
07/08/2025
ሐና ዊልያም በማደጎ ወደ አሜሪካ ስትመጣ የ8 ዓመት ልጅ ነበረች። የመጣችበት ቤት ግን ተገቢውን እንክብካቤ አልተደረገላትም ። ኬሪ ውልያም እና ባለቤትዋ ላሪ ውልያም ሰድስት ልጆች ያላቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ሐናን እና አንድ የ10 ዓመት ወንድ ልጅ በማደጎ ወደ አሜሪካ አምጥተዋል።
እ.አ. አ May12, 2011 ኬሪ ዊልያም 911 በመደወል ልጇ ሀና ዊልያም ራስዋን ስታ መሬት ላይ መውደቅዋን ህይወቷ እንዳለፈ ትናገራለች።
ነገሩ እንዲህ ነው ።
ሐና በማደጎ የገባችበት ቤት ገሀነብ ሆኖባት ነበር። ሐና ብዙ ድብደባ ተፈጽሞባታል፤ በርሃብ ተቀጥታለች። በተደጋጋሚ በረሃብ ከመቀጣትዋ የተነሳ ሰውነቷ እጅግ በጣም የከሳ ነበር።
May10 ሐና ጥፋት አጠፋች ተብላ ቅጣትዋ ውጪ መቆየት ነበር። ከፍተኛ ዝናብ እና ብርድ በጣም ነበረ። ኬሪ እንደምትለው ሐና እቤት እንድትገባ ብትጠራ። አልገባም እንዳለች እና ውጪ መቆየት እንደመረጠች ነው፤ ይህ ግን ውሸት ነው፤ ሐና ውጪ የነበረችው ቅጣት ተበይኖባት ነው። በርሀብ የተጎዳው የሐና ሰውነት በዛን ቀን የነበረውን ብርድ አልቋቋም ብሎ ነው ህይወቷ ሊያልፍ የቻለው። ሐና ሰውነቷ በጣም የከሳ፣ ፀጉሯ የተቆራረጠ እና በሰውነቷ ላይ ብዙ የመደብደብ ምልክቶች እንደነበሩ ፖሊስ ተናግሯል ።
ኬሪ ውልያም እና ላሪ ውልያም ፍርድ ቤት ቀርበው ሁለቱም ጥፋተኛ ተብለዋል። ኬሪ ወደ 37 ዓመት የጽኑ እስራት የተፈረደባት ሲሆን። ላሪ ውልያም ወደ 28 ዓመት ተፈርዶበታል። በወቅቱ ከኢትዮጵያ በማደጎ ያመጡት ወንድ ልጅ እና የነሱ ሰድስት ልጆች ግዜያዊ ማቆያ ተወስደዋል።
ሐና ውልያም ( ለማደጎ ከመሰጠትዋ በፊት ሙሉ ስሟ ሐና አለሙ በፍቃዱ ነበር ) በማደጎ የተሰጠችው በ2008 ነበር፤ ሶስት የስቃይ ዓመታትን አሳልፋ በመጨረሻም ረሃብ እና ዱላ መቋቋም ያቃተው ሰነትዋ ወደ ዘላለማዊው እረፍት ሄዷል።
እ.አ.አ ከ2008 እስከ 2011 ባለበት ዓ.ም ወደ 13ሺ ኢትዮጵያኖች ወደ አሜሪካ በማደጎ መጥተዋል ።
ሐና ከዛ ስቃይ ህይወት ካረፈች 14 ዓመት ሆናት ። ነፍስ ይማር 🙏
|***
👤 በመንበረ ካሳዬ Menbere Kassaye
ጣዕም ሚዲያ
🎙የሚያነሳሱ ታሪኮች፤ የሚያገናኙ ድምፆች