የኛ page

የኛ page ፍቅር ለሁላችን ሰላም ለሀገራችን

ትክክለኛ መረጃ ለህዝባችን

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልል መሰል ተቋሞች ተቋማቶች ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ድርጊት ተደርጓል አሁን ደግሞ የባሰ እናንተ በየቢሮአችሁ ቁጭ ብላችሁ ስታንቀላፉ ይሄን ድርጊት የፈ...
27/06/2026

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልል መሰል ተቋሞች ተቋማቶች ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ድርጊት ተደርጓል አሁን ደግሞ የባሰ እናንተ በየቢሮአችሁ ቁጭ ብላችሁ ስታንቀላፉ ይሄን ድርጊት የፈፀሙ ወጣቶች ግን ጭካኔ እንዴት እንደሆነ እየተማሩ እና ታናናሾቻቸውን እያስተማሩ ነገ የሰው ልጅንም እንደዚህ ባሰቃቂ ሁኔታ ይጨፈጭፋሉ ምክንያቱም ጭካኔን በእንስሳት ላይ የተለማመዱ ስለሆነ እናንተን አንቅቶ ለድርጊቱ እርምጃ እንድትወስዱ ለማድረግ የግድ የሆነ አካል እናንተ ማንቃት አለበት:: ሆሳዕና አካባቢ ያላችሁ የመንግስት ኃላፊዎች ታሳፍራላችሁ::Abiy Ahmed Ali Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ Addis Ababa Police Ethiopian Federal Police Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ Addisu Arega Kitessa እናንተም የመንግስት ባለስልጣናት እና መሰሎች ወጣቱ በየቦታው ተደራጅቶ ጭካኔን ሲለማመድ ዝም ማለት ነገ የበለጠ ለሀገር ኪሳራ የመጣል:: የምንሰማቸውን አሰቃቂ ግድያዎች በሰው ላይ የሚደርሱ እንደዚሁ ጭካኔን በእንስሶች ላይ እየተለማመዱ ነው:: እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት የሚሰሩትን እያዩ ዝም ማለት ሀገራችን አሁን ካለችበት ችግር የባሰ ችግር ውስጥ ይከታታል ምክንያቱም ጨካኝ ትውልድ እየተፈጠረ ነው::

መልካም ዕድል Abiy Ahmed Ali
01/06/2026

መልካም ዕድል Abiy Ahmed Ali

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

13/05/2026
ከዳላስ እስከ ኢትዮጵያ፦ የፍቅር እና የርህራሄ ድልድይ የሆነው በፍቃዱ እና የዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ! በየዓመቱ ከአሜሪካ ዳላስ ተነስቶ ለተቸገሩ ወገኖቹ ደስታን ይዞ የሚመጣው ተወዳጁ...
22/02/2026

ከዳላስ እስከ ኢትዮጵያ፦ የፍቅር እና የርህራሄ ድልድይ የሆነው በፍቃዱ እና የዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ!

በየዓመቱ ከአሜሪካ ዳላስ ተነስቶ ለተቸገሩ ወገኖቹ ደስታን ይዞ የሚመጣው ተወዳጁ በጎ አድራጊ በፍቃዱ፣ ዘንድሮም በአስደናቂ የበጎ አድራጎት ስራው ደምቆ ታይቷል።

በፍቃዱ በዳላስ ከሚኖሩ ለጋስ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር በአጠቃላይ 2,322,000 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ) ብር በመሰብሰብ ለወገኑ ደርሷል።

ይህ ትልቅ የገንዘብ መጠን ለሁለት ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በእኩልነት ተከፋፍሎ ተበርክቷል፦

* ለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት፦ 1,161,000 ብር
* ለካሊድ ፋውንዴሽን ድርጅት፦ 1,161,000 ብር

ይህ በጎ ተግባር የገንዘብ እርዳታ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያውያንን አንድነት፣ መተሳሰብ እና ለወገን ያለን ፅኑ ፍቅር ማሳያ ነው።

* በፍቃዱን እናመሰግናለን በየዓመቱ ሳይታክት፣ ድንበር ሳይገድበው፣ ጊዜውን እና ጉልበቱን መስዋዕት አድርጎ ይህን ቅዱስ ተግባር ስለሚያከናውን ታላቅ አክብሮት ይገባዋል።

* የዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እናንተ የኢትዮጵያ ኩራቶች ናችሁ! በባዕድ ሀገር ሆናችሁ ለወገናችሁ የዘረጋችሁት እጅ የብዙዎችን እንባ አብሷል፣ ተስፋም ሆኗል።

“ ለሰው ልጅ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው"
የሚለውን እውነት በተግባር አሳይታችኋል።

እንደነዚህ አይነት በጎ አድራጊዎች በበዙልን ቁጥር የሀገራችን ችግር ቀልሎ፣ ተስፋችን ይለመልማል።

"ቸርነት ለራስ ነው!"

©️Seifu on EBS

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኛ page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የኛ page:

Shortcuts

Share