Ethio Fact ኢትዮ ፋክት

Ethio Fact ኢትዮ ፋክት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Fact ኢትዮ ፋክት, Digital creator, Addis Ababa.

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ላቀርቧቸው ጥያቄዎች ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሰጡት ምላሽ
16/04/2025

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ላቀርቧቸው ጥያቄዎች ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሰጡት ምላሽ

#ዜና #ኢትዮጵያ Ethio Fact ወቅታዊ የኢትዮጵያን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ እንዲሁም የተረጋገጡና የትም ያልተሰሙ ዜናዎች የሚቀርቡባት የብዙኃ....

ልጅቱ:-"እየሱስ ያድናል አባ"አባ:-"አንች አትድኝም እንጅ እርሱስ ያድናል አዳኝ ነው"ልጅ ምጥ ለእናቷ ልታስተምር ስትሞክር     አለም በቃኝ ብሉ ስለኢየሱስ እየሰበከ የሚኖር መነኩሴ ወንጌ...
11/04/2025

ልጅቱ:-"እየሱስ ያድናል አባ"

አባ:-"አንች አትድኝም እንጅ እርሱስ ያድናል አዳኝ ነው"

ልጅ ምጥ ለእናቷ ልታስተምር ስትሞክር
አለም በቃኝ ብሉ ስለኢየሱስ እየሰበከ የሚኖር መነኩሴ ወንጌል ማስተማር ምነኛ ድፍረት ነው።

መልካም ምሽት

አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3 ለ ዐ አሸነፈአዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)  በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3 ለ 0 አሸንፏል።...
08/04/2025

አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3 ለ ዐ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3 ለ 0 አሸንፏል።

መድፈኞቹን አሸናፊ ያደረጉ ጎሎችን ዴክላን ራይስ (2) እና ሚኬል ሜሪኖ በ2ኛው አጋማሽ አስቆጥረዋል።

ካማቪንጋ በሪያል ማድሪድ በኩል በጨዋታው መጠናቀቂያ በ2 ቢጫ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በሌላ የምሽቱ መርሃ ግብር ኢንተር ሚላን ከሜዳው ውጭ ባየርን ሙኒክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ለኢንተር ጎሎቹን ላውታሮ ማርቲኔዝና ፍራቴሲ ሲያስቆጥሩ፥ ባለሜዳዎቹን ሙኒኮች ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ቶማስ ሙለር ከመረብ አሳርፏል።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ተረከቡ   | ጄኔራል ታደሰ ወረደ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን በዛሬው ዕለ...
08/04/2025

ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ተረከቡ

| ጄኔራል ታደሰ ወረደ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን በዛሬው ዕለት ተረከቡ።

ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

ዛሬ በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግርና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራምም ተከናውኗል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመሰገኑአዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ...
07/04/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት÷“በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት 62 (9)፣ አዋጅ 359/1995 አንቀጽ 15(3) እና ደንብ ቁጥር 533/2015 እንዲሁም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በተለይም አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ÷ለነበራቸው ቆይታም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የድምጻዊ አንዱዓለም ጠበቃ በችሎት፣  "የአስክሬን ምርመራ ውጤትና ማብራሪያው መጥቷል፡፡ ውጤቱ የሚያሳየው ሟች ከከፍታ ቦታ ላይ በመውደቋ መሞቷን ነው፡፡ የሟች አስከሬን ምር...
07/04/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የድምጻዊ አንዱዓለም ጠበቃ በችሎት፣ "የአስክሬን ምርመራ ውጤትና ማብራሪያው መጥቷል፡፡ ውጤቱ የሚያሳየው ሟች ከከፍታ ቦታ ላይ በመውደቋ መሞቷን ነው፡፡ የሟች አስከሬን ምርመራ ውጪያዊ ሠውነቷ የመበለዝ፣ የመቧጨር፣ ቀድማ መሞቷን ወይም ተገፍትራ መውደቋን የሚያሳይ ነገር የለም፡፡ ሟች ራሷን ነው ያጠፋችው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ሟች የዕለት ተዕለት ውሎዋን የምትፅፍበት ማስታወሻ ወይም ዲያሪ አግኝቷል፡፡ በዲያሪዋ ላይ ህይወቷን ልታጠፋ እንደምትችልና ለዚህም ውሳኔዋ ቤተሰቦቿ፣ አንዱዓለም እና ጓደኞቿ ይቅር እንዲሏት የሚጠይቅ ነው፡፡ ስለሆነም ደንበኛዬ በዋስ ወጥቶ የደረሰበትን ከባድ ሐዘን እንዲጨርስ ይፈቀድልን” ሲሉ ጠይቀዋል።

"ውጤት አልደረሰልኝም" ፖሊስ   #ሾውቢዝበቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመ...
07/04/2025

"ውጤት አልደረሰልኝም" ፖሊስ

#ሾውቢዝ
በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ የለበትም አንዱዓለም የዋስ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል ብሎ ተከራክሯል። በተጨማሪም ከእስር ወጥቶ የሙዚቃ ስራውን ለፋሲካ ያቅርብ የሚለው የዩቲዩብ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሊታረም ይገባል ብሏል።

ፍርድ ቤት የሁለቱን ክርክር ከሰማ በኋላ የክርክሩን ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ማክሰኞ ጠዋት ቀጥሮ ሰጥቷል።

ሰበር ዜና ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የሸኔው መሮ ዋና ሰው እንደሆነ የሚታወቀው መገደሉ ተገለፀ። የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድ...
05/04/2025

ሰበር ዜና

ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ

ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የሸኔው መሮ ዋና ሰው እንደሆነ የሚታወቀው መገደሉ ተገለፀ።

የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድርድር ከጫካ ወጥቶ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ድረስ ከመሮ ጋር ተጉዞ የሸኔ ሽብር ቡድን ተደራዳሪ የነበረው ሾዴ በተወሰደበት እርምጃ ተገድሏል።

ሾዴ የተባለው የሽብር ቡድኑ አመራር ከታንዛኒያ መልስ የአጠቃላይ የወለጋ ዞኖች አዛዥ ተደርጎ በመሮ ተሹሞ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ሾዴ የተገደለው ምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ገንጂ አካባቢ ከኮርማ ወንዝ ወደ ሱጊ በሚወሰደው መንገድ ላይ በሞተር ሳይክል ተደብቆ ሲጓዝ የፀጥታ ኃይሎች ባገኙት መረጃ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እርምጃ ተወስዶበታል።

ከሾዴ ጋር አብረው አጅበው ሲጓዙ የነበሩ በርካታ የሸኔ ሽብር ቡድን አባላትም ተደምስሰዋል።

ከሠሞኑ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በሌሎችም አካባቢዎች የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ክፉኛ እየተመቱ በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን የሸኔ ታጣቂዎች የመከላከያ ሠራዊቱን ምት መቋቋም ተስኗቸው እየተፍረከረኩ እጅ እየሠጡ እየተማረኩ እርምጃ እየተወሰደባቸውና እየተበተኑ ይገኛሉ።

መረጃው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገፅ ነው

በአዲስ አበባ የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT) ግንባታ በተያዘው ዓመት እንደሚጀመር ተገለጸ  | በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚሰራው የፈጣን አውቶብስ መስመር (Bus Rapid Transit ...
03/04/2025

በአዲስ አበባ የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT) ግንባታ በተያዘው ዓመት እንደሚጀመር ተገለጸ

| በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚሰራው የፈጣን አውቶብስ መስመር (Bus Rapid Transit - BRT) ግንባታ በተያዘው ዓመት እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዳኛቸው ሽፈራው ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በቅርብ ዓመታት ውስጥ 15 የፈጣን አውቶቡስ መስመር (BRT) ግንባታዎች ይጠናቀቃሉ ተብሎ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ ከጀሞ 3 እስከ ፒያሳ አድዋ ድረስ የመጀመሪያ የሚሆነው ግንባታ በዘንድሮው ዓመት ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

19 ኪሎ ሜትር የሚሆነው ይህ መስመር በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ ታግዞ የሚሰራ ሲሆን፤ ለኮንትራክተር ሙሉ ኃላፊነት መሰጠቱና የግንባታው ሂደትም በተያዘው ዓመት እንደሚጀመር ተመላክቷል።

የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታው ሲሰሩ ከመደበኛው የመኪና መስመር የተለየ ቦታ እንደሚኖረው የገለጹት ምክትል ኃላፊው፤ አሁን ላይ አውቶቡሶች ሰዎችን ለመጫንና ነዳጅም ለመቆጠብ ሲባል ሰው እስኪሞላ ድረስ የሚጠብቁበት አግባብ መኖሩን አንስተዋል።

በመሆኑም የፈጣን አውቶብስ መስመሩ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ግን ሰው እስኪሞላ የሚጠበቅበትና ቆመው የሚሄዱበት ጉዳይ እየቀረ ስለሚሄድ፤ ሰዎች በሚፈልጉበት ሰዓት ሳይቸገሩ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማግኘት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።

የፈጣን አውቶቡስ መስመሮችን የተለያዩ የዓለም ሀገራት ጭምር ተጠቅመው ጥሩ ውጤት የታየበት መሆኑን የገለጹት ምክትል ኃላፊው፤ "በተያዘው ዓመት የሚጀመረው ግንባታ በሂደት ላይ እያለ ሌሎች መስመሮችም እንዲሰሩ ይደረጋል " ብለዋል።

አክለውም ወደፊት በከተማዋ ሁለት አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን፤ አንደኛው የብዙሃን ትራንስፖርት የሚባለው ባቡር እንዲሁም ቀላልና ፈጣን የአውቶቡስ ሲሆን ሌላኛው መካከለኛ ገቢ ያላቸው የሚጠቀሙበት ተብሎ የሚታሰበው የታክሲ አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል።


ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

"""""""""""***""""""""""
ዩቲዩብ ገጽ: https://youtube.com/channel/UCDn81lZTuIGrWyDtjJen-Rg?si=bVwudn_oLISS7Lnq

ሰበር| ጃዋር ስለአዲሷ ፍቅረኛው ተናገረ | ትዳሩ መፍረሱ ታወቀ |
01/04/2025

ሰበር| ጃዋር ስለአዲሷ ፍቅረኛው ተናገረ | ትዳሩ መፍረሱ ታወቀ |

#ዜና #ኢትዮጵያ Ethio Fact ወቅታዊ የኢትዮጵያን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ እንዲሁም የተረጋገጡና የትም ያልተሰሙ ዜናዎች የሚቀርቡባት የብዙኃ....

"በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ አዲስ ምዕራፍ በተሰኘ ፕሮግራሙ እሑድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ...
01/04/2025

"በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ አዲስ ምዕራፍ በተሰኘ ፕሮግራሙ እሑድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ እርምጃ ወስጃለሁ" ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገልጸ።
" በቴሌቪዥን ጣቢያው የቀረበው ፕሮግራም በሐሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ ሕዝብን የሚያሳስትና ጥርጣሬን የሚፈጥር፣ የመገናኛ ብዘኃን አዋጅ 1238/2013፣ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ 1185/2012 እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባርን፣ መደበኛ የጋዜጠኝነት አሰራርን የሚጥስ የፓራጆርናሊዝም አሰራርን የተከተለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡" ሲል መግለጫ የሰጠው ባለስልጣኑ "ጣቢያውም በፕሮግራሙ ዙሪያ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ያሰራጨው ፕሮግራም ሐሰተኛ መሆኑንና ስህተት መፈጸሙን ገልጿል፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣኑ ጉዳዩን መርምሮ በጣቢያው የሚሰራጨው “አዲስ ምዕራፍ” የተሰኘ ፕሮግራም በኤዲቶሪያል አሰራሩ ላይ አስፈላጊውን እርምት ወስዶ ለባለሥልጣኑ እስኪያሳውቅና ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የአዲስ ምዕራፍ ፕሮግራም በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሰረት ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ" መወሰኑን አስታውቋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Fact ኢትዮ ፋክት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Fact ኢትዮ ፋክት:

Share