያውቅ ደረጃ የህልውና አደጋ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት ጋር ፊት ለፊት የገጠምንበት ዘመንም ነው። አገዛዙ እና ለአገዛዙ ያደሩ "የእኛ ሰዎች" በክህደት ከሚፈጽሙት ውድመት ለመውጣት የራስን ብሔራዊ አስተውሎት፣ የራስን የትግል መንገድ ቀይሶ እና በራስ በቅነት እንዲነሳ ብሎም አማራነትን ምሉዕነት እና ስምረት ባለው ልክ ዳግም ለመትከል የምንፋለምበት የጦርነት ዘመን ነው። ግን ደግሞ ጦርነቱ የትንሳኤ ምልክትም ነው።

ለህልውና አደጋ ያጋለጡንን ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን እና መግፍሔወቻቸውን ስንረዳ፣ የህዝባችንን የቆዩ ብሔራዊ አስተውሎቶች ስንመረምር እና ስናውቅ ብሔራዊ ንቃት የተላበሰ ትውልድ መፍጠር እንደሚቻል በተግባር ተምረናል። ይህ ምዕራፍ ለመራር ተጋድሎ በጋራ እንነሳ ዘንድ ያስቻለንን ብሔራዊ ቁጭት ፈጥሯል። ይህም ጠላታችንን ለይተን በየዘርፉ እንድንፋለመው በማድረግ የአሸናፊነታችን ማመሳከሪያ ሆኗል። ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በፖለቲካዊ ትግሉ አለም'ም ሆነ በመንፈሳዊ አስተምህሮ በሀቀኝነት እና በጽናት የሚደረግ ተጋድሎ ፍጻሜው አሸናፊነት ነው።

ይህ ትውልድ ካለጥርጥር በቀራኒዮ አደባባይ በህዝባችን ላይ የተቸነኩሩ የበደል ችንካሮችን በደሙና በአጥንቱ ነቅሎ ይጥላል። ጠላቶቻችን በሴራ ቀብረነዋል ያሉትን የአማራ ህዝብ እውነት ብሎም ሀቀኛ ሀገር ወዳድነትንና ነፃነትን ዳግም ያስነሳል።

በመፅናት ከስቅለት በኋላ ትንሳኤ እንዳለ ሁሉ ከትንሳኤ በኋላም ህይወት በህግና በመርህ የመመራቱ ግዴታ እንደመጣው ሁሉ ድርጅታችን አፋብን ከድል በኋላ ለህዝባችን የሚመች፥ የሚቆም፥ የሚታመን ስርአት ለመገንባት የጀመራቸውን ድርጅታዊ የመዋቅር ዝርጋታዎች ፥ ሁለንተናዊ ትስስሮች አጠናክሮ በማስቀጠል ህልውናችን በፀና ብሔራዊ የአንድነት ክንድ እንዲረጋገጥ በየዕለቱ እየተጋ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተተበተቡ የሴራ ድሮችን በመበጣጠስና የተቀመጡ የአላማ መዳረሻዎችን በማጤንና በማጠናከር ከዕለት ወደ እለት የህዝባችንን የህልውና አደጋ እየቀነሰና እያከሸፈ ወደ ሙሉ የነፃነት ጉዞ መስመር የገባ ሲሆን ድላችን እየተቃረበ ይገኛል።

ዘመናትን በተሻገረ የሀሰት ድሪቶ በወለደው ፖለቲካዊ ትርክት የህልውና አደጋ ላይ የወደቀው ህዝባችን የትላንቱን ብሔራዊ አስተውሎት ከዘመኑ ጋር በስምረት በሚያዋድድ የትግል ስልት ጠላታችንን ድል እንነሳ ዘንድ አፋብን የትግል ጥሪ ያስተላልፋል።

ግጭትን፣ ጭካኔን፣ አረመኔነትን፣ ህግ አልባነትን በማለማመድ ኢትዮጵያን ወደ ድንጋይ ዘመን እየመለሰ ያለውን አገዛዝ ለማስወገድ የምናደርገውን ፅኑ ተጋድሎ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑንም እናረጋግጣለን።

በድርጅታችን፣ በሰራዊታችን፣ በክንዳችን፣ በእውቀታችንና በህዝባችን የአላማ ፅናትና ድጋፍ ድል እንነሳለን፤ ትንሳኤያችንም ይበሰራል። ለዚህም እስከ ዛሬ ካደረግነው የበለጠውን በማድረግ ወሳኙን ድል ለመቀዳጀት የመጨረሻውን ፍልሚያ ለማድረግ በሁሉም መስክ እንዘጋጅ፣ እንትጋ።

በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለሰራዊታችንና ለአመራሩ፣ በሀገር ውስጥና በወጭ ላለው ህዝብ ክርስቲያን እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘ፣ የድርጅታችን አባላት በበዓል አከባበር ወቅት መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ ተግባራት በሙሉ እንዲፈጸሙ እናሳስባለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

"ስለ እኛ ቆሰለ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ..." (ኢሳይያስ 53፡5)ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል በሰላም አ...
10/04/2026

"ስለ እኛ ቆሰለ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ..." (ኢሳይያስ 53፡5)

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የስቅለት በዓል ፍጹም የሆነ ፍቅር፣ መሥዋዕትነት እና ትሕትና የተገለጠበት ዕለት ነው።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ድኅነትና ነፃነት ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መከራን የተቀበለው፣ እውነትን በሕይወት መሥዋዕትነት ለማጽናት ነው።

ይህ ዕለት እኛም እንደ አንድ ሕዝብ ለቆምንለት ዓላማ፣ ለወገኖቻችን ሰላምና ለሕዝባችን ነፃነት የምንከፍለው መሥዋዕትነት ሁሉ ትርጉም የሚኖረው እውነትንና ፍቅርን መሠረት ሲያደርግ መሆኑን የምናስብበት ነው። መከራን በትዕግሥት ማለፍ መጨረሻው የትንሣኤ ብርሃን እንደሆነ ሁሉ፣ ዛሬ ሕዝባችን ያለበትን የመከራ መስቀል በጽናትና በአንድነት ከተሸከምነው፣ የነፃነታችን ትንሣኤ እውን መሆኑ አይቀርም።

ኢትዮ 251 ሚዲያ በዚህ ታላቅ ዕለት፣ በግፍ ለተገደሉ ንጹሐን፣ በመከራ ውስጥ ላሉ ወገኖቻችንና ስለ እውነት መሥዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የነፃነት አርበኞች ሁሉ ጽናቱንና ሰላሙን ይመኛል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነፃነት አንደበት!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio 251 News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share