10/07/2025
❗ ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ወርሃዊ በዓል ነው ምክንያቱም እርሷ ለእግዚአብሔር የስዕለት ልጅ ነበረችና።
🔷👉 ታዲያ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው ብለን ብቻ ማለፍ ሳይሆን እንዴት እንደገባች ማወቅ ያስፈልጋልና አጠር አድርገን እንመለከታለን።
🔴👉 የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጅ እናት ቅድስት ሐና ትባላለች። እናታችን ቅድስት ሐናም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግሥት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት።
🔴👉 እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲጸልዩ ሲያዝኑ ዋሉ። ሀዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም፡- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ጸሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ/ች ወንድ ወይም ሴት ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ። ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማኅጸኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች።
🔷👉 እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ዐይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ፣ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ፣ መሶብ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ፣ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
🔷👉 ከዚያም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱኑ ራዕይ ዐይተው ነገር አግኝተው አደሩ። ራዕዩም ኢያቄም “ርኢኩ በህልምየ እንዘ ይትረኀው ሰባቱ ሰማያት - ፯ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነጭነቱ ንጽሐ ባሕሪው ነው፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ ዐየሁ ማለቱ፤ አምላክ የኢያቄምን ( የሰውን) ባሕርይ ባሕርይ እንዳደረገው ሲያጠይቅ ነው፤ ፯ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩ መንግሥቱ ናቸው።
🔴👉 ሐናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፤ “ዖፍ ጸዓዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርዕስየ ወቦአት ውስተ ዕዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርስየ - ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ነጭ መሆንዋ ንጽህናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ድንግልናዋ ነው። ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው። ይህንኑም ራዕይ ያዩት ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ዕለት ነው።
🔷👉 እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆ