Nocho Multimedia Production

Nocho Multimedia Production Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nocho Multimedia Production, Broadcasting & media production company, Addis Ababa.

ኖቾ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በፈጠራና ወጣት በሆኑ የኪነጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች የተሞላ የሚዲያና የመዝናኛ ድርጅት ሲሆን… ከ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን (Ethiopian Media Authority) የብቃት ማረጋገጫ በመዉሰድና ፍቃድ በማዉጣት በዋናነት መቀመጫዉን በመድናችን አዲስ አበባ አድርጎ የተለያዩ የሚዲያና የኪነ-ጥብብ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነዉ።

26/07/2026

በ85.5 ሚልዮን ብር የተገነባው ድልድይ ተመረቀ

🏅 ወደ ዳካር 2026 100 ቀናት ቀሩ! ዛሬ ትልቁ ባለ ሁለት አሃዝ ቁጥር ላይ ደርሰናል! ከኦክቶበር 31 እስከ ኖቬምበር 13 ቀን 2026 በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የዳካር...
24/07/2026

🏅 ወደ ዳካር 2026 100 ቀናት ቀሩ!

ዛሬ ትልቁ ባለ ሁለት አሃዝ ቁጥር ላይ ደርሰናል! ከኦክቶበር 31 እስከ ኖቬምበር 13 ቀን 2026 በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የዳካር 2026 የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ፣ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ2,700 በላይ ወጣት አትሌቶች የሚሳተፉበት ውድድር ለመጀመር 100 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

🇪🇹 ኢትዮጵያ በአምስት የስፖርት አይነቶች ትሳተፋለች ተብሎ ይጠበቃል፦
🏃 አትሌቲክስ
🚴 ብስክሌት
🥋 ቴኳንዶ
🏊 ዋና
🥋 ውሹ

🏅የማጣሪያ እና የምርጫ ሂደቶች ከተጠናቀቁ በኋላ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የተረጋገጠው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ቡድን። ዳካር 2026! ለአፍሪካ ታሪካዊ ወቅት ዳካር 2026 ለኦሎምፒክ እንቅስቃሴ ትልቅ ስኬትን ያመለክታል።
የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ማስተናገድ በመላው አህጉሪቱ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን እንደሚያነሳሳ፣ እንዲሁም በስፖርት፣ በትምህርት እና በወጣቶች ልማት ላይ በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት ዘላቂ አሻራ እንደሚያሳርፍ ይጠበቃል።
የ100 ቀናት የመቁጠሪያ ጊዜ ሲጀመር፣ ኢትዮጵያ የማይረሱ የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ከዓለም ጋር ትቀላቀላለች፤ የአገሪቱ ቀጣይ ትውልድ የስፖርት ኮከቦችም በአፍሪካ ትልቁ የኦሎምፒክ መድረክ ላይ ችሎታቸውን ለማሳየት ዝግጁ ናቸው።

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፌስቡክ ገጽ ነዉ።
ኖቾ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፣ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገፆቻችን ያገኙናል።
YouTube - http://www.youtube.com/
Tiktok - www.tiktok.com/
Telegram - https://t.me/+d0wRonggq

23/07/2026

ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በትጋት እየሠራ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች በትጋት በመስራት ላይ ትገኛለች። መንግስት የተለያዩ ስትራቴጂና ፖሊስ ቀርጾ ወደ ልማት ከገባባቸው ዘርፎች አንዱ የስፖርት ዘርፍ ይገኝበታል።

ስፖርት እጅግ ሰፊና ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን ከዚህም መካከል በኦሎምፒክ የተመዘገቡና እውቅና ተሰጥቷቸው በተለያዬ ጊዜ የሀገራችንን ስም ከፍ የሚያደርጉ የውድድር አይነቶች ይገኛሉ።

በኦሎምፒክ ሀገራችን የነበራትን ስምና ዝና ለማስጠበቅና ገናና ታሪካችንን ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተተኪ ወጣቶች ላይ በትጋት እየሰራ እምደሆነ የኢፌዴሪ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕረዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በትናንትናው እለት ለተተኪ ተመራጭ አትሌት ስፖርተኞች አስገንዝበዋል ።

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፌስቡክ ገጽ።
ኖቾ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፣ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገፆቻችን ያገኙናል።
YouTube - http://www.youtube.com/
Tiktok - www.tiktok.com/
Telegram - https://t.me/+d0wRonggq

19/07/2026

ዶናልድ ትራምፕ የምታደሙበት የአለም ዋንጫ

A little about "Christmas" (ገና)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና በመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ አብይ በዓላት አንዱ የጌታችን መድሀኒታችን ...
06/01/2026

A little about "Christmas" (ገና)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና በመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ አብይ በዓላት አንዱ የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል "ገና" ነዉ።

"ገና" የሚለዉ ቃል ከጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ የተወረሰ ቃል እንደሆነና ትርጉሙም "ልደት" ማለት እንደሆነ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ።

"ገና" የሰዉን ልጆች በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ (ኢየሱስ) ሰዉን ለማዳን ሰዉ ሆኖ የተፈጠረበት ቀን ሲሆን፣ በዓለ ልደት በየአመቱ የሚከበረው ታህሳስ 29 እና በዘመነ ዮሐንስ ግን የሉቃስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ስለምትሆን ልደቱ ታህሳስ 28 ይዉላል።

በዚህ እለትም የገና በዓልን የምታከብረው ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የእስክንድርያ ቤተክርስቲያንም በደማቅ ስታከብር፣ በግብፅ፣ ኤርትራ፣ (በተለይ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች)፣ ሶሪያ፣ ህንድ፣ አርመን፣ ግሪክ እና ሩሲያ ያሉ ክርስትያኖች ገናን በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 (በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ ታኅሣሥ 28) በደማቅ መልኩ ያከብሩታል።

👉 ኖቾ መልቲሚዲያም በማረሚያ ቤት ላሉት እና በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የገና በዓል እንዲሆን ይመኛል!
✍️ እስራኤል ግርማ (Ezra)

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 200 ዓ.ም። እና የተለያዩ........

ኖቾ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፣ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገፆቻችን ያገኙናል።
YouTube - http://www.youtube.com/
Tiktok - www.tiktok.com/
Telegram - https://t.me/+d0wR-A2xqk45YmQ0
page – Nocho Multimedia Production

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nocho Multimedia Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share